>
5:13 pm - Thursday April 20, 3645

 አርቲስት ፍቃዱ የሕዝብ ልጅ በመሆኑ ከገዳሙ ወጥቶ እንዲቀበር ተፈቅዷል!!!

አልመጣም! – ደህና ሁኑ!
 አርቲስት ፍቃዱ የሕዝብ ልጅ በመሆኑ ከገዳሙ ወጥቶ እንዲቀበር ተፈቅዷል!!!
ጌጡ ተመስገን
ትናንት – ባለቤቱን – ወይዘሮ ሙሉጌጥ መሰለ፣ ታናሽ ወንድሙ፤ ግርማ ተ/ማሪያም እንዲሁም የቅርብ ጓደኛው ሳሚ ስልኮች ዝግ ናቸው፡፡
ጉዳዩን ለማጣራት CMC መኖሪያ ቤቱ አመራን፡፡ በግቢው ኮምፓውንድ የጋሽ ፍቄ መኪና ቆማለች፡፡ አንደኛ ፎቅ ወጥተን አንኳኳን፤ ምላሽ የሚሰጥ ሰው አጣን፡፡
ጎረቤት ጠየቅን – ‹‹ፍቃዱስ?›› አልን፡፡
አልሰሙም፡፡ የፍቃዱን ነገር ቤተሰብም – ጎረቤትም – አገርም አልሰማም፡፡
በፌስቡክ መንደር ሞተ – ተብሎ ድንኳን ተጥሏል፡፡
‹‹የለም – አልሞተም!›› የሚል መረጃም በፌስቡክ ሸማቾች ዘንድ ነበር፡፡
ስልኬ ይንጫረራል – ‹‹ጌጣችን – ፍቄ ሞተ የተባለው እውነት ነው?››
***
እስከ ምሽቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ CMS መኖሪያ ቤቱ ግቢ ሆነን እየደወልን ነው፤ (አርቲስት ዳንኤል ተገኝ፣ ቴዎድሮስ ተስፋዬ፣ ናትናኤል ግርማ (ናቲ ድሬ)፣ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ እንዲሁም አንዷለም ሀዘኑን ወግ ለማስያዝ እየጣርን ነበር፡፡
በአንጋፋው አርቲስት ፍቃዱ ተ/ማሪያም፤ በአንተ ሥም በክብር ልጠራ ያለው የመንፈስ ልጁ ጋር ደወልኩ፡፡
ሀዘኑን ከፍቃዱ ተክለማሪያም ወንድም መስማቱን አረጋገጠልኝ፡፡ ይሁንና የፍቃዱ ወንድም ስልክ ዝግ ነው፡፡
 ከገዳሙ ሰው ፍለጋ ስልኬን መጠቅጠቅ አልተውኩም …
ከገዳሙ ዘመድ ጠይቃ የወጣች ልጅ – ‹‹መሞቱን አረጋገጠችልን!››
ጠዋት – የገዳሙን አስተዳዳሪ ወይንም የፍቃዱን ባለቤቱን – ወይዘሮ ሙሉጌጥ መሰለ እንድታገናኘኝ ለመነኳት፡፡
እሺ! – ብላ ተሰነባበትን፡፡
***
ለታናሽ ወንድሙ፤ ግርማ ተ/ማሪያም ደወልኩ …
‹‹ በተውኔት አርበኛ፤ በእምነቱ ጽናት አርበኛ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ልጅ፤ አንጋፋው አርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል …››
ወሎ- ሲርንቃ – አርሴማ ጠበል እንዳለ ትናንት ከምሽቱ 12፡00 ህይወቱ አልፏል። … የነሐሴ ፤ የፍልሰታ ጾም 16 ቀናት ቆይቶ ለመምጣት እቅድ ነበረው፡፡ …አልሆነም፤ አልፈቀደም!››
‹‹ገዳም ውስጥ የሞተ – የሚቀበረው በገዳሙ ውስጥ ነበር፡፡ ይሁንና ፍቃዱ የአገር እና የሕዝብ ልጅ በመሆኑ ከገዳሙ ወጥቶ እንዲቀበር አስፈቅደናል፡፡ …
አስከሬን ይዘን እየመጣን ነው …
Filed in: Amharic