>

በብአዴን ላይ ያለዉ ገደብ ያልተበጀለት የህዉሀት ተፅእኖ!!! (ሰልማን መሀመድ)

በብአዴን ላይ ያለዉ ገደብ ያልተበጀለት የህዉሀት ተፅእኖ!!!
ሰልማን መሀመድ
ብአዴን ስሙን ሊቀየር መሆኑን እየሰማን ነዉ ከቀናት በፊት ብአዴን ባደረገዉ ስብሰባ የአማራ ስራ አመራር ምክትል ሀላፊ የሆኑት አቶ Dessie Tilahun Ayalew <<ብአዴን ስሙን ሁሉ ሊቀይር ይገባል>> ሲሉ ተናግረዉ ነበር። ዛሬ ደግሞ አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው መታገዳቸዉን ሰማን ይህ በጣም ትልቅ የምስራች ነዉ።
ብአዴን ስሙን ብቻ ሳይሆን ግብሩንም (ስራዉን) መቀየር አለበት ስያሜ ብቻ መቀየር ፋይዳ የለዉም የአማራን ህዝብ ያቆሰለዉ ግብሩ ነዉ በተጨማሪም የአማራ ማንነት ይዘዉ የተቀመጡ ትግሬዎች ከቦታዉ ላይ መንቀል አለበት። እስከ አሁን ያለዉን የበሰበሰ ብአዴን አስተዳደር በእጅ አዙር የሚመራዉ ህዉሀት ነዉ ይህን አጀንዳዉን እንዲያስፈፅሙለት አማራነትን እንደሽፋን የሚጠቀሙ የትግሬ ማንነት ያላቸዉ ግለሰቦችን በድርጅቱ ከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ እንዲቀመጡ አድርጓል በመሆኑም ብአዴን እነዚህን ገለሰቦች ጠራርጎ ማስወገድ አለበት።
.
ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ብአዴን የአማራ ህዝብ ወኪል ነኝ ማለት አይቻልም በመሰረቱ ብአዴን በድርጅቱ ዉስጥ ያሉትን አማራ ያልሆኑ ግለሰቦች ሳይመነጥር አሁንም የአማራ ህዝብ ወኪል ነዉ ለማለት አያስደፍርም።
ከሁሉም የሚያሳፍረዉ እነዚህ የአማራ ማንነት የሌላቸዉ ግለሰቦች ከትላንት እስከ ዛሬ በድርጅቱ ዉስጥ ተፅኖ ፈጣሪ መሆናቸዉ ነዉ። መብረሃቱ ገብረህይወት(በረከት ስመኦን) ፣ አዲሱ ለገሰ ፤ ካዕሳይ ተክሉ (ከበደ ጫኔ)  ፤ ገነት ገብረእግዚያቤር ወዘተ……
.
እነዚህ በአማራ ስም በድርጅቱ ዉስጥ የተሰገሰጉ ትግሬዎች ናቸዉ ብአዴንን በዋናነት የሚመሩት እነዚህ ሰዎች በብአዴን ዉስጥ ያላቸዉን ተፅኖ በጥቂት ምሳሌዎች ላሳያችሁ።
1=> ብአዴን ስለሚለዉ ስያሜ 
#ብአዴን ስያሜ አማርኛ ሳይሆን ትግርኛ ነዉ ቃሉም ሲተነተን  ” #ብሄረ_አማራ_ንድሞከራስ_አብ_ንቅናቅ” የሚለዉን ፍቺ የሚሰጠን ሲሆን አንዳንድ የዋሆች ብአዴን የሚለው ቃል “ብሄረ አማራ ዴሞክሪያሳዊ ንቅናቄ ” የሚል ይመስላቸዋል። ይህ ፈፅሞ ስህተት ነዉ #የአማርኛ_ሰዋሰዉ ጠንቅቆ የሚያዉቅ ማንኛዉም ሰዉ በዚህ ሀሳብ አይስማማም።
.
