>

"ውሸትን በዜና በመግለጫ ደጋግሞ በማወጅ እውነት ማድረግ አይቻልም!!" (ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና)

“ውሸትን በዜና በመግለጫ ደጋግሞ በማወጅ እውነት ማድረግ አይቻልም!!”
ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና
 በኢሳት እለታዊ
ዛሬ “መኖር ይችላሉ” ከተባልክ ነገ “ከፍለህ ኑር” ከነገወዲያ ” ንብረትህን ትተህ ውጣ!!” መባሉ የማይቀር ነው!!!
 
እኛ ሃገር አንድነቷ እንዳይከስም ሁሉንም ነገር በጥሞና እና ሁሉንም ተጠቃሚ ባደረገ መልኩ እንድትሄድ እየታተርን እንገኛለን።
በተደጋጋሚ እንደሚታየው ግን በኦሮሞ ስም የተደራጁ ድርጅቶች (የኦሮሞን ህዝብ ባይወክሉም) ሃገር በትንሽ ፊደል ቀመሶች እንደምትመራ የታወቀ ነው። የተለያዩ ብሄር ልሂቃኖች ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ሲያስቡ የኦሮሞ ፊደል ቀመሶች ደግሞ ባሪያ መሆንን ስለመፈለግ ነው የሚሰብኩት። ዛሬ በእነ አቶ በቀለ ገርባ የተነበበው ጥራዝ ነጠቅ መግለጫ የአዲስ አበባን ህዝብ “ስደተኛ” አድርጎ ከመቁጠር አልፎ የአማራን ህዝብ ልእልና የሚያጠፋ በደናቁርቶች የረቀቀ መግለጫ ነው።
አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና ናት
አዲስ አበባ የኢትዮጵያ መዲና ናት
አዲስ አበባ የዓለም ከተማ ናት
አዲስ አበባ ራሷን የቻለ የነቃ ህዝብ ያለባት በነፃነት ያለብሄር አተካራ የሚኖርባት የአዲስ አበቤዎች ሃገር ናት!!(አዲስ አበባ የአዲስ አበቤ ናት)
አዲስ አበባ ይሄ ሁሉ ካልሆነች እና ታሪክ እናገላብጥ ከተባለ .. የዘረ-ያዕቆብ ሃገር ..(የአማራ ሃገር ነች!) እደግመዋለው…. “ታሪክ እናገላብጥ ከተባለ እስከ ዝዋይ ድረስ ደብረዘይት፣ናዝሬትን አካሎ ምድሪቷ የአማራ ምድር ነች” ነገር ግን አሁን የአማራ አይደለችም!! የኦሮሞ ደግሞ ልትሆንም አትችልም!! ነገሮች በፍጥነት መስመር እንዲይዙ ይፈለጋል። መስመር ካልያዙ እና የተፋለሰ ዜና እያወጡ..ዜናውን በተፋለሰ መግለጫ እየደገፉ ውሸትን እውነት አድርጎ በመደጋገም የአዲስ አበቤን ህዝብ ብሎም የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማጥፋት የሚደረግ ዘመቻን እጃችን አጣጥፈን እሹሩሩ እያልን አንመለከትም!!
አዲስ አበባ የአዲስ አበቤዎች ናት ግን ኦሮሞም መኖር መብቱ ነው!! ማንኛውም ኦሮሞ መብቱ ተጠብቆ በሚፈልገው ቋንቋ ተናግሮ መኖር ይችላል። በተረፈ በዚህ በሰለጠነ ዘመን ወረራ አካሂዳለው ማለት ዋጋ ያስከፍላል።
ደጉ የኦሮሞ ህዝብ ፊደል ቆጥረናል የሚሉት የፖለቲካው መዝባሪዎች ሊያባሉህ ታጥቀው ተነስተዋል እና “ተዉ!!” በላቸው። ይሄ አካሄድ ለማንም ለምንም አይጠቅምም።
የአዲስ አበባ ህዝብ ስደተኛ ላለመሆንህ የሃገሩ ባለቤት ራስህ መሆንህን ለማሳየት ። በመዋቅር ተደራጅ እና ራስህን ተከላከል። ዛሬ “መኖር ይችላሉ” ከተባልክ ነገ “ከፍለህ ኑር” ከነገወዲያ ” ንብረትህን ትተህ ውጣ!!” መባሉ የማይቀር ነው። ስለዚህ ዘመቻው “የአዲስ አበባ ህዝብ አዲስ አበባ ላይ መኖር ይችላል¡¡” ሳይሆን መሆን ያለበት “ማንም ሰው አዲስ አበባ መኖር ይችላል፤ ኦሮሞም መኖር ይችላል ግን አዲስ አበባ የአዲስ አበባ ህዝብ ናት!!” የሚለው አቋም ነው!! (ምንጭ- ዳንኤል ገዛህኝ)

Filed in: Amharic