>

 ነፃ አውጪዎቹ ህውሓትና ኦነግ  እንዲህ ታጥቀዋል፣ ተደራጅተዋልም!!! (ዘመድኩን በቀለ)

 ነፃ አውጪዎቹ ህውሓትና ኦነግ 
እንዲህ ታጥቀዋል፣ ተደራጅተዋልም!!!
 ዘመድኩን በቀለ
ምንጊዜም ቢሆን “ጥቂት የተደራጁ አካላት ሚሊዮኖችን እንደበግ የመንዳት አቅም አላቸው።” እንዲያም ሆኖ ግን የሚሸነፍ መንግሥት እንጂ የሚሸነፍ ህዝብ የለም። አከተመ። 
#ETHIOPIA  | ~ የኢትዮጵያ ሠራዊት ሆይ ከወዴት አለህ ? አሁን በሀገሪቱ የሚታየው ወታደር በኢትዮጵያ ሀብት የሚንቀሳቀስ የፓርቲዎች ጠባቂ ጋርድ ነው። ይኸው ነው።
አብዛኛው ሰው ለተቃውሞ ሲወጣ ፖሊስና ወታደር መከላከያም ሲያይ የራሱ ይመስለዋል። ይኮራልም። ተስፋም ይጥልበታል። ደኅንነትም ይሰማዋል። ነገሩ የተገላቢጦሽ የሚሆነው። ህዝብም በሠራዊቱ ላይ እምነት የሚያጣው ወታደሩ ወዲያውኑ በዚያው ፍጥነት ሰላማዊ ሰልፈኛውን እንደ አልሸባብ ቆጥሮ የጥይት ናዳ አውርዶ ሲረፈርፈው ነው።
አሁን ሁለት ነፃ አውጪ ድርጅቶች እስከአፍንጫቸው ታጥቀዋል። ህውሓትና ኦነግ። የዋሁ ህዝብ ደግሞ የኦነግና የህውሓትን ጥፋት ለመቃወም አደባባይ ይወጣል። አደባባይ ሲወጣ ግን የሚያየው ፣ የሚያገኘውም የኢትዮጵያን ጦር፣ መከላከያውን፣ የሀገሪቱንም ፖሊስ ልብስ የለበሱ ወታደሮችን ነው። እነዚህ ወታደሮች ግን ላያቸው የኢትዮጵያ ወታደር ቢመስሉም ውስጣቸው ግን በፓርቲ ፍቅር ያበደ ነው። እናም ፓርቲያቸው ያጠፋውን ጥፋት የሚቃወም ሰው ሲመጣ ድብን አድርገው ለፓርቲያቸው ዘብ ይቆማሉ። ችሎታቸውም ፣ ሙያቸውም መግደል ነውና ለፓርቲያቸው ሲሉ የፓርቲያቸውን ተቃዋሚዎች በአደባባይ ይገድላሉ።
እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ ያለ ራሱ በሚከፍለው ግብር የሚያኖረውና የሚያስተዳድረው የራሱ ሀገር የጦር ሠራዊት መልሶ ራሱኑ የሚገድለውና የሚጨፈጭፍ ሠራዊት ተመልክቼ አላውቅም። በቱርክ የሀገሪቱን ፕሬዘዳንት ኤርዶጋንን ለመገልበጥ ወታደሩ በተነሳ ጊዜ የቱርክ ህዝብ በአደባባይ ወጥቶ በታንኮች ስር ነበር የተኛው። ወታደሩ አልተኮሰም፣ አልገደለም። እንዲያውም መሳሪያውን ለህዝብ እያስረከበ በሰላም እጁን ሰጥቶ ነው ወደ ወኅኒ ቤት የገባው። ምክንያቱም ህዝብ ክቡር ነው። ዜጋ ክቡር ነው። በኢትዮጵያ ግን የተገላቢጦሽ ነው። ሀገር የሚመሩት ነፃ አውጪ ግንባሮች ናቸው። የሚገርመው ትግራይን ነፃ አወጣለሁ የሚለው ህውሓት ወታደሩን የሚያደራጀው በኢትዮጵያ ህዝብ ግብርና ታክስ በሚመደብለት በጀት መሆኑ ነው። ይጋጠው አንጂ ታዲያ ሞኝ ህዝብ ሲያገኝ ምን ያድርግ?
