>

የቱን እንመን???

የቱን እንመን???

* ከ40 በላይ የፌደራል ፖሊስ የፀረ-ሽብር ግብር ኃይል አባላትን መቀሌ ላይ ከበው እያናገሯቸው ነው!!!  ስዩም ተሾመ – ከዶ . ቬ

የኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ የፀረ-ሽብር ግብር ኃይል የሚል መለዮ እና አርማ ያደረጉ ከአርባ በላይ ታጣቂዎች መቀሌ፤ አሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ጣቢያ ተያዙ። ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ምንጮች ለዶቸ ቬለ እንደገለፁት ታጣቂዎቹን ያሳፈረዉ አንቶኖቭ አዉሮፕላን መቀሌ ያረፈዉ ዛሬ ጠዋት ነዉ።

መትረየስ ጭምሮ የተለያዩ የጦር መሳሪያ የታጠቁት ሰዎች ከሱዳን አዲስ አበባ ለመጓዝ አልመዉ በስሕተት መቀሌ ማረፋቸዉን ተናግረዋል ተብሏል።ዉስጥ አዋቂ ምንጮቻችን እንደሚሉት የትግራይ መስተዳድር ልዩ ኃይል ታጣቂዎቹን ክብቦ ጉዳዩ እየተጣራ ነዉ።

DW amharic

* የትግራይ ክልል “ወንጀለኞችን አሳልፌ አልሰጥም” አለ!!!
ሸምሱ ቢረዳ
ክንፈ ዳኘው ከፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ ወጥቶበት በፌደራል የፀረሽብር ግብረሀይል ለምርመራ ቢፈለግም የትግራይ ክልል ፀጥታ እና ደህንነት ሀይሎች ክንፈን አሳልፈን አንሰጥም በሚል ከፌደራል ሀይሎች ጋር በመቀሌ አሉላ አባነጋ አየር ማረፊያ ተፋጠዋል
ክንፈ ዳኘው የቀድሞው ሜቴክ ዋና ሀላፊ የነበረ ሲሆን በኢንጅነር ስመኘው በቀለ የነፍስ ግድያ ወንጀል እና የህዝብ ሀብትን በመዝረፍ ወንጀል ተጠርጥሮ ለምርመራ እየተፈለገ ነው።
የትግራይ ክልል ክንፈን ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ክንፈን ለህግ ለማቅረብ ወደ ክልሉ የተላኩ 40 የፀረሽብር ግብረሀይል ወታደሮችን በመቀሌ አሉላ አባነጋ አየር ማረፊያ አግቶ ይገኛል። ተጨማሪ መረጃ ይዘን እንመለሰላለን።
Filed in: Amharic