>

ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ ወደ እናት ሀገራቸው ሊገቡ ነው!!! (ዳንኤል ደምሴ)

ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ ወደ እናት ሀገራቸው ሊገቡ ነው!!!
ዳንኤል ደምሴ
የጎሬው ቡቃያ፣ የሐረር ወታደራዊ አካዳሚ ምሩቅ መኮንን ባለብሩህ አዕምሮ ባለቤት ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ ከ32 አመታት ስደት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ በዝግጅት ላይ ናቸው።
ዛሬ አቶ ስዩም መስፍን፣ ኃይለማርያም ደሳለኝና ወርቅነህ ገበየሁ የተባሉ መናኛዎች መንቦጫረቂያ ለሆነው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትክክለኛው የአክሊሉ ሀብተወልድ ምትክ ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ ነበሩ።
ይሁንና “ትክክለኛው ሰው በተሳሳተ ቦታ” የሆኑት ኮሎኔል ጎሹ በብልሹው የኮሎኔል መንግስቱ አስተዳደር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቦታ የነበራቸው ቆይታ አጭር ነበር። በዚህም ምክኒያት ሀገራችን ሳትጠቀምባቸው ካባከነቻቸው ወርቃማ ልጆቿ አንዱ ናቸው። ይህም ሆኖ ከ3 ከአመታት ባልዘለለው የውጭ ጉዳይ ቆይታቸው የብቃታቸውን ልክ የሚያሳዩ ስራዎችን ሰርተዋል።
በኢትዮጵያ ጉዳይ እየገባች ትፈተፍት ለነበረችው እንግሊዝ የስኮትላድን ጉዳይ አንስተው የሞገቱበት አጋጣሚ ነብይነታቸውን ያስመሰከሩበት ሁኗል። እኤአ በ1991 ለአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ያደረጉት ንግግርም የኮሎኔሉን የዕውቀት ልዕልና ጥግ ያሳየ ነበር(ዩቲዩብ ላይ ማየት ይቻላል)።
ዛሬ በህወሓት የዝንጀሮ ፖለቲካ ምክኒያት በጃርት ለተወረረችው ሀገራችን ኮሎኔል ጎሹና መሰል ሰዎች ፍቱን መድኃኒት ናቸውና የአብይ አስተዳደር ሳይውል ሳያድር በማካታት የለውጡን ሂደት በፅኑ መሰረት ላይ ሊያቆመው ይገባል።
Filed in: Amharic