አሁን የትግራዩ ህውሓት ከዐማራ ጋር የማይቀር ጦርነት ይኖረኛል በሚል መጠነ ሰፊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ይነገራል። ህውሓት መሳሪያውን የምትታጠቀው ራሱ ዐማራው ጭምር ለኢትዮጵያ ብሎ ከሚከፍለው ግብር ላይ ተቆርጦ በሚመደብለት በጀት ነው። ራሴን በራሴ ማለት እንግዲህ ይኸው ነው።
የጌዲኦ ህዝብ ባዶ እጁን ስለሆነ ተፈናቅሎ ጫካ እንዲጠለል ተገደደ፣ የዐማራ ገበሬ ከሱዳን ጦር ጋር በክላሽ ይተናነቃል፣ የሶማሌ ክልል 40 ሺ የራሱ የሆነ ልዩ ጦር አለው። ኦሮሞ የኦህዴድና የኦነግ ታጣቂዎች በጥምረት አሉት። የደቡብ ፖሊስ የማን እንደሆነ ራሱ አያውቅም። እናም ኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊቷ የተጠለፈ ነው። በፓርቲ ወታደሮች የተሞላ ነው። ይኸው ነው።
ፊንፊኔን ኬኛ፣ ጃዋር ሌንጨ ኬኛ፣ ኢትዮጵያ አውት ኦፍ ኦሮሚያ የሚለው የጃዋር አፍቃሪ ወታደር፣ የሚኒሊክ ሠፋሪ ብሎ ከፈረጀህ የኦሮሞ ወታደር ፊት ቆመህ ” #ኢትዮጵያ!  #ኢትዮጵያ ! ብትል ምንም ዋጋ እንደሌለህ ልታውቅ ይገባሃል።
በቡራዩ ያ ሁሉ ጭፍጨፋ ሲካሄድ የኦሮሚያ ፖሊስ ሳያውቅ ቀርቶ መስሎህ ከሆነ ተሳስተሃል። በደንብ ያውቃል። በደንብ። የክልሉ ፖሊስ ኃላፊ ለኢቲቪ በሰጡት መግለጫ ላይ ለምን ህዝቡን መታደግ አቃታችሁ?  ይኼ ሁሉ ጥፈት፣ ጭፍጨፋ ሲደርስ ለምን አልተከላከላችሁም ሲባሉ የሰጡትን መግለጫ ሰምታችኋል አይደል?  አዎ ” የመልክዓምድሩ አቀማመጥ ስላልተመቸን ለተጎጂዎች ልንደርስላቸው አልቻልንም ይልሃል። ወዲያው ግን በዚያው ዕለት የመከላከያ ሠራዊቱ በሶማሌ በአልሸባብ ላይ እርምጃ ወሰደ ይልልሃል። የቡራዩ ሜዳ ወንጀለኛ ለመከላከል አመቺ አይደለም። የሶማሊያ በረሃ ግን ወንጀለኛ ለመከላከል ይመቻል። ቀልደኞች።
በቡራዩ ህዝቡ ታረደ፣ ተጎዳ፣ ተፈናቀለ፣ ንብረቱም ወደመ። ፖሊስ ከጥቃት አድራሾቹ ጋር ህዝብ ሲቀጠቅጥ የሚያሳይ ቪድዮም ተለቋል። ፖሊስ አብሮ ከተቃዋሚዎች ጋር ድንጋይ ሲወረውርም ታይቷል። ከወንጀል ፈጻሚዎቹ አንዳቸውም ጉዳት አልደረሰባቸውም። አንዳቸውም። አሁን ለጊዜው ይያዛሉ። መስከረም ላይ ኦቦ ለማ መገርሳ በይቅርታ ይፈቷቸዋል። ይኸው ነው። ይኸው ነው ድራማው።
አሁን ያለው የኢትዮጵያ ሠራዊት የፓርቲ፣ የድርጅቶች ዘበኛ ነው። ህውሓትና ኦነግ ኦህዴድም የሚያዙት ጦር ነው። ብአዴን በድን ናት። ለብአዴን ከክልሏ ፖሊስ ይልቅ የገበሬ ጦሯ የተሻለ ወገናዊ ነው። የብአዴን ፖሊስ በህውሓት እየታዘዘ መግለጫና እርምጃ በገዛ ህዝቡ ላይ የሚወስድ ነፈዝ ነው። እሱን እርሱት።
የሚገርመው አቶ ዘይኑ ጀማል የደኅንነት ኃላፊ የነበሩት የአቶ ጌታቸው አገልጋይ የነበረ ሰው ነው ይባላል። አሁንም መመሪያ የሚቀበለው ከመቐለ ነው የሚሉ አሉ። አቶ ዘይኑ ትናንት በአዲስ አበባ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ዜጎችን ከገደሉ በኋላ ” በአደገኛ ቦዘኔዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ተወስዷል ነው ያሉት”
ይኼን ሟቹ ጠቅላይ አቶ መለስ ዜናዊ ይጠቀሙበት የነበረን ቀፋፊ ቃል ከስንት ዓመት በኋላ አቶ ዘይኑና ሃጂ ጀዋር በድፍረት በአዲስ አበባ ህዝብ ላይ ሲጠቀሙት ታይተዋል። የእኔ ጥያቄ መቼ ነው ኢትዮጵያ እንደሀገር የራሷ የጦር ሠራዊት የሚኖራት ?  መቼ ነው ለህዝብ የወገነ ሠራዊት የሚኖረን ?  መቼ ነው ባዶ እጁን ለተቃውሞ የወጣን ህዝብ ለፓርቲያቸው በወጡ ወታደሮች መገደሉ የሚያቆምልን? ይሄ የእኔ የዘወትር ጥያቄ ነው።
ማስታወሻ | ~ ሐጂ ጃዋር ዜግነቱ አሜሪካዊ ነው ይባላል። አሜሪካዊ ዜጋ ይህን ያህል በኢትዮጵያ ዜጎች ላይ ንጉሥ መሆን ይችላል ወይ። መመሪያ መሥጠት፣ ጠቅላይ ሚንስትሩን መናቅ፣ ማጣጣል፣ ይችላል ወይ? የአሜሪካ ህ ሕገ መንግሥትስ አንድ ዜጋዋ ” በሜንጫ ነው አንገቱን የምንቆርጠው የሚል ዜጋዋን እንዴት ነው የምትመለከተው? እንዲያው ለጥያቄ ያህል ነው።
ሻሎም !  ሰላም !
Filed in: Amharic