ከብአዴን እና ከህዉሀት ዉጭ ያሉትን ድርጅቶች ስያሜ ብንመለከተ የሚወክሉትን ህዝብ መጠርያ ከፊት ለፊት በማስቀደም ከሰዋሰዉ ህግጋት ጋር በቀጥታ የሚስማሙ ሆነዉ ይህም  እናገኛቸዋለን ለምሳሌ
#የኦህዴ(የኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክሪያሳዊ ) ፣
#አብዴፓ(የአፋር ህዝቦች ዴሞክሪያሳዊ ፓርቲ) ፤
#ደኢህዴን(ደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክሪያሳዊ ፓርቲ) ፤
#ሶህዴፓ(ሶማሌ ህዝቦች ዴሞክሪያሳዊ ፓርቲ) ወዘተ…….. የሚለዉን ስያሜያቸዉን እናገኛለን። ለዚህም ነዉ ብአዴን ማለት አማርኛ ሳይሆን ትግረኛ ነዉ የምለዉ ይህን ስያሜ የሰጡት ደግሞ የአማራ ማንነት የሌላቸዉ ነገርግን አማራ ነን ብለዉ በድርጅቱ ዉስጥ ሰርገዉ የገቡ ትግሬዎች ናቸዉ።
2=> የብዴን የምስረታ ቀን ህዳር 11 
ብአዴን የተመሰረተዉ ህዳር 7 ጀምሮ ህዳር 11 ቀን 1973 ባለዉ ቀን ዉስጥ ነዉ። ነገር ግን በድርጅዩ ዉስጥ ያሉ ትግሬዎች ከ7 እስከ 11 ካሉት ቀናት #ህዳር_11 መረጡለት። 11 የትግሬዎችን የግንባር አካባቢ ንቅሳትን እንደሚወክል ኤርትራዊዉ #ተስፋየ_ገብረአብ የደራሲው ማስታወሻ በተሰኘዉ መፀሀፉ ፅፎበታል፡፡ህዉሀት ቢሆን ተመሰረትኩበት የሚለዉ እና የሚያከብረዉ ብሎ የሚያከብረዉ #የካቲት_11 ቀን 1967 ነዉ።
3=> አማራን ይወክላል የተባለዉ ባንዲራ 
ሌላዉ ጉድ የሚያሰኘዉ እነዚህ በብአዴን ዉስጥ የተሸጎጡ ትግሬዎች ለብአዴን የሰጡት ባንዲራ ከህዉሀት ጋር መመሳሰሉ ነዉ። በአሁኑ ሰአት የአማራ ህዝብን ይወክላል ተብሎ ለብአዴን የተሰጠዉ ባንዲራ ከአማራ ህዝብ ስነልቦናም ሆነ ታሪክ ጋር ምንም ተያያዥነት የሌለዉ ሲሆን ትግሬ የሆኑት እነ #መብረሃቱ_ገብረህይወት(በረከት ስመኦን) ባላቸዉ የትግሬነት ስነልቦና የአማራ መለያ ብለዉ ከህዉሀት ባንዲራ መለየት እስከሚቸግር ድረስ ተመሳሳይ አድርገዉ ሰርተዉታል።
2ቱም ቀይ እና ቢጫ ቀለምን ብቻ ይጠቀማሉ
2ቱም በባንዲራቸዉ ላይ ኮከብ ይጠቀማሉ
2ቱም በባንዲራቸዉ ላይ በቀይ መደብ ላይ ባቢጫ ኮከብ አርማ ይጠቀማሉ።
4=> የአማራ ህዝብ ተቋማትን ትግራይ ተኮር ስያሜዎች መስጠት
ሌላዉ አሳፋሪ ነገር ደግሞ የአማራ ህዝብ የራሱ የሆኑ ጀኞች ፣ ታሪክ ፣ ቅርስ የሌለዉ ይመስል እነዚህ በብአዴን ዉስጥ የተሰገሰጉ የትግራይ ሰዎች በአማራ ክልል ዉስጥ ያሉ ለተቋማትን ፤ ትምህርት ቤቶችን ፣ መንገዶችን ሳይቀር በትግራይ ተወላጆች እና ትግራይ ነክ የሆኑ ስያሜዎችን ቀይረዉታል ሌላዉ ቀርቶ ወያኔ ከመግባቱ በፊት በ 1940 ዎቹ የተገነባው የባህርዳር የአየር ማረፊያን ሳይቀር ግንቦት 20 ብለዉ ሰይመዉታል።
#በሸዋ አንድ መንገድን በመለስ ዜናዉ ስም ሰይመዋል።
#በጎጃም የባህርዳር አየር መንገድን ግንቦት 20 ብለዉ ሰይመዋል
#በወሎ ኮምቦልቻ አንድን ትምህርት ቤትን በመለስ ዜናዉ ስም ሰይመዋል።
#በጎንደር በለሳ ላይ አንድ ትምህርት ቤትን በመለስ ዜናዉ ስም ሰይመዋል።
.
.
5=> የአማራ ግዛቶችን በተመለከተ 
ህዉሀት እንደ ትልቅ ስኬት ከሚቆጥረዉ አንዱ በብአዴን ዉስጥ በሰገሰጋቸዉ ግለሰቦች አማካኝነት የአማራን መሬት ያለህዝብ እዉቅና መዉሰዱ ነዉ። በእነ #ታደሰ_ካሳ አስማሚነት #ራያን ሲወስድ #በነበረከት_ስማኦን ዉሳኔ ደግሞ #ወልቃይትን ወስዷል። ከሁሉም በላይ ደግሞ #ሱዳን በመተማ በኩል የአማራ ግዛቶችን ለመቀማት ወረራ ስትፈፅም እንዳላየ ሆኖ አልፎ ኤርትራ ታሪካዊ ዛቶቿ ሆኑትን #ባድመን እና #ሽራሮን ለማስመለስ ወረራ ስትፈፅም ድረሱልኝ በማለት ከ80,000 በላይ ህዝብ ማስጨረሱ ነዉ።
.
እዉን የአማራ ህዝብ የራሱ ስነልቦና እና ታሪክ የሌለዉ ህዝብ ስለሆነ ነዉ እንደዚህ መቀለጃ የሆነዉ??? ፈፅሞ አይደለም እዉነቱን ለመናገር ድፍን ኢትዮጵያ ላይ እንደ አማራ ህዝብ ከዉቅያኖስ የሰፋ ፤ ከባህር የጠለቀ ታሪክ ያለዉ አንድም ህዝብ የለም ዳሩ ግን ህዉሀት በዉክልና ያስቀመጣቸዉን ሰዎች ተጠቅሞ ክልሉን በእጅ አዙር ስለሚያስተዳድር ነዉ።
የግርጌ ማስታወሻ
ብአዴን ከሁሉም በላይ ሊያስብበት የሚገባዉ ስሙን ብቻ ሳይሆን ግብሩንም መቀየሩ ላይ ነዉ ይህን ለማድረግ ቁርጠኝነት ካነሰዉ የለዉጥ ሀይል የሚል የሞኝ ብሂል መጠቀብ ቢያቆሙ የተሻለ ይመስለኛል ።
Filed in: Amharic