>
5:13 pm - Saturday April 18, 7891

ስለ ENN ውሸት በየቦታው እያወሩ የጋዜጠኞችን ህይወት ማበላሸት ከመሪዬ አልጠብቅም! - የፕሮግራም ክፍል ሃላፊ በቃል አላምረው

ስለ ENN ውሸት በየቦታው እያወሩ የጋዜጠኞችን ህይወት ማበላሸት ከመሪዬ አልጠብቅም!
የፕሮግራም ክፍል ሃላፊ) በቃል አላምረው
ስለ ENN እና ስለ እኔ!
ይህንን የፃፍኩት ስለጣቢያ የማስረዳትና ዋስትና የመቆም ስልጣን ኑሮኝ ሳይሆን እውነቱን ለማሳወቅ ነው! Enn በተመለከተ ያለው ሀሜትና ጠቅላይ ሚኒስትራችን የተናገሩት ከእውነቱ ይልቅ ለእኔ ለግሌ ውሸትና ተራ ሀሜት ይሆንብኛል፡፡ በክፍያና በአሰራር ዙሪያ ያለውን ነገር እየጠቀሱ ሰራተኛው ሞራል ላይ መረማመድ ለነጋችን ጥሩ አይደለም!  እኔ enn. በሙያ ፍቅር የተለከፋ፤ ነፃነት የሚፈልጉ፤ ለሀገርና ለወገን ክብርና መሻሻል የሚተጉ ትንታግ ሰራተኞች የነበሩበት ተቋም ነው፡፡ ተቋሙ ለጋዜጠኛና ለሀሳባችን የሚሰጠን ነፃነት ሀገር ውስጥ ባሉ ሚድያዎች ውስጥ በፍፁም  ይኖራል ብለን  የማይታሰብ ነው! የምናነሳቸው ጉዳዮችን ከወገናዊነት በማፅዳት ለሀገር እንዲጠቅሙ ማሰብ እጅጉን የሚበረታታበት ቤት ነበር፡፡ በአጭሩ ለሀገር ይጠቅማል የምትለው ነገር ስራ የምባልበት ቤት ነበር! ይህንን የትም ብንሄድ አናገኘውም! ሌሎች ሚዲያዎች ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ከፖሊሲያቸው በፋቁበት ዘመን ነበር ስለኢትዮጵያዊነት ሀገራዊ አንድነት፤ ስለ አብር መኖርና ብሔርተኝነትን ስለመዋጋት ያወራና ይዘግብ ነበር! አላማውም ህግና ስርዓት ያለውና የሚያከብር የህዝብ ድምፅ የሆነ ኢትዮጵያዊነትን የሚገነባ ነበር!!እኔ ፋና፤ አዲስ ቲቪ፤  ከመስራቴ ሁሉ በእጅጉ ENN መስራቴ ያስደስተኝና ያኮራኛል ፤መጀመሪያ ላይ ስቀጠር አዲስ ቲቪ ይከፍለኝ ከነበረው ደሞዝ እጅግ ባነሰ ገንዘብ ነው፡፤በሗላም ያንን ሁሉ ስራ እየሰራን የሚከፈለን ከሁሉም ሚዲያ በእጅጉ ያነሰ ነበር፡፡ በተለይ ሪፖርተሮች 5 ሺህ ብር ሁሉ ይከፈላቸው ነቀር! ሌላ ሚዲያ  በእኔ  ተመሳሳይ ደረጃና የሃላፊነት ቦታ ያለ ጋዜጠኛ ለጥቅማጥቅም ተብሎ የሚሰጠውን የሚያህል ደሞዝ እንኳን አልነበረኝም፡፡ የፕሮግራም ክፍል ሀላፊ እኮ ሌሎች ሚዲያዎች ላይ መኪና፤ ቤት፤ ብዙ ጥቅማጥቅም ይሰጠዋል፡፡ ለእኔ ግን እጄ ላይ የሚደርሰኝ 10 ሺ ብር ነበር!  እንዲሁም የግለሰብ መኖሪያ ቤት ተከራይቶ ቢሮ አድርጎ ይሰራ የነበረ ሚዲያ ነው፡፡ ሙሉ ሰራተኛው  ጥበቃና ፅዳትን ጨምሮ ከ90 የማይበልጥ ነበር፡፡ ተቋሙ የነበረው መኪና ሁለት ነበሩ! አንድ ባለ አራት መቀመጫ እና አንድ ቪትዝ፡፡ የምንቀሳሰቀሰው በታክሲ ነበር፡፡ ለስራ ወጥተን የሌላ ሚድያ ጋዜጠኞች ለምነን በጋራ የምንመጣበት ጊዜ ነበር! የትኛው መኪናና ነው ለኢኤንኤን ጋዜጠኛች መንፈላሰሻነት የተሰጠው..?
