>
5:13 pm - Thursday April 20, 7139

ከውዝግቡ በስተጀርባ!!! (አበበ ገላው)

ከውዝግቡ በስተጀርባ!!!
አበበ ገላው
ኢትዮጵያ ነጻነትነቷን አስጠብቃ፣ የውጭ ወራሪዎችን መክታ እንደ አገር ኮርታና ተከብራ ለዘመናት የኖረችው በህዝቧ አንድነት ነው። ምንም አንኳን የኢትዮጵያ ነገስታትና ገዢዎች ጨቋኞች የነበሩ ቢሆንም ህዝቡ አንዱ በሌላው ላይ ክፋት ኖሮት አያውቅም፣ አንድነቱም ላይ ጥያቄ አንስቶ አያውቅም ነበር።
ህወሃት የኢትዮጵያን ህዝብ ካልከፋፈለ ቀጥቅጦ መግዛትና መዝረፍ እንደማይችል በመገንዘቡ የዘር ፖለቲካን በህገ መንግስት ደንግጎ፣ በዘር ላይ የተመሰረቱ ክልሎችን አዋቅሮ ዘረኝነትን መዋቅርና ቅርጽ ሰጥቶ ለእያንዳንዱ ብሄረሰብ ነጻ አውጭ ግንባርና ንቅናቄ አደራጅቶ ኢትዮጵያውያንን እርስ በርስ እንደ አንድ አገር ዜጋ ተማምነው እንዳይኖሩ አደረገ። በአለለፉት 27 አመታት ሌላው እርስ በርሱ ሲናቆር የህወሃት መሪዎች መጠነ ሰፊ ዘረፋ በአገሪቷ ላይ ፈጸሙ። አፋኝ እና ዘራፊ ስር አታቸውን የተቃወመ ሁሉ የደረሰበትን ግድያ፣ አፈና እና ሰቆቃ ማንም ዘርዝሮ አይጨርሰውም። የህውሃቶች ግፍ ዋነኛ ሰለባ የሆኑትም የ አማራና የኦሮሞ ተወላጆች መሆናቸው ያደባባይ ሚስጢር ነው።
ከኦነጉ መሪ ዳውድ ኢብሳ የአቀባበበል ዝግጅት ጋር ተያይዞ የተከሰተው የባንዲራ ጭቅጭቅ ዋና ችግር ህዝብ ለመተማመን መቸገሩ ነው። በኢትዮጵያችን የዘር ፖለቲካ እጅግ ጦዟል። ከጡዘቱም ያተረፉና እያተረፉ ያሉ የፖለቲካ ነጋዴዎች በየቦታውና በየጎራው አሉ። ለእነዚህ ነጋዴዎች በከንቱ የሰው ደም መፍሰሱ ብዙም አያሳስባቸውም።
ህወሃቶችም በበኩላቸው ያጡትን የበላይነት ለማስመለስ አሁንም የዘር ፖለቲካን ማጦዝና ግርግር መፍጠርን እስትራቴጂ አድርገውታል። ከባንዲራ ውዝግብ በስተጀርባ ያለው የዘር ፖለቲካ ጡዘት መሆኑን በመገንዘብ የተፈጠሩትን ውዝግቦች ማርገብ እጅግ አስፈላጊ ነው። ከዚህ ግርግር በዋናነት የሚያተርፉት እሳት እያቀጣጠሉ ያሉት የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪካዊ ጠላቶች ናቸው።
በእኩዮች የተዘራው የዘር እንክርዳድ በጥንቃቄ ካልታረመ ውጤቱ ዛሬ ከምናየው ችግር የከፋ የኢትዮጵያን ህልውና የበለጠ አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል መረዳት ያስፈልጋል።
ለኦነግ ያለኝን ክብር ስገልፅ በደስታ ነው!
አብርሀ ደስታ
ነገ በዛላምበሳ በኩል ለሚገባው የኦነግ ወታደር – በዓዲግራት  የቁርስ፣ በመቀለ ደግሞ የምሳ ግብዣ እንደሚደረግለት የትግራይ ክልል መንግስት ኮምኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡
የአዲስ ዓመቱ ምርጥ ግብዣ! ለዚህ ምርጥ ተግባሩ የትግራይ ክልል መንግስት ምስጋና ይገባዋል።
****** 
አሸባሪ እያሉ ስንቱን የኦሮሞን ልጅ የገረፉና የገደሉ ህወሃቶች ዛሬ ለኦነግ ድግስ እየደገሱ ነው። የሴራ ፖለቲካ የተንኮል ድግስ….
Filed in: Amharic