>

የፕሬዚዳንት  ኢሳያስ ምክር ለአዲሱ የለውጥ ሀይል!!! (የሺሀሳብ አበራ)

የፕሬዚዳንት  ኢሳያስ ምክር ለአዲሱ የለውጥ ሀይል!!!
የሺሀሳብ አበራ
ፕሬዜዳንት  ኢሳያስ አፈወርቂ ” ያረጁ የትህነግ አመራሮችን እና እነ በረከት መሰሎችን ከኢትዮጵያ  ፖለቲካ ካልተገለሉ ኢትዮጵያ ሰላም አትሆንም”” እንዳሉ አቶ በረከት ተናግረዋል፡፡
 …
አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝም” ህዋኃቶች ናቸው በሃገሪቱ ላይ ሰላም እንዲርቅ የሚያደርጉ” ብለው ለኢሳያስ እንደተናገሩ አቶ በረከት ሰው ነግሮኛል ብለው  መስክረዋል፡፡
 …
አቶ ኢሳያስ ለኢትዮጵያ  መንግስት እንዲህ አይነት ምክር የሚመክሩ ከሆነ የኢትዮጵያ  ፖለቲካን ከኢህአዴግ  በላይ ገብቷቸዋል ማለት ነው፡፡  ሁሌም ይምከሩልን አቶ ኢሳያስ እንል ዘንድ እንገደዳለን፡፡
..
አቶ ኢሳያስ ከትህነግ ጋር በፍፁም እንደማይደራደሩ ፣ግንኙነታቸውን ከተቀረው የኢትዮጵያ  ክፍል ጋር እንደሚያደርጉ ተሰምቷል፡፡ትህነግ አሳድጌ ከድቶኛል ብለው ይሆናል፡፡አቶ በረከት ለመባረራቸው  ኢሳያስን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡ የአሁኑ ብአዴንም ኢትዮጵያን ያፈርሳል ብለዋል፡፡በአማራ ክልልም በደቦ ፍርድ እየተናጠ  ሰላም የለም ብለዋል፡፡
 የብአዴኑ አቶ ምግባሩ ከበደ ደግሞ” አዲሱ  ብአዴን ያመጣው  ለውጥ አቶ በረከት በነፃነት  እንዲተቹ አስችሏቸዋል፡፡አቶ በረከት ጥረትን በመምራት ስንፈትና ዘረፋ ተጠያቂ ናቸው፡፡የፖለቲካ ውሳኔ ተላልፏል፡፡፡ቀጣይ በህግ አግባብ ይጠየቃሉ” ብለዋል፡፡
 ..
አቶ በረከትን ቀድም  ያባረራቸው  የአማራ ወጣት እንጂ  ብአዴን ወይም ኢሳያስ አይደሉም፡፡ ከወሎ እስከ ጎንደር፣ ከጎጃም እስከ ሸዋ አቶ በረከት ታዮ በተባሉበት ሁሉ ወጣቱ ሲያሳድዳቸው ኑሯል፡፡ ምክንያቱም ህዝብ ጠልቷቸዋል፡፡ ለምን?
በ27 ዓመቱ ዘረፋ እና ግድያ አቶ በረከት አንዱ እንደሆኑ ተነግሯል፡፡ አቶ መላኩ ፈንታ ብቻ ለአቶ በረከት ጨካኝነት አንዱ ምስክር ነው፡፡ አቶ መላኩን  አቶ በረከት ከባለቤቴ ካሜራ ታክስ ቆረጥሃል ብለው እስር ቤት አስገብተውታል፡፡ አቶ በረከት የአቶ መላኩን ቃለመጠይቅ  በሪፖርተር ጋዜጣ ቢያነቡ ራሳቸውን የሚጠሉት ይመስለኛል፡፡
 …
አሁንም ብዙ አቶ በረከቶች ብአዴን ከስልጣን ያንሳ፡፡ መነሳታቸውን የሚጠረጥሩ አቶ በረከቶች በህዝብ ላይ ጥርጣሬ በመዝራት የአማራን ብሎም የኢትዮጵያን  ህዝብ ወደ ልዮነት በመክተት፣ለልዮነቱ አስታራቂ ሆነው ለመምጣት ቀጣይ መጣራቸው አይቀርም፡፡
ተደራጅቶ እና ተናቦ ወቅቱን የማይነቃነቅ የተቋም እና የስራዓት መሰረት የሚገነባበት ካልሆነ ለውጥ ይመክናል፡፡አዲስ አብዮት ለአዲስ ችግር እና ውድቀት ይጋብዛል፡፡ እንደ 1966 ቱ ወይም 1983 የባከነ አብዮት ሆኖ ብዙዎች ሙተው ያመጡት ነጥብ የምታህል የለውጥ ጅማሬ ካለፈ፣ ሌላ የቅኝ ግዛት ዘመን መንሰራፋቱ አይቀሬ ይሆናል፡፡ የብአዴን የለውጥ ሃሳብ መደገፍም ታክቲካልም ስትራቴጂካልም  አዋጭ ነው፡፡ብአዴን በሙሉ ልቡ ከተለወጠ የታመመው  የኢትዮጵያ  ፖለቲካ ይድናል፡፡አማራነትም ይደረጃል፡፡
 …
 ብአዴን በእነ  አቶ በረከት የጠፋውን ጥፋት ዝርዝር  ሰንዶ የህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡አቶ በረከትም  ተቃውሟቸውን መቀሌ ሆነው ባህርዳር ላለው የብአዴን  ማዕከላዊ ኮሚቴ አስገብተዋል፡፡
Filed in: Amharic