>

ብአዴንም ኦህዴድም ስማቸውን ሊቀይሩ ነው፤ ህወሀት "ይህ የሚደረገው በመቃብሬ ላይ ነው" እያለ ነው!!!

ብአዴንም ኦህዴድም ስማቸውን ሊቀይሩ ነው፤ ህወሀት “ይህ የሚደረገው በመቃብሬ ላይ ነው” እያለ ነው!!! TFI
ብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) በ12ኛ ድርጅታዊ ጉባኤው ስሙንና አርማውን ለመቀየር ውይይት ሊያደርግ ነው። ለውይይት ከሚቀርቡት ስያሜዎች መሃል
1. የአማራ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አህዴፓ)
2. የአማራ ክልል ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ አንድነት ፓርቲ (አህዴአፓ)
3. የአማራ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (አህዴድ)
4. የአማራ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አህዴን)
እና ሌሎችም እንደሚገኙበት የ TFI ምንጮች ነግረውናል። ብአዴን የሚለው ስያሜ በህወሃት የተሰጣችሁ ነው በሚል በአማራ አክቲቪስቶች ክፉኛ ይጠላል። “አ” በ “ዐ” መተካት አለበት የሚሉም አሉ።
በተመሳሳይ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ስሙን እና የድርጅቱን መለያ (ሎጎ) ልቀይር ነው ተብሏል። የኦህዴድ አዲሱ ስም የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ሲሆን ሎጎውም ሊቀር ነው::
ህወሃቶች በተቃራኒው ስም ለመቀየር በሚደረገው ጥድፊያ ደስተኛ አይደሉም። በደኢህዴን ውስጥም ደቡብ አቅጣጫ ነው እንጂ ብሄር አይደለም የሚል የተለያዩ ብሄረሰቦች ጥያቄ ላይ ውይይት ቢደረግም  በምን ይተካ የሚለው ጉዳይ ከባድ አለመስማማት ፈጥሯል።
ከጥቂት ወራት በፊት በኢህአዴግ ፅ/ቤት ትዕዛዝ በአቶ ተፈራ ደርበው የሚመራ ቡድን ኢህአዴግ አንድ ወጥ ሀገራዊ ፓርቲ ውህደት ማድረግ አለበት ወይስ የለበትም የሚል ጥናት በማድረግ ላይ ነበር። ነገር ግን ከህወሃት ጋር ያለው የቃላት ጦርነትና የideological divergence እየከረረ በመምጣቱ ውህደቱን ጥያቄ ውስጥ ከቶታል።
ህወሃት በተደጋጋሚ አብዮታዊ ዴሞክራሲ (አዴ) የሚቀየረው በመቃብሬ ላይ ነው በማለት ላይ ስትሆን ብአዴን በተቃራኒው “አ.ዴ” ከጊዜው እና ከህዝቡ ንቃተ ህሊና ጋር  የሚጣጣም ርዕዮተ ዓለም አይደለም ብሎ ወስኗል። ስለዚህ የብአዴን ጉባኤ “አዴ” ይተካ አይተካ ሳይሆን ባብዛኛው የሚወያየው በምን ይተካ የሚለው ላይ  እንደሚሆን ይጠበቃል። ብአዴኖችና ኦህዴዶች revolutionary democracy is past its sell by date ብለዋል።
በሌላ በኩል ህወሃት ውስጥ በተወሰኑ ሰዎች ደብረጺዮንን በአለም ገብረዋህድ ለመተካት እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሆነ ምንጮች ነግረውናል። በተጨማሪም በሚቀጥለው ጉባኤ እስክ ስድስት የሚደርሱ ወጣት አመራሮች ወደ ማእከላዊ ኮሚቴው ለማምጣት እቅድ ይዘዋል። አላማውም በመስከረም መጨረሻ ላይ የሚደረገው የኢህአዴግ ኮንግረስ ላይ በተሻለ ጥንካሬ ለመውጣት ነው።
መቀሌ ላይ በተደረገው የመለስ ዜናዊ መታሰቢያ ስብሰባ ላይ ተሳታፊዎች ደብረጺዮንን “አንተ የኛ ፑቲን ነህ ጭንቅላትህም የፑቲንን ሃያ እጥፍ ነው” ብለውት የነበረ ቢሆንም የፓርቲው አመራሮች ግን የብቃት ጥያቄ አንስተውበታል። በተለይም የኢህአዴግ councilና ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባዎች ውስጥ እንደ ህወሃት ሊቀመንበርነቱ ጉዳዮችን የመተንተንና ተናግሮ የማሳመን አቅሙ አናሳ ነው በሚል ይተቻል።
ወደ ብአዴን ጉባኤ ስንመለስ ከስያሜና አርማ ለውጥ ሌላ የድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብና ኘሮግራም ላይ ማሻሻያ ያደርጋል። ምንጮች እንደነገሩን መሻሻል ያለባቸውን አንቀፆች አጥንተው እንዲያቀርቡ ላቀ አያሌው፤ ፀጋ አረጋ እና ፈንታው ጥበቡ ሃላፊነት ተሰቷቸዋል። በጉባኤው እስከ 1600 ተሳታፊ ይገኛል ተብሎ ሲጠበቅ ከዚህ ውስጥ ድምጽ የሚሰጡት 1250 አካባቢ ብቻ ናቸው። ተጨማሪ ከ 450-500 ተጋባዥ የዩኒቨሲቲ አመራሮች፣ባለሀብቶች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ አርቲስቶች እና የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ ተማሪዎች እንደሚጋበዙ ሰምተናል።
Filed in: Amharic