>

የብአዴን የማእከላዊ ኮሚቴ ሌጋሲ!! (ሚኪ ኣምሃራ)

የብአዴን የማእከላዊ ኮሚቴ ሌጋሲ!!
ሚኪ ኣምሃራ
1. 3.5 ሚሊየን የአማራ ህዝብ በሴፍቲኔት (በእርዳታ ስንዴ) እንዲኖር ተደርጓል፡፡
2. 1 ሚሊየን የአማራ ወጣቶች በአረብ ሀገራት ተሰደዉ የቀን ሰራተኛ እንዲሆኑ ተደረግዋል፡፡ በቅርቡ የአለም አቀፍ የስደተኞ ድርጅት በኢትዮጵያ ዉስጥ ከፍተኛ ስደት ያለበት አካባቢ ብሎ
ቢሮዉን አማራ ክልል ዉስጥ ከፍቷል፡፡
3. ለክልሎች የሚበጀተዉን በጀት በህዝቡ ፕሮፖርሽን ስንሰራለት ከ9ኙ ክልሎች የመጨረሻዉን ይይዛል፡፡ 8ቱ ክልሎች በግለሰብ ደረጃ ሲሰላ ከ 1ሺህ ብር በላይ ሲደርስ የአማራ ክልል 700 ብር ነዉ።
4. ኢንዱስትሪ የሚባል እንኳን መሬት ላይ ወረቀት ላይ የለም፡፡
5. ከ 1 ሺህ ሜጋ ዋት በላይ መብራት መብራት በክልሉ ዉስጥ ቢመረትም የክልሉ ህዝብ ወፍጮ እንኳን አስፈጭቶ እንዳይበላ በመብራት እጦት በእጁ ነዉ የሚፈጨዉ፡፡ መብራት እና መኪና
ሚባል አይተዉ የማያዉቁ ወደ 6 ወረዳወች አሉ።
6. 3 ሚሊየን ወጣቶች ስራ አጥ ናቸዉ፡፡
7. ከ 25 ሺህ በላይ የዩኒቨርስቲ ተመራቂዎች ስራ አጠዉ ከተቀመጡ አመታት አለፋቸዉ።
8. ከ 1500 በላይ የዳስ ትምህርት ቤቶች አሉን፡፡ወደ 50 ሺህ ዜጎች  እስር ቤት ገብተው ግማሹ ወጥቷል ግማሹ የእስር ቤቱ ነዋሪ ሆኗል፡፡
9. በሃገሪቱ ዝቅተኛዉ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አሉን፡፡
10. 45 በመቶ የሚሆኑት የአማራ ህጻናት በምግብ እጥረት ምክንያት የመቀንጨር ችግር ያጋጥማቸዋል።
11. ከ 2008 እስከ 2010 ብቻ ከ 1500 በላይ አማሮች ተገድለዋል፡፡ ወደ 50 ሺህ እስር ቤት ገብተዋል፡፡
12. በባለፉት ትቂት አመታት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል 150 ሺህ አማራ ከቀየዉ ተፈናቅሏል፡፡
13. ክልሉ ዉስጥ የገበሬዉ መሬት እየተቀማ ለጠላት እንዲያርስ ተሰጥቷል (ለምሳሌ ብር ሸለቆ፤ አየሁ፤ እና ዘለቀ እርሻ ልማቶች)
14. ጥረት የተባለ ድርጅት ከ 2 ቢሊየን ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ አባክኗል፡፡ ድርጅቱ የተያዘዉም በ 3 ቤተዘመዶች ነዉ፡፡
15. ባንኮች በሌሎች ክልሎች ለባለሃብቶች እና ወጣቶች በአመት እስከ 20 ቢሊየን ብር ያበድራሉ፡፡ አማራ ክልል ባለፈዉ አመት ለምሳሌ ልማት ባንክ 200 ሚሊየን ብር ብቻ አበድሯል፡፡
16. የትራነስፎርሜሽን አቅድ የሚባለዉ አንዲት ፕሮጀክት በአማራ ክልል ዉስጥ ሊሰራ ቀርቶ የእቅዱ አካል አይደለም፡፡ ለብአዴን የትራንድፎርሜሽን አቅድ ማለት የ 1ለ5 ሪፖርት ነዉ፡፡
17. ከጅቡቲ የሚመጣዉ ባቡር የአማራ ከተሞችን እንዳይነካ በርሃ ለበርሃ ሲሰመር ብአዴን ቁጭ ብሎ ያይ ነበር፡፡
18. ትልቁ ክልልና የቱሪዝም መዳረሻ ቢሆንም ያሉት 3 የአየር ማረፊያዎች ብቻ ነዉ፡፡ በመንገድ መሰረተ ልማት ከአለም ዝቅተኛዉ ነዉ እንደ አለም ባንክ ጥናት መሰረት።
19. ግፋችሁ ተቆጥሮ አያልቅም እና 80 በመቶዉ የሚሆነዉ የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ተጠርጎ
መባረር አለበት፡፡ ደግሞ ደህና እንደሰራ እወጣለዉ አልወጣም እያለ የሚያለቃቅስ መኖሩ ነዉ የሚገርመዉ፡፡
……
ተጨማሪ፡
በአጭሩ የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ክልሉን ሳይመራው ስለቆየ  ከመሸ በኋላ ዛሬ ህዋኃት ተጭኖኛል ብሎ እያወራ ነው፡፡ ክልሉን በትክክል እየመራነው አልነበርነም ብለው አቶ ገዱ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ብአዴን የፖለቲካ ድርጅት እንጂ የስራ ዕድል መፍጠሪያ አማራጭ መሆን የለበትም፡፡
ብአዴንን የስራ ዕድል መፍጠሪያ አማራጭ ብቻ ያደረጉት ሌላ ስራ ይፈለግላቸው፡፡ ብአዴን በቀጣዩ ጉባዔ ከአማራ ህዝብ ጋር  ወይ ተለውጦ ይደመራል አሊያም ሰማኒያውን  ቀዶ ፍች ይፈፅማል!!!
Filed in: Amharic