>
5:14 pm - Saturday April 20, 7878

ከበረከት ስምኦን "ትንሳኤ ዘ ኢትዮጵያ" ከሚለው መፅሀፍ ውስጥ የተቀነጫጨቡ ሀሳቦች!!! (ፍጹም አማረ)

ከበረከት ስምኦን “ትንሳኤ ዘ ኢትዮጵያ” ከሚለው መፅሀፍ ውስጥ የተቀነጫጨቡ ሀሳቦች!!!
ፍጹም አማረ
 መታሰቢያነቱ ለምንጊዜም መምህሬ መለስ ዜናዊ  ካላንተ ይህች ኢትዮጵያ ካሸለበችበት ቀና አትልም ነበር። ይህን የምለው የጓዶችህንና የሰፊውን ህዝበ ኢትዮጵያ ሁሉ ሚና አሳንሼ በማየት አይደለም ። ካለነርሱ አንተም እንዲህ አትሆንም ነበርና ነገር ግን አንተ ልዩ ሰው ነበርክ በዚህ መጽሃፍ በበቂ ሁኔታ ብገልፀውም ባልገልፀውም  በተሟላውም በተነካካውም  አሻራህ የሌለበት  አርቆ አስተዋይነትህ ያላረፈበት ከቶ ምን ነገር ነበር ? በርግጥ ያላንተ የማሽቆልቆሉ ጉዞ ይገታ ነበርን ? ቀና ማለትስ እንችል ነበርን ? ታሪክ ሰሪው ሰፊው ህዝብ መሆኑ ባያከራክርም  በታሪክ የማይተካ ሚና የሚጫወቱ አንተን የመሰሉ ታላቅ መሪዎች በሌሉበት ሃገራችን ይህን ያህል ርቀት መጓዝ አትችልም ነበር ።
 የፃፍኩት ዛሬን ብቻ እያሰቡ ህይወታቸውን ያለ ትህትና ለሚኖሩና ለሚመሩ ሰዎች የፍርድ ቀን በሰማይ ቤት ብቻ ሳይሆን በምድርም ላይ እንዳለ ለማሳየት ነው” ከቅርብ ግዜ ወዲህ ደግሞ በፌዴራል እና በሁሉም ክልሎች የምታዘበውን የማን አለብኝነት አዝማሚያ በግልፅ በአደባባይ በመግጠም በትንቢት ለተሞሉ መሪዎች የዲሞክራሲያችን ወርድ እና ስፋት ለማሳየት እና የምንወስናቸው ውሳኔዎች ኃላፊነትና ተጠያቂነት እንደማይቀርልን ለማስገንዘብ ነው።
 የምጨነቀው ለአሁኑ ሳይሆን ከስድስት መቶ አመት በኃላ ለኖረው ስሜ ነው
 ይህንን መፅሀፍ የፃፍኩት የፍርድ ቀንን ከሰማይ ሲጠብቁ ጊዜ ያላቸው የሚመስላቸው ሁሉ ማህበራዊ ብይን እዚሁ በምድር ላይ ከቅርባቸው እንደሚያገኙት ለማሳየትም ጭምር ነው።
 ( በረከት ስምኦን ፥ ትንሳኤ ዘ – ኢትዮጵያ )
Filed in: Amharic