>
5:13 pm - Friday April 18, 9603

ውለታ የምትበላ ሀገር እንዳንሆን!!! (ዐቢይ ሠለሞን)

 ውለታ የምትበላ ሀገር እንዳንሆን!!!

ዐቢይ ሠለሞን

ይቺ ውለታ የምትበላ ሀገር በበላይ ዘለቀ አልበቃ ብሏት እምየ ሚኒሊክ የሰራልንን የማይሻር ዘላለማዊ ውለታ ከ ዋለላቸው የሀገሩ ልጆች ውለታው እንዴት እየተበላ እንዳለ ዛሬ በ አዲስ አበባ አይተናል::

የሰጠን የነፀነት አየር በተቃራኒው የሚከረፋ የሲጋራ ጭስ ሆኖብን
ነፃነት ሊሰጠን ጦር የሠበቀበትን እጁን ካልቆረጥን ብለን የታሪክ አተላ ለመሆን እሩጫ ላይ እንገኛለን::

እነዚህ ትላልቅ የአለማችን ሠዎች የሠጡትን ምስክርነት እንመልከት

የቀድሞው የአሜሪካ ፕረዘዳንት ጆንኦፍ ኬኔዲ

” በምድር ላይ ጀግና ጥራ ብትሉኝ ቀድሜ ምጠራው የንጉስ ሚኒሊክን ነው ደርባባና ደፋር ናቸው። የነጭ ቅኝ ገዥን በአፍሪካ ምድር ያንበረከኩ ቆራጥ ሰው። ኢትዮጵያውያን ጀግንነታቸው የመነጨው ከሌላ ሚስጥር አይደለም ከሚኒሊክ ነው። ለዚህም አገሬ አሜሪካ በክብር እዚህ ድረስ ታሪካቸውን በሙዚየም  አስቀምጣለች”

የፈረንሳዊ የቀድሞው መሪ ዣክ ሽራክ “የት አለ ጀግና ለዛውም በአፍሪካ ምድር ከንጉስ
ሚኒሊክ በላይ “ በማለት ዘክረዋቸው ነበር።

የሊቢያው መሪ ጋዳፊ ከመኖሪያ ሰገነታቸው ባንዱ ክፍል የንጉስ ሚኒሊክ ፎቶ ነበር ከስሩም
” ታላቁ ሰው “ ይላል።

የ ዐፄ ሚኒሊክ ሀውልት ባለመብት እኛ የኢትዮጵያውያን ብቻ እንዳልሆነ መረዳት አለብን ይህ ሀውልት የመላው የጥቁር ህዝብ የ አሸናፊነት ምልክት መሆኑ መረሳት የለበትም::

በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ፣ የትምህርትና ባህል ማዕከል /UNESCO/  ላይ እንዳይመዘገብ ህወሀት/TPLF/ እንዳደረገም በግልፅ የምናውቀው ነው::

እናም የዚህን የጥቁር ህዝብ የድል ምልክት እንታደገው::ውለታ የምትበላ ሀገር እንዳንሆን!!

Filed in: Amharic