>

እቅጩን ልንገራችሁ… ህወሓት ፋሽስት ነው! (ስዩም ተሾመ)

እቅጩን ልንገራችሁ… ህወሓት ፋሽስት ነው! 
ስዩም ተሾመ
የህወሓትን አመሰራረትና ባህሪ በዝርዝር ለማወቅ ያደረኩት ጥረት አንድ እውነት እንድገነዘብ አስችሎኛል። ይኸውም፣ ህወሓት ወደ ስልጣን የመጣበት መንገድ እና አሁንም ድረስ የሚከተለው የፖለቲካ ስልት፣ እ.አ.አ. በ1938 በጀርመን ከነበረው የናዚ ፋሽስት፣ እንዲሁም በተመሳሳይ ወቅት በጃፓን ከነበረው ወታደራዊ ፋሽስት ጋር አንድና ተመሳሳይ መሆኑ ነው።
የህወሓት መሰረታዊ ባህሪ በአጭሩ በሚከተሉት እሳቤዎች ላይ የተመሰረተ ነው፡-
 አንደኛ፡- በህወሓት አባላት መካከል ልዩነት የለም፣ ሁለተኛ፡- ከህወሓት ሌላ የትግራይን ህዝብ ጥቅም የሚያስከብር የፖለቲካ ቡድን የለም፣
 ሦስተኛ፡- በትግራይ ሕዝብ (ተጋሩዎች) መካከል ልዩነት የለም፣
አራተኛ፡- በህወሓት እና የትግራይ ሕዝብ መካከል ልዩነት የለም። ስለዚህ የተለየ አቋምና አመለካከት ያለው አባል ወይም የአማራጭ የፖለቲካ ቡድን ከሌለ፣ በትግራይ ህዝብ መካከል፣ እንዲሁም በሕዝቡና ፓርቲው መካከል ልዩነት ከሌለ አጠቃላይ የፖለቲካ ስርዓቱ በፍፁም አንድነት ወይም አንድ-ዓይነትነት (Oneness) ላይ የተመሰረተ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል።
ይህ ምን ማለት እንደሆነ እና ህወሓት የትግራይ ህዝብና ኢትዮጵያን ወደዬት ሊወስዳቸው እንደሚችል ማወቅ ከፈለግክ በተለይ “Hannah Arendt” የተባለችው ጸሓፊ “On the Nature of Totalitarian: An Essays in Understanding” በሚል ርዕስ የፃፈችውን ጥናታዊ ፅሁፍ፣ እንዲሁም “Edward Said” (1993) “Representations of the Intellectual፡ Holding Nations and Traditions at Bay” በሚል ርዕስ ያወጣውን ፅሁፉ አንብብ። ከዚያ በኋላ የህወሓት ማንነትና ወደዬት እንደሚወስደን ቁልጭ ብሎ ይታይሃል። ያኔ እልም ካሉ ፋሽስቶች ጋር አብረህ እየኖርክ እንደሆነ ይገለጥልሃል። ከዚያ በኋላ ከፋሽስት ጋር እንዴት መደራደር እንደሚቻል ትነግረኛለህ።
Filed in: Amharic