>
5:13 pm - Thursday April 19, 9331

ከጠላት ጋር ሆናችሁ የኦሮሞ ትግልን ወደኋላ ለመመለስ ያሰባችሁ ከጠላት ለይተን አናያችሁም!! ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ 

ከጠላት ጋር ሆናችሁ የኦሮሞ ትግልን ወደኋላ ለመመለስ ያሰባችሁ ከጠላት ለይተን አናያችሁም!!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ 
 
የኦህዴድ እና የኢህአዴግ ሊቀመንበር እንዲሁም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በጅማ እየተካሄደ ባለው የኦህዴድ 9ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ ከተናገሩት የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች:-
* “ከዚህ በኃላ በኦሮሞ ህዝብ ስም መነገድ የለም። ኦሮሞ የሞተላትን ሃገር ጥሎ ወዴትም አይገነጠልም። ኦሮሞ ከኢትዮጵያ ውጭ ሃገር የለውም አይኖረውም። ኢትዮጵያ ብዙ አባቶቻችን ከአድዋ ጀምሮ ዋጋ የከፈሉባት ሃገራችን ነች። አንዳንዶች ጠዋት ስለ አንድነት አብሮነት እያወሩ ማታ ሃገር ስለማፍረስ ይዶልታሉ። መደመር እንደዚ አይደለም።የኦሮሞ ህዝብ ወላዋዮችን ይጠየፉል። የምትበተን ኢትዮጵያ ይለችም። ኦሮሞ ባህሉ ማቀፍ እንጅ ጥላቻ ዘረኝነት አይደለም።
 
 ኢትዮጵያን እንገነባለን፣ አፍሪካን እንገነባለን፣ ማንም ኃይል ደግሞ ከዚህ ሊያቆመን አይችልም፡፡
 ኦሮሞ ማቀፍን፣ እናት የሌላቸውን ልጆች ማሳደግን ነው ያስተማረን፣ ኦሮሞ ከተዋጋ ያሸንፋል እንጂ ሰውን መግደልን አላስተማረንም፡፡
 የዚህ አገር አንድነት ለማስጠበቅ ኦሮሞ ኃላፊነት አለበት፡፡
 ኢትዮጵያ ከጠላት ጋር ባደረገችው ጦርነቶች ውስጥ ኦሮሞ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡
 አባጅፋር ለኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያም ጭምር አርቀው የሚያስቡ ነበሩ፡፡
 አሁን ባለንበት ዘመን በትናንትናው ስልት ማሸነፍ አይቻልም፡፡
 ኦሮሞ አገር መምራት አይችልም የሚሉን አሉ፤ ኦሮሞ አገር መምራት ብቻ ሳይሆን አገር መገንባት ይችላል፤ ኦሮሞ ገዳን ለዓለም እንደ ሰጠ ሁሉ፣ ኦሮሞ በቅርቡ አዲስ ፍልስፍና ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ሰጥቶ ሊያሳያቸው ይፈልጋል፡፡
 የሚዲያ ጦርነት፣ የጦር ሜዳ ጦርነት፣ የኢኮኖሚ ጦርነት ማድረግ ስለምንችል ጠላቶቻችን ሁለት ሶስቴ ማሰብ አላባችሁ እንላለን፡፡
 ከጠላት ጋር ሆናችሁ የኦሮሞ ትግልን ወደኋላ ለመመለስ ያሰባችሁ ካላችሁ ከጠላት ለይተን አናያችሁም፡፡
 የህግ የበላይነት የማስከበር ኃላፊነት ለማንም አሳልፈን አንሰጥም፡፡
 ከዚህ በኋላ በኦሮሞ ስም መነገድ አይቻልም፡፡
 አስራ አምስት፣ ሃያ ሆኖ ለኦሮሞ መታገል አያስፈልግም፤ ከበዛ ሁለት ሶስት ፓርቲዎች ለኦሮሞ በቂ ናቸው፡፡
 አብሮ መቆም ማለት ጠዋት ጠዋት እዚህ መቆም ከሰዓት፣ ከሰዓት ደግሞ እዚያ መቆም ማለት አይደለም፡፡
 ከሁሉም ኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር በጋራ በአንድነት ተባብረን መስራት አለብን፡፡
 ኦሮሞነት በርካታ ነገሮችን አስተምሮናል ፤ በገዳ ስርዓት መሰረት ብሔር ብሔረሰቦችን አቅፈን በጋራ መስራት ይጠበቅብናል፡፡
 ዋናው መልዕክት አሸናፊን ሀሳብ መያዝ ነው
Filed in: Amharic