>

ዶ/ር ዳኛቸውና ኢ.ቴ.ቪ (ሄኖክ አሰፋ)

ዶ/ር ዳኛቸውና ኢ.ቴ.ቪ
ሄኖክ አሰፋ
 
“….ሕወሃት ሆይ  ይህንን ህዝብ እንደገና እንጋልበዋለን የሚል አባዜህ ማክተሙን ተገንዘብ!!!”
ዶ/ር ዳኛቸው
 
* ሕወሃት ሆይ ከእንግዲህ ሌብነት፤ ግድያ ፤ ዘረፋ፤ ውሸት ፤ ዘረኝነት አክትሟልና ከቅዠትህ ተመለስ! ዓለም በሙሉ ወራዳና ጨካኝ ፋሺስት፤ አሸባሪ ድርጅት መሆንህ አውቋል!
 
ዶ/ር ዳኛቸው የፖላቲካ ፈላስፋ እንደሆኑ በውይይቱ ጊዜ ሰምቻለሁ። ብርሃን በርቶ ይኸው አሁን ብርሃን የሆነ ነገር እየሰማን ነው። ዶ/ር ዳኛቸው የሕወሃት መንግሥት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በግፍ ያባረራቸው ምሁር ናቸው። ዶ/ር አቢይ አህመድ ግን በመንግሥታቸው ስም ይቅርታ ጠይቀዋቸው ወደ ቀደመው ሥራቸው እንዲመለሱ በሩ ብው ብሎ ተከፈተላቸው። እሳቸውም ይህን በሰሙ ጊዜ በጣም ጣፋጭ እንቅልፍ እንደነበራቸው መሰከሩልን።
ብርሃን በራላቸው ለምሁራን። በኢ.ቲ.ቪ በይፋ የሚፈልጉትን እየተናገሩ ነው። ሕዝባቸውንም እየመከሩና እያስተማሩ ነው። ይኸው ኢቲቪና ጋዜጠኛ ከአራት ወር በፊት እንደ ዶ/ር ዳኛቸው ያሉትን ማየትም ማነጋገርም አይመቸውም ነበር። አሁን ግን ኢቲቪና ጋዜጠኞች ነፃ ወጡ።
ዶ/ር ዳኛቸው በስህተት የተጋበዙ ይመስለኛል። ጋዜጠኛው የሚደጋግማቸው ነገሮች ሁሉ የሕወሃት መንግሥት ባለመኖሩ አገር እንደሚፈረስና በመኖሩ ምን ያህል እንደተጠቀመ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊጠቁመን የሚፈልግ አዝማሚያ ያለው ነው። ጋዜጠኛው በጥያቄዎቹ ሁሉ የሚሰካቸው አሳቦች በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ሊመክራት የሚችል ፈላስፋ እንዳጣች፤ በየቦታው ግጭት እንዳለ፤ የፌዴራል ሥርዓቱ እየፈረሰ እንደሆነ፤ የመሳፍንት ዘመን እንደመጣ፤ ልማታዊ ዲሞክራሲያዊ መንግሥት እንደተወገደ፤ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ወዴት እያመራች ነውና የመሳሰሉት ናቸው።
ምስጋና ይግባቸውና ዶ/ር ዳኛቸው ለወጣቱ ጋዜጠኛ፤ለታዳሚዎችና ለኢትዮጵያ ሕዝብ በረጋና ጨዋነት በተሞላበት መንገድ የሚያስፈልጉትን ነገሮች አስተምረዋል፤አስተላልፈዋል።በሕወሃት ተጠምቀው ፤በሕወሃት ቋንቋ ሲናገሩ የነበሩ የኢቲቪ ጋዜጠኞች አሁንም ሕወሃት ሆይ ተመለስልን እያሉ ነው።አዲሱ ቋንቋ አልተመቻቸውም፤ብዙ ማንበብ ያስፈልጋልና።ሁሉንም ጋዜጠኞች ማለቴ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ።በሥጋቸው የደለቡት አሁንም ለውጡ አልተመቻቸውም።
 አንዳንዱን ብናገር ደስ ይለኛል።አሁንም አቦይ አቦይ የሚሉ አንዳንድ የትግራይ ምሁራንና ካድሬዎች አሉ።አቦይ ከሚነግሯቸው ውጭ ያማይሰማቸውና የማይታያቸው አሉ። እንደ አብርሃ ደስታ፤ጌታቸው ረዳ፤አባይ ፀሐየ፤ተክለብርሃን ወልዳረጋይ፤ሳሞራ ዩንስ፤በረከት ስምኦን፤ሕላዊ ዮሴፍ፤ስዩም መስፍን ያሉት አሁንም አቦይ እያሉ ነው።አሁን ብርሃን አልታያቸውም፤በጨለማ ውስጥ ናቸው።ብርሃን ስታይ ተከተል ሲሉ ዶ/ር ዳኛቸው የሚሉት ፋና ወጊ አሳብ ዓይናችንን ያሳውራል ብለው ስለሚያስቡ አሁንም በጨለማ ውስጥ መኖሩን ተያይዘውታል።
