>

የዶ/ር አብይ መንግስት ከቲ.ፒ.ዲ.ኤም ጋር የተፈራረመው የሰላም ስምምነት ለህወሀት የመጨረሻው ካርድ ይሆናል!!! (ታደለ አሰፋ)

የዶ/ር አብይ መንግስት ከቲ.ፒ.ዲ.ኤም ጋር የተፈራረመው የሰላም ስምምነት ለህወሀት የመጨረሻው ካርድ ይሆናል!!!
ታደለ አሰፋ
 በዛሬው ቀን  በጄኔራል አደም አህመድ የደህንነት ሀላፊው ኢትዮጵያን ወክሎ የTPDM መሬ መኮንን ተስፋዬ ጋር  የሰላም ስምምነት አስመራ ፈርመዋል ።
ተመሳሳይ ፊርማ ከOLF አስመራ ሲፈረም ከጥቂት ሳምንት በፊት በኢትዮጵያ በኩል ለማ መገርሳና ወርቅነህ ገበየሁ ተገኝተው ነበር ።
የትግራይ ክልል በዛሬው ስብሰባ አለመገኘቱ የተጠበቀ ቢሆንም በቅርቡ ክልሉ የሰላም ጥሪ በይፋ ለTPDM ማቅረቡ ይታወቃል ።
ምናልባት በክልሌ ጉዳይ ፌዴራል መንግስት ጣልቃ ገባ ብሎ  ህወሓት ይከስ ይሆን?? ከኤርትራ ጋር ያለው ማናቸውም ግንኙነት የትግራይ ክልል ካለፌዴራል ጣልቃ ገብነት ለመወሰን በሁለቱ ህዝቦች መሀከል ሌላው አያገባውም ለሚለው የህወሓት የዐቢይን መንግሥት ትንኮሳ  በሶማሌ ክልል አብዲ ኢሌን መንካት ህገ መንግሥት መጣስ ነው እንደተባለው ።
በመሳሪያ ና ወታደራዊ ዝግጅት የሚታወቀው TPDM ምናልባት የዐቢይ የመጨረሻ ካርድ ሊሆን ይችላል። ህወሓት የጀመረውን የመቀሌውን ስብሰባ ነባር መሪዎቹን ብአዴን እንዳሰናበተው እንዲሸኝ በጡረታ ቢቻል በሹመት ስም ያልተሸነፉ ለማስመሰ ል።
 የቀድሞው TPDM መሪ ሞላአስገዶም እንደከዳው ከድተው ወደ ህወሓት የሚመጡ ቢኖሩ አያስገርምም።
በመሠረቱ TPDM እና ህወሓት የዛሬ 27አመት በፈጠሩት ካርታ ላይ ልዩነት የላቸውም ።
እነ አረጋዊ በርሄ ና ሌሎች በቅርቡ የተመለሱት ህወሓትን ተቃዋሚ ነን የሚሉት በሙሉ ከጎንደርና ወሎ ቀምተው በብዙመቶ ሺህ የትግራይ ተወላጆችን ያሰፈሩትበትን ህገወጥ የመሬት ወረራ እንደ ችግር አይቀበሉትም ለወንጀላቸው “ሁሉምየኢትዮጵያ መሬት ነው” የሚል ሽፋን ያበጁለታል እንጂ።
የጎሳ ፌዴሬሽን እና አንቀፅ 39 እያለ ሁሉም ኢትዮጵያ ነው የሚለውን ህወሓት እንደማይቀበለ ው ግልፅ ቢሆንም እነርሱን እስከጠቀመ ድረስ ይዘውት ይጓዛሉ።
ይህንንም በረክት ስምኦን በሰጠው ቃለመጠይቅ ምናልባት ከመቀሌ ትላንት ግልፅ አድርጓል ።
“….መጪው ጦርነት ኢትዮጵያን የሚያፈርስ ምንጩ የአማራ ክልል አዲሱ አስተዳደር ነው….” ብለዋል ምክንያቱም በወያኔ አሽከርነቱ የሰጠዉን መሬት  ለትግራይ ና  ሱዳን ለማስመለስ ህዝቡ ጥያቄውን ስለማያቆም ነው።
በረከት ለመጭው ግጭትም ኤርትራ እጆች እንዳሉበት ጠቁመዋል ።ለበረከት ጥያቄ ዛሬ  ከፊል መልስ TPDM ሰጥትዋል። መልሱ ግን የሰላም ፊርማ ነበር ።
TPDM ከ አማራ ክልል ጋር በአስመራ ተነጋግሮ በረከት ና ህወሓት የተመኙት ደም መፋሰስ እንዳይመጣ ሁኔታዎች ከወያኔ በፊት የነበረው ተከዜ ወንዝ የትግራይ ጎንደር  ድንበር መሆኑን መስማማት ያስፈልጋል ።
የሰፈሩት የትግራይ ተወላጆች የመኖር መብታቸው በኢትዮጵያ ዜግነት  ሊረጋገጥ ይገባል ።
Filed in: Amharic