ሌላው የገንዘብ ምንጩ በእየወሩ ከሚገኘው ስፖንሰር እና የባለቤቶቹ ኪስ ነበር፡፡ ከቤት ኪራዩና ከሙሉ ክፍያው ጋር 7 መቶ ሺ የማይሞላ  ከታክስ ውጪ በወሩ ያወጣ ነበር! ጣቢያ የቀጥታ ስርጭቱና የውይይት ዝግጅቱ የመዝናኛ ጉዳዮቹን የአየር ሰዓት ይሸጥ ስለነበር ባለቤቱ ከኪሱ ከማውጣት ይድን ነበር፡፡ እውነትና ሀገርን እንደመውደዳችን መጠን በደስተኛነትና በልዩ ተነሳሽነት እንድንሰራ የነበረን ስንቅና ድጋፍ ጣቢያውን አሳድገንና  አላማውን አስፍተን  ሀገር ጠቅመን እንድንጠቀም ነበር! ዶክተር አብይ፦ ዜናው የፃፈው የመንግስት ባለስልጣን ነበር ያሉትም ውሸት፤ የዜና ክፍል ሀላፊው ብሩክ ወርቁ የት ሄዶ ነው!? ፤ ከፍተኛ ተከፋይ ያሉትም ከሌሎች ሚዲያዎች እጅግ ዝቅተኛ ክፍያ የሚፈፅም ተቋም ነበር፡፡ ድጋፋ ስፖንሰር ከሆነ ይህ መብት ነው፡፡ እሳቸውስ ለፋና ቲቪና ለebs ፤ ለetv፡ለኦሮሚያ ቲቪ የነበሩባቸው ተቋማት ይደግፋ ነበር አሁንም ይደግፋሉ!ነገር ግን መንግስት ennን  የመደጎም ሀላፊነት እንዳለበትም መርሳት የለባቸውም፡፡ስለ enn ውሸት በየቦታው እያወሩ የጋዜጠኞችን ህይወት ማበላሸት ከመሪዬ አልጠብቅም! የጣቢያ ባለቤት ጋ ዶክተር አብይና ደመቀ በእጅጉ የሚቀራረቡ ስለሆነ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ሲዋሹ ደስ አይልም! የenn ባለቤቶችና ስራ አስኪያጆች በዘር፤በብሄር  ከታሰበ ለዶክተር አብይ ይቀርባሉ! ጣቢያው የተዘጋ በእሳቸው አመራሮች መረጃ እንዳይሰጠን ስለተከለከልና የእሳቸው ወሬ በራስ ካሜራ አስቀርፆ ቆራርጦ አስተላልፋ እያሉ የሚልኩትን የመረጃ አፈናና ሌሎች የማይገቡ የመንጋ አካሂዶችን ስለምንቃወምና ለዚህ አሰራረም ስለማንመችም ጭምር ነው፡፡ ጣቢያው ኢህአዴግና ካድሪዎቹ በደንብ የሚያውቁትና የሚፈሩት በስራው ነው፡፡ግብር ከፍሎ ከመንግስ ስፖንሰር በህጉ መሰረት ከተደረገለት ችግሩስ ምንድነው..!? enn ከesat ጋ ማወዳደረስ ጤነኛኀት ነው..? ከጠቅላይ ሚኒስት አብይ አህመድ ለምን ነቀፋችሁን ከሚል ተራ ጥላቻ የእኛን ህይወት ከሚያበላሹ በመረጃ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ አይችሉምን..?
Filed in: Amharic