>
5:13 pm - Sunday April 19, 6922

ከስደት የተመለሱት አባቶች ለመከራ ይዘጋጁ!!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

ከስደት የተመለሱት አባቶች ለመከራ ይዘጋጁ!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው 
ወያኔ ቤተክርስቲያኗን ተቆጣጥረው ጥቅሙን የሚያስከብሩለት፣ አከርካሪዋን የሚሠብሩለት በርካታ ሐሰተኛ ካህናት መንበረ ፓትርያርክ ግቢ ውስጥና በየሀገረ ስብከቱ ውስጥ አስቀምጧል፡፡
እነኝህ ሰዎች ሰዎች እንዳይመስሏቹህ፡፡ በቁማቸው ሥጋ የለበሱ አጋንንትና እራሱ ሳጥናኤልን ናቸው፡፡ እንኳን ለሃይማኖት ሕግጋት ይቅርና ኢአማኒ፣ አረመኔ፣ አሕዛብ እንኳን ለሚገዛበት ለሞራል (ለቅስም) ሕግ እንኳን የሚገዙና የሚያከብሩ አይደሉም፡፡ እነኝህ አጋንንት ወያኔዎች ናቸው የቤተክርስቲያኗን ካዝና ያራቆቱት፣ በአሥተዳደር በደል ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንንና ካህናትን ቁምስቅል የሚያሳዩ፣ በአገልግሎት መጓደል በሙስናና በአድልኦ ምእመናንን አሳር የሚያበሉ….. እነኝህ ልቡሳነ ሥጋ አጋንንት ናቸው፡፡
ከስደት የተመለሱት አባቶች እንግዲህ በእነዚህ አጋንንት እጅ ነው የወደቁት፡፡ ምን ያህል ፈተና መከራና ፍዳ እንደሚጠብቃቸው እንግዲህ አስቡት፡፡ እነኝህ ተሰዶ የነበረው የቤተክርስቲያኗ ሲኖዶስ አባላት በእርግጠኝነት በሚቀጥሉት ሁለት ሦስት ቀናት ውስጥ ይሄ የወያኔ ቡድን የቤተክርስቲያኗን አሥተዳደር ተቆጣጥሮ ባለበት ሁኔታ ከስደት ለመመለስ ተስማምተው መግባታቸው ሲበዛ የዋህነት የተሞላ የተሳሳተ ውሳኔ እንደሆነ ይገነዘባሉ፡፡ ያኔ ያ ተኩላ ዐቢይ እንዴት አድርጎ አዋክቦ፣ ደልሎና አታሎ እንደተጫወተባቸው ይገባቸዋል፡፡
እርግጥ ነው በድርድሩ ወቅት እንዲህ ዓይነት ችግሮችን ለመከላከል በማሰብ የመተዳደሪያ ደንብ እንደሚቀረጽ ተስማምተዋል፡፡ ነገር ግን አሁንማ እኮ ገብተዋል፡፡ አሥተዳዳሪዎቹ እነ አቦይ ማትያስ እንደሚሏቸው ማደር እንጅ ምን የማለት መብት አላቸው??? ከዚህ በኋላ እንኳንና መብታቸውን የሚያስከብር ደንብ የማይወጣ መሆኑ ግልጽ ሆኖ እያለ ቀርቶ መብታቸውን የሚያስጠብቅ ደንብ ቢወጣም እንኳ ተፈጻሚ ስለማይሆን መከራው የሚቀርላቸው አይሆንም፡፡ ምክንያቱም አሁን እንደሚታየውና ሁሉም እንደሚያውቀው የአሥተዳደር በደልና ሙስና እጅግ አሳፋሪ በሆነ ደረጃ በቤተክርስቲያን ውስጥ የተንሰራፋው ሕገ ቤተክርስቲያን ይሄንን ስለሚፈቅድ አይደለምና፡፡ ወይም ደግሞ ሕገ ቤተክርስቲያን ሳይከለክል ሳያወግዝ ቀርቶ አይደለምና ነው፡፡
