>

የኢትዮጵያ አየር መንገድ - የውጭ አንበሳ: የውስጥ ሬሳ!!! (ሚኪ አምሀራ)

የኢትዮጵያ አየር መንገድ – የውጭ አንበሳ: የውስጥ ሬሳ!!!
ሚኪ አምሀራ
ይህ አየር መንገድ የኢትዮጵያዊያን ነው እንዴ እስከመባል የደረሰ የአንድ ብሄር የበላይነት የሚንፀባረቅበት አግላይና አታላይ ህውሃታዊ ድርጅት ነው:: ይህ ድርጅት በተለይ አማራ ክልል ላይ እየፈፀመ ያለው ግፍ እንዲህ በቀላሉ ተመልክቶ ማለፍ ማይቻልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው:: ማሳያዎችን እንመልከት:-
1. አማራ ክልል ውስጥ አራት የአየር ማረፊያዎች አሉ (ባ/ዳር, ጎንደር, ላሊበላና ደሴ/ኮምቦልቻ):: እነዚህ ማረፊያዎች እርስ በእርስ በአየር በረራ የተሳሰሩ ስለነበሩ የክልሉ ህዝብና ሌሎች ጎብኝዎችም በሚፈልጉት ሰዓትና ቦታ መንቀሳቀስ ይችሉ ነበር:: ነገር ግን በአየር መንገዱ ኃላፊ ያለምንም ገበያ ጥናት ከላሊበላ ወደ ባህርዳር ያለውን መደበኛ በረራ (schedule flight) በመሰረዝ ከላሊበላ መቀሌ እንዲሆን ተደረገ:: በዚህ ምክንያት ጎብኝዎችና ሌሎች ከላሊበላ ባህርዳር የሚመጡ ሰዎች እየተቸገሩ ነው::
2. የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሃገሪቱን የቱሪዝም ሃብት በአለም አቀፍ ደረጃ የማስተዋወቅና የማሳደግ ሃላፊነት በህግ ተሰጦታል:: በዚህም ምክኒያት በየአመቱ ከ 15 በላይ የትውውቅ ጉዞ (Familiarization Trip/ Fam Trip) ለታዋቂ ቱር ኦፕሬተሮች: ታዋቂ የሚዲያ አካላት, ዝነኛና ተጽኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ይዘጋጃል:: በዚህ 2010 ዓመት ከተደረጉ 14 አለም አቀፍ የትውውቅ ጉዞዎች ውስጥ 12 የሚሆኑት ወደ ትግራይ ሲደረጉ, 1 ወድ ደቡብና 1 ወደ ሃረር መሆኑን መረጃው ያሳያል:: የአማራና ሌሎች ክልሎች ኢትዮጵያ ውስጥ አይደሉም??
3. የኡትዮጵያ አየር መንገድም ሆነ ሌሎችን አየር መንገዶች በረራ ሊዘገይ ወይም ሊሰረዝ የሚችልበት አጋጣሚዎች ይኖራሉ:: ለምሳሌ መጥፎ የአየር ሁኔታ: በአሮፕላኑ የቴክኒክ ችግር: የሚበርበት አካባቢ የፀጽታ ሁኔታ: የማንገደኞች ቁጥር, ወዘተ:: ነገር ግን ወደ አማራ ክልል ለሚደረጉ በረራዎች ከሌላው በተለየ መልኩ የሚሰረዙትና የሚዘገዩት በምን ምክንያት ነው ብሎ መጠየቅ ጤነኝነት ነው::
4. የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር መንገዱ በተደጋጋሚ ለሚጠቀሙ ደንበኞች የተለያዮ ማበረታቻዎች ያደርጋል:: ከነዚህም ውስጥ ሸባሜይል (Shebamile) አባልነት አንዱ ነው:: በዚህም ምክንያት እያንዳንዱ የአየር መንገዱ ተጠቃሚ ወደ እሚፈልገው መዳረሻ በሚሄድበት ሁሉ እንደ መዳረሻው ርቀትና ቅርበት የማይል ማባረታቻ (bonus miles) ይበረከትለታል:: ነገር ግን በሃገር ውስጥ በረራ (domestic flight) ለአንድ ጉዞ (single trip) ሲሰጥ የነበረው 500 ማይል ወደ 50 ዝቅ እንዲል ተደረገ:: አየር መንገዱ በአፋሪካ ቀዳሚና ትርፋማ እየተባለ በሃገር ውስጥ ተሳፋሪዎች ላይ እንዲይ የዘቀጠ አሰራር መዘግጋቱ ምን የሚሉት ድንቁርና ነው??
አየር መንገዱ ኢትዮጵያዊ ይሁን!
cc// ANDM CC office ANRS Communication Affairs Office Nigussu Tilahun Agegnehu Teshager   ይሄን ድርጅት ግን አንድ አትሉትም
Filed in: Amharic