ብርሃን የሚያስጠላቸው የሕወሃት ምሁራንና አንዳንድ የትግሬ ሰዎች ጨለማን እየሰበኩ ነው።ሱማሌ የሚካሄደው የአብዲ ኢሌ አመራር፤በሕወሃት የተገነባው የጨለማ መዋቅር  ቤተክርስቲያናትን እያቃጠለ፤ዜጎችን በብሄራቸው ተለይተው እየተረሸኑ፤ንብረት እየተዘረፈ፤ንብረት እየተቃጠለ ነው።ዘር ተኮር ጥቃት ይቁም እያለ በየሰላማዊ ሰልፉ የሚለፍፈው የትግሬ መንግሥት ዘርን አስመልክቶ የሚረሽነውን አብዲ ኢሌን በመደገፍ ጸጥታን ለማስከበር ሱማሌ ክልል የገባውን የፌዴራል ፖሊስና የደህንነት ኃይል እየተቃወመ ነው።በብርሃን የሚመላለሱ  የሚናገሩትንና የሚሰሩትን ነገር ሁሉ በሚገባ ያጤናሉ።ሕወሃት ግን በኒኮል ማክአቬሌ ዘመን ያሉ የጨለማ ሰዎች ናቸው።ሌላ አያውቁምና።ዶ/ር ዳኛቸው ምስጋና ይግባቸውና ለሕወሃት መልእክት አስተላፈዋል።   አሁን ያለው ለውጥ የሕዝብ ተቀባይነት አግኝቷል።በየክልሎችና  በአዲስ አበባ የተደረጉት  ሰላማዊ ሰልፎች ለሚገባው ሥር ነቀለ መልእክት አስተላፈዋል።ሕዝቡ ለውጡን ተቀብሎታል።ሌላው ደግሞ ይህን ለውጥ ለማደናቀፍ የምትፈልጉ የጨለማ እጆች ሰብሰብ በሉ የሚል ነው።አለበለዚያ ግን የሚቀጥለው እርምጃ እንደገና አራት ኪሉ ቤተመንግሥት ገብተን የጨለማውን ዘመን እንመልሳለን የሚል ቅዠት ካላችሁ ከነቅዠታችሁ ትጠፋላችሁ የሚል ነው።የመጣው ለውጥ በግድያ ሳይሆን በሰላም የተደረገና የሕዝብን ልብ የሳበ ነው።ልብ ያለው ሁሉ እየተደመረ ነው።የማይደመሩ ሁሉ ከባቡሩ መውረድና መፈጥፈጥ ግድ ይላል።ከዚህ በፊት ግን ይመከራሉ።ተመክረው ተመክረው የማይደመሩ ሁሉ መከራው ይደምራቸዋል።
ዶ/ር ዳኛቸው ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ።አማራና ኦሮሞ መሸከም በቃን ብሏል።ሕወሃት ሆይ  እንደገና እንጋልብሃለን የሚል አባዜ ማክተሙን ተገንዘብ።ዶ/ር አቢይ አህመድ አራት ኪሎ ቤተመንግሥት ሲገባ ለመስረቅ ሳይሆን ሕወሃት የሰረቀውን ለማስተፋትና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሕወሃት ካሸከመው ቀንበር ነፃ ለማውጣት ነው።መቐለ መሽጎ በገንዘብ የሚሰራ አሻጥር በሕዝብ ኃይል እንደሚኮላሽ አትጠራጠሩ።ለውጡ የሕዝብ ነው።ሕዝብ የተሰዋበት ለውጥ ነው።ሕወሃት ሆይ ከእንግዲህ ሌብነት፤ግድያ ፤ዘረፋ፤ውሸት ፤ዘረኝነት አክትሟልና ከቅዠትህ ተመለስ።ሕወሃት ዓለም በሙሉ ወራዳና ጨካኝ የፋሺስት፤አሸባሪ ድርጅት መሆኑን አውቋል።ይልቅስ ሰው ወደመሆንና ወደ ሰው አስተሳሰብ መመለስ እራስን ማዳን ነው።ኢህ አዴግ የመረጠው ጠ/ሚ አቢይ አህመድ የሕዝብ ጠ/ሚ ሆኗል።ከእንግዲህ ዶ/ር አቢይ አህመድን ከኢትዮጵያ ሕዝብ መለየት አይቻልም።
 
Filed in: Amharic