>
5:13 pm - Friday April 19, 1912

የበረከት ተስፈኞች ትንሳኤ የሌለው የፖለቲካ ሞት መሞቱን አውቃችሁ እርማችሁን አውጡ !!! (ቬሮኒካ መላኩ)

የበረከት ተስፈኞች ትንሳኤ የሌለው የፖለቲካ ሞት መሞቱን አውቃችሁ እርማችሁን አውጡ !!!
ቬሮኒካ መላኩ
በረከት ስምኦን በፌደራል ደረጃ ያለውን ከፍተኛ ስልጣን ሲለቅ 32 ሁለት ጥርሱን እያሳዬ በደስታ ነበር የተቀበለው ። በረከት ከፓርቲው ስልጣኑ ሲወገድ ግን  በከፍተኛ ድንጋጤ  እያጓራ ነው፡፡ በፍፁም ይሄን እንደ መብረቅ የሚያስደነግጥ እርምጃ አልጠበቀውም ነበር ።  የደም-ግፊቱ እስኪነሳበት ድረስ አንዘፍዛፊ ብስጭት እያናወዘው ነው። የብአዴን ውሳኔ የበረከትን የህይወት ዘመን ህልም በአጭሩ የቀጨ ነው።
ለመሆኑ በረከት ከፓርቲው መወገዱ ለምን ሊቋቋመው የማይችለው ህመም ሆነበት ?  
 የበረከት የዚህ አለም የፖለቲካ ህይወት አላማና ግቡ አማራን መጉዳት ነው።  ለበረከት ስምኦን ስኬታማነት የሚለካው በአማራ ህዝብ የጉዳት መጠን ነው። በፌደራል ደረጃ እያለ አማራን እሱ በፈለገው መጠን መጉዳት ስለማይችል ከፌደራል ስልጣኑ ሲለቅ ምንም ቅር አላለውም ።
በረከት በፓርቲው ባለው ስልጣን እንደ ሸረሪት ድር በዘረጋው የተወሳሰበ ኔትወርክ አማካኝነት አማራን የመጉዳት አቅሙ ግን ከፍተኛ ነበር ።አሁን በረከት በብስጭት የሚንዘፈዘፈው በፓርቲው ውስጥ እስከመጨረሻ ቁጭ ብሎ አማራን  የመጉዳት ህልሙ ስለተጨናገፈበት ነው።
ብአዴንን በማንቃትና  የሰሞኑን ቆራጥ ውሳኔ በተመለከተ ጎንደርና ባህርዳር የነፃነት ችቦ ፈር-ቀዳጅ ሲሆኑ  ደብረማርቆስ ላይ  ደሞ የመጨረሻው የብአዴን ምሽግ በባዙቃ የተደረመሰበት ቦታ ነው።
ምስጋና  ለደብረማርቆስ ወጣቶች ይሁንና  ዛሬ በረከት ስምኦን  በመቀሌና በአዲስ አበባ መካከል በሰማይ ላይ በፕሌን  ብቻ የሚንቀሳቀስ  ግኡዝ እንጅ በየብስ ላይ  እንቅስቃሴው የተገደበ ጎንደርና ባህርዳር ከተሞች  የሚናፍቁት ግን የማያገኛቸው የቁም እስረኛ ሆኗል። የደብረማርቆስ ብርቱ ክንድ ብርቱ  ብአዴን እንድወጣና ብአዴን ይሄን እርምጃ እንድወስድ  መሠረት ጥሏል።
አሁን እኔን እያበሳጩኝ ያሉት በአማራ ማስ ሚዲያ ያሉ ለበረከት ስምኦን የአየር ሰአት በመስጠት ሞገዱን እንድበከል እያደረጉ ያሉ ሰዎች ናቸው።  እነዚህ የአማራ ሚዲያ ሰዎች በረከትን በአማራ ሚዲያ እያቀረቡ በብአዴን ውስጥ ያለውንነ  መፈረካከስ የጀመረውን ኔትወርኩን ኮማ ውስጥ ከገባቡትና ለመሞት ከሚያጣጥሩበት ኦክስጅን በመቀጠል ቀና ቀና እንድሉ እድል እየሰጧቸው ነው። ይሄ በፍፁም ተቀባይነት የለውም።
ማንም ሰው ሀሳቡን የመግለፅ መብት እንዳለው አምናለሁ ። በረከት በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት አማራ የሚረገጠው መሬት ፣ የሚተነፍስበት ሚዲያና የሚፅፍበት ጋዜጣ ሁሉ አልነበረውም ።
ዛሬ ያን ግፍ የፈፀመ አውሬ በአማራ መሬትና አየር ላይ የሚተነፍስበት ሚዲያና የሚረገጠው መሬት ሊኖር አይገባም።
በብአዴን ውስጥ ያላችሁ  የበረከት ተስፈኞች ተስፋችሁን ቁረጡ ። በረከት ስምኦን ከዚህ በኋላ ትንሳኤ የሌለው የፖለቲካ ሞት መሞቱን አውቃችሁ እርማችሁን እንድታወጡ እመክራችኋሁኝ።
Filed in: Amharic