>
5:13 pm - Friday April 19, 3135

ለአብዲ ኢሌ የተገለጠ የህግ መፅሀፍ ለወንጀለኛው በረከትም ይገለጥ!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

ለአብዲ ኢሌ የተገለጠ የህግ መፅሀፍ ለወንጀለኛው በረከትም ይገለጥ!!!
ቬሮኒካ መላኩ
ደራሲ ከበደ ሚካኤል ተረትና ምሳሌ በሚለው መፅሀፋቸው ላይ ” አውራ ዶሮ ሌሊቱ የሚነጋው የእሱን ድምፅ ሰምቶ እየመሰለው ሲኮፈስ ይኖራል ።” የምትል ድንቅ አባባል ፅፈዋል።
ይች የአውራ ዶሮ ምሳሌ በረከት ስምኦንን በደንብ ትገልፀዋለች።  የኢህአፓው አንበርብር የብአዴኑ በረከት ስምኦን “እኔ የሌለሁበት ብአዴን የአገር አደጋ ነው ። ” እያለ ባገኘው ሚዲያ ሁሉ እየለፈለፈ ነው።
አቶ በረከት ከፍተኛ የሆነ የአእምሮ ድባቴ (Depression) በሽታ እንዳለበትና በየጊዜው ውጭ እየሄደ እንደሚታከም ድፍን ኢትዮጵያ ያቦካው የተረጋገጠ ሃቅ ነው።  ነገር ግን በረከት ስምኦን ፈረንጆቹ ” Megalomaniac” እያሉ የሚጠሩት ራስን በድለላ የማተለቅ በሽታ ያለበት አይመስለኝም ነበር ። ከሰሞኑ የሚዲያ ልፍለፋው በረከት የዚህ በሽታ ተጠቂ እንደሆነ አረጋገጥኩኝ።
በረከት ስምኦን የመጨረሻው ምሽግ ወደሆነው መቀሌ ካምፕ ውስጥ መሽጎ  ፍሬቻ ሳያበራ በአደገኛው ታጥፎ ፍሬን የሌለው የፕሮፓጋንዳ መኪናውን በአማራ ህዝብ እየረጨ ይገኛል ። ይባስ ብሎ የአማራ ህዝብን ለ27 አመታት የጎዳው ሳይበቃው ዛሬም ክልሉን “ኢትዮጵያን የሚያፈርስ ” በማለት እየከሰሰ ይገኛል።
ይሄ ሰው በአስቸኳይ  አደብ እንድገዛ መደረግ አለበት ። ካለበለዚያ የሚያመጣው መፃኢ የፕሮፓጋንዳ ጥፋት የከፋ ይሆናል።
ተክለፃድቅ መኩሪያ  በፃፉት ዳጎስ ባለው መፅሀፋቸው ” የኢትዮጵያ ገናና ንጉሶች ከነበሩት አንዱ የነበረው አፄ አምደፂዮን አንድ ከፍተኛ ባለስልጣናቸው በወሬ እና ባልተጨበጠ ፕሮፓጋንዳ ህዝብን እርስ በርስ ሲያባላና አገር ሊያፈርስ ሲሞክር ቢመከር ቢዘከር ስላልሰማ  በመጨረሻ አምደፂዮን የዛን ባለስልጣን የምላስ ጫፍ በፍርድ እንድቀነጠብ ተወስኖ የምላሱ ጫፏ ከተቀነጠበች በኋላ በአገሩ ሰላም ሰፈነ  ” በማለት ፅፈዋል።
በረከት ስምኦንም በአማራ ህዝብ ላይ የሚነዛውን ፕሮፓጋንዳ ካላቆመ መንግስት በሰራው ወንጀል ልክ በአስቸኳይ ሊጠይቀው ይገባል።
ከወደቁ በኋላ መንፈራገጥ ለመላላጥ እንደሚባለው አሁን በረከት የመጨረሻው አጭበርባሪ ሰው ሆኖ እያለ  ሌላውን አጭበርባሪ ብሎ  አ የዘለፈ ነው ፡፡ የመጨረሻው ቀጣፊ ሰውዬ ሌሎችን ቀጣፊ ብሎ ይሰድባል፡፡ የመጨረሻው የህግ እና የፍትኅ ጠላት የሆነ ሰው ምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን  በህገ ወጥነት ይወነጅላል፡፡ የመጨረሻው ሕገ-መንግሥትን ሲደረምስ የኖረ ሰውዬ፣ ደርሶ የሕገ-መንግስት ጠበቃ ነኝ ይላል፡፡
በደመቀ መኮንን ላይ እየሰነዘረ ያለው ትችት ደመቀ መኮንን ገና ድሮ የአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ የነበረ መሆኑን ፍንጭ የሚሰጥ ብቻ ሳይሆን ያረጋገጠና  የአማራ ህዝብ ደመቀን የበለጠ እንድያከብረውና እንድጠብቀው የሚያደርግ ማረጋገጫ መሆኑ ደስ ብሎኛል።
በመጨረሻ ጥቅሜ አደጋ ላይ ወድቋል  ብሎ የሚያስብ ሰው ጥቅሙን ለማስጠበት አቅሙ የፈቀደለትን አማራጭ ሁሉ ይወስዳል። የበረከት ስምኦን መፍጨርጨር የዚሁ ውጤት ምልክት ነው ። የህግ ዥንጉርጉር የለውምና ለአብዲ ኢሌ የተገለጠ የህገ መፅሀፍ ለወንጀለኛው በረከትም እንድገለጥ እንጠይቃለን።
Filed in: Amharic