በመሆኑም መከራ አይቀርላቸውም፡፡ ፈተናው መከራው ከምን ይጀምራል መሰላቹህ እነኝህን አባቶች ሊጎበኟቸው የሚፈልጉ እንግዶችን፣ የብዙኃን መገናኛ አካላትን ወዘተረፈ. እንዲያገኟቸው፣ እንዲጎበኟቸው፣ እንዲጠይቋቸው ባለመፍቀድ ወይም በመከላከል፣ ምግብን ጨምሮ አስፈላጊ አቅርቦቶችን በመከልከልና በማስተጓጎል አሳራቸውን ነው የሚያበሏቸው፡፡ ያኔ ዐቢይ ዐቢይ ቢሉ ዐቢይ መስሚያው ጥጥ ነው፡፡ “ቄሶቹ ምን እያሉ ነው?” እያለ በሚሆነው ነገር ሁሉ እግሩን እያነሣ ነው መሥሪያ ቤቱ ውስጥ ተቀምጦ የሚስቀው፡፡ አቤቱታ እንኳ ለማቅረብ አያገኙትም፡፡ በሆነ አጋጣሚ ቢያገኙት እንኳ “መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ራሳቹህ ተነጋግራቹህ ፍቱት!” ብሎ ነው የሚያፌዘው፡፡
እንግዲስ አባቶች ሆይ! ሲኦል ውስጥ ገብታቹሀልና እግዚአብሔር ይሁናቹህ!!! ከአጋንንት ጋር በግላጭ ተገናኝታቹሃልና መጽሐፈ መነኮሳታቹህ እንደሚያዛቹህ ወገባቹህን አስራቹህ ተጋደሉ እንግዲህ!!!
“ወደመጣንበት እንመለሳለን!” እንዳትሉ እንኳ ከእንግዲህ በፈቃዳቹህ ማደር አትችሉም፡፡ አጠቃላይ እንቅስቃሴያቹህ በሙሉ የቤተክርስቲያኗን አሥተዳደር አሳልፋቹህ በሰጣቹህት አካል ነው የሚወሰነው፡፡ እንሔዳለን ብትሉ “ቆይ ምደባ አልተሠራም!” እያሉ አይፈቅዱላቹህም፡፡ ሲመድቧቹህም እነሱ በፈለጉት ቦታና ሀገር ነው እንጅ የሚመድቧቹህ እናንተ በምትፈልጉት ቦታና ሀገር አይሆንም፡፡
ጭራሽ እንዲያውም እነሱ ራሳቸው በቤተክርስቲያን ስም ኑፋቄ የተሞላበት የትግርኛ መጽሐፍ ቅዱስ አሳትመው በትግራይ በማሰራጨት ትግሮችን በሙሉ መናፍቅ ለማድረግ እንዳልሠሩና ከነሱ መሃል መናፍቃን ጳጳሳት እንደሌሉ ሁሉ ለቤተክርስቲያን ያሰቡና መናፍቅነትን የማይደግፉ የሚያወግዙ በመምሰል ከስደት ከተመለሱት ውስጥ በመናፍቅነት የሚጠረጠሩትን እንዲህ ዓይነት ችግር እንዳለባቸው በመግለጽ “እስኪጣራ ድረስ ሥልጣናቹህ ተይዞባቹሃል!” ይሏቸውም ይሆናል፡፡ ይሄኛው እርምጃ እንኳን ጥሩ ነበር ግን እነሱ እራሳቸው ዋናዎቹ ሆነው እያለ ጠላትን ለማጥቃት ካልሆነ በስተቀር ለቤተክርስቲያን በማሰብ ይሄንን እርምጃ ሊወስዱ አይችሉምና ይሄ እርምጃ እነሱንም ካላካተተ በስተቀር አግባብነት አይኖረውም፡፡
ለማንኛውም እንግዲህ ከስደት የተመለሱት አባቶች ይሄንን ሁሉ ፈተና፣ መከራና ችግር ለመቀበልና ለማስተናገድ ተዘጋጁ!!!
እግዚአብሔር ይርዳቹህ!!!
ድል ለቤተክርስቲያን!!!
Filed in: Amharic