>
5:13 pm - Sunday April 18, 5638

የኢትዮጵያ መከላከያ ሀይል ቢዘገይም መግባቱ ነፍሰ ለማዳን ተገቢ ነው!!! (ታደለ አሰፋ)

የኢትዮጵያ መከላከያ ሀይል ቢዘገይም መግባቱ ነፍሰ ለማዳን ተገቢ ነው!!!
ታደለ አሰፋ
ባለፈው ቅዳሜ ጅጅጋ ላይየሰማነውን ድረሱልኝ ዋይታ ዛሬ ሰኞ  መልስ ማግኘቱን በሚካኤል ቤተክርስቲያን ተጠግቶ የነበረው ህዝብ በሆታና በዕልልታ ድምፁን ሲያሰማ ቪኦኤ አማርኛ በቀጥታ አሰምቷል ዛሬ ኦገስት 6 2018።
የትግራይ ክልል መግለጫ  ስለህገ መንግስት መከበር የመጨነቁን ያህል ስለህይወት መጥፋት ቅድሚያ ያለመስጠቱ በአጋጣሚ አይደለም።
የክልል ታጣቂዎች ህዝብ ሲገድሉ ቤተክርስቲያን ሲያቃጥሉ  በመሠረቱ ህገመንግስትነው የተጣሰው ይህ ሲሆን የፌድራል መንግስት በመዘግየቱ የኢትዮጵያን ህዝብ በይፋ ይቅርታ መጠየቅ ይኖርበታል ።
የክልል ነዋሪዎች በዜግነት  ኢትዮጵያውያን በመሆናቸውና ድረሱልንአለቅን ሲሉ መከላከያ ዝም ካለ ታዲያ ሌላ ምን ስራ አለው ???
የትግራይ ክልል መግለጫ ና የኦጋዴን ብሔራዊ ንቅናቄ መግለጫተመሳሳይ ነው ።መከላከያ ከገባ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የመከላከል መብት እንዳለው ነው የተነገረን።
ዘጠኝ ክልሎች ክልላቸውን ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጥቃት የመከላከል መብት ልክ እንደ ዘጠኝ ነፃ ሪፐብሊክ ካላቸው ታዲያ ኢትዮጵያ አለች ይባላል ??
የትግራይ ክልል ያሰማው ጩኸት የኢትዮጵያ ን መከላከያ ለማስጠንቀቅ ይመስላል ። በኔ ክልል ዝርብትሉ እዋጋለሁ ማለት ነው።
ጅጅጋ በዕልልታ ተቀብሎታል መከላከያ ሰራዊቱን የአብዲኢሌ ልዩ ፓሊስ ልብሱን ቀይሮ ጥቃት ይቀጥል አይቀጥል ወሳኙ አብዲ ኢሌ ነው። ከክልል ፕሬዚዳንትነቱ ይልቀቅ እንጅ ክልሉ መዋቅር እንዳለ ነው ።
የዐብዲ ኢሌ ልዩ ፖሊስ በይፋ ማሸበሩን ሊያቆም ቢገደድም  ከኦብነግ ከህወሓት ጋር ግንባር በመፍጠር የዐቢይን አስተዳደር መቃወሙን ይቀጥላል ።
በድሬዳዋም ከአስራ አራት በላይ ዜጎች የተገደሉት ሳጅን የፖሊስ ሀላፊ  ጀርመንአማርኛ ዘርን መሰረት አይደለም ያሉት በቪኦኤ አማርኛ ግድያው ሶማሌ ና ናሮሞዎችመካከል መሆኑ ተነግሯል ።
 ጅጅጋ ላይ የተፈፀመው ግድያ ቁጥር ገና ያልተረጋገጠ አስከሬን ያልተቀበረ ሰባት አብያተክርስቲያናት የተቃጠሉበት ህዝብቤትና ንግዶችየተቃጠሉበት ሶማሌ ተወላጆች ባልሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ አልሻባብ ሲመኘው የነበረው በመፈፀሙ መግለጫ ቢሰጥአይገርምም።የታላቅዋ ሱማሌ ባንዲራ በጅጅጋ እንደተዉለበለበው ሁሉ።
የጅጅጋው ከሌላው ጊዜ ልዩ የሚያደርገው አሸባሪውአልሸባብንሲዋጋየነበረው ልዩ ፖሊስ ጠመንጃውን ወደ ህዝቡ ማዞሩ ነው።
ይህን ዕልቂት በህገመንግስት ሽፋን የኢትዮጵያ መከላከያ ሀይልሳይገባ ለጠፋው ህይወት ና ንብረት የጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግሥት ሀላፊነት መውሰድ አለበት ።
የሶማሌ ክልል ፀጥታ ከምንጊዜውም በላይ ፈተና እንደሚጋረጥበት የታወቀ ቢሆንም ሌሎች ክልሎች ውስጥ ያሉ ማናቸውም ታጣቂዎች እንደ ሶማሌ ልዪ ፖሊስ ዘርተኳር ግድያ ዘረፋ ማፈናቀል በማድረግ ላይ ባሉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሳይዘገይ  ቁጥጥር ማድረግ ይኖርበታል።
ድሬዳዋም ከጅቡቲ ባለው ትስስር በአርባ አርባ ሀያ ጎሳዊ ቅምር የሰው ህይወትማዳን ስላልተቻለ በመከላከያየኢትዮጵያናኢትዮጵያውያንደህንነት ይረጋገጥ ።
Filed in: Amharic