>
5:13 pm - Tuesday April 20, 6213

የባንዲራው ኮኮብ ምንድነው⁉️ (ፍቅሩ አበበ)

የባንዲራው ኮኮብ ምንድነው⁉
ፍቅሩ አበበ
• ባንዲራችን ላይ ስላለው ኮኮብ ማወቅ ከፈለጉ ሁላችሁም ትኩረት ሰታችሁ አንቡት።
•️ ይህ ኮኮብ pentagram ይባላል ። ባለ 5 ጫፎች እንደ ማለት ነው ፡፡ ይህን ኮኮብ ጥንታዊ ባቢሎን እና ግሪክ ለሰይጣናዊ አምልኮ ይጠቀሙበት ነበር ፡፡ አሁንም ይህን ኮኮብ መተተኞች ይጠቀሙበታል ፡፡ በዘመናዊ አለም freemasonry ወይም illuminitism የተባሉ ማኅበረ – ሳጥናኤል ለአምልኮት ይጠቀሙበታል ፡፡
በዮሐንስ ራዕይ 15 ÷ 9 ላይ ‹ የቀደመው ሰይጣን እና ዳቢሎስ ታላቁ ዘንዶ ወደ ምድር ተጣለ ….› በማለት አስቀድሞ ተነግሯል ፡፡ ታላቁ ዘንዶ የዚህ ዓለም ገዥ የዘመኑን ፍጻሜ በመረዳት ለእሱ ፍቃድ በተገዙ ሰዎች ላይ በማደር የርኩሰት አምልኮውን በገሃድ እያስደረገ ነው ፡፡
•️ የዚህ ኮኮብ ምስል የፍየል ፊት ወይም የሳጥናኤል ገጽ አለው ፡፡ ስዕሉን በትክክል ተመልከቱ ፡፡ ሁለት ቀንድ ፣ ሁለት ጀሮ እና አንድ አጋጭ አለው ፡፡ ሲሳል ረቂቅ በሆነ ዘዴ ነው ፡፡ በግልጽ አማርኛ ከሰንደቃችን ላይ የሳጥናኤል ምስል ተለጥፎ እየተሰገደበት ነው ፡፡ በኢትዮጲያ ምድር የሳጥናኤል ምስል ተሰቅሎ መመለክ የዘመኑን ፍጻሜ ያመለክታል ፡፡ እንግዲህ የተኛህ ንቃ !
ኮኮብ በየትኛውም መስፈርት ፣ በየትኛውም ሳይንስ ፣ በየትኛውም ሃገር እኩልነትን በፍጹም አይገልጽም ፡አራት ነጥብ ፡እንዲህ ማለት ሃገርን እና ሕዝብን መዋሸት ነው ፡፡ ግለሰብን ማታለል ይቻላል፡፡ሕዝብን ግን በፍጹም ፡፡
️• google ላይ በመግባት pentagram ብላችሁ ፈልጉት ፡፡እውነታውን ትረዳላችሁ ፡፡
በየትኛውም ሃገር እና ሳይንስ እርግብ ሰላምን ፣ ሚዛን እኩልነትን ፣ ኮኮብ ሰይጣናዊ አምልኮን ፣ የበላይነትን እና ማኅበረ -ሳጥናኤል መሆንን ይገልጻል ፡፡
• ኢትዮጲያን በ 7500 ዓመታት ውስጥ 327 መሪዎች መርተዋታል ፡፡ እንደ መታደል ሆኖ ከአባታችን ኖህ ተቀብለው ለእኛ ያስተላለፉልን ሰንደቅ አረንጓዴ ፣ ቢጫ እና ቀይን ብቻ ነው ፡፡ ከእነዚህ ቀለሞች ውጭ ሌላ ኮተት መጠቀም ታሪክን ማበላሸት እና ሃገርን መሸጥ ነው ፡፡
️• አባቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው በሰጡን ሰንደቅ ላይ ኮተት መጨመር አጥንታቸው ይፋረደናል ፡፡ አምላክም ይጠይቀናል ፡፡ አምላክን መሸጥ ነው ፡፡ ህሊናንም መሸጥ ነው ፡፡
የሚያሳዝነው ጭንቅላታቸው እንደ ኮምፒውተር ዳወንሎድ በማድረግ ውሸት እንደ ሙዚቃ የሚያቀነቅኑ ግለሰቦች ኮኮቡ የእኛ አይደለም ሲባሉ እናታቸውን የገደልክባቸው ያክል ያለቅሳሉ ፡፡ አትፍረዱባቸው ሆዳቸው አምላካቸው ነውና ፡፡ በመዝሙረ ዳዊት 18÷26 እነዚህን ሰዎች እንዲህ ይላቸዋል ‹ ከጠማማ ጋር ጠማማ ትሆናለህ ….›› ይላል ፡፡ በራሳቸው ህሊና የማይመሩ የተናገራቸውን ብቻ እንደ ውሻ የሚተገብሩ ፣ ዐይን እያላቸው የማይመለከቱ ፣ አፍ እያላቸው የማይናገሩ አካል ብቻ የያዙ በምድር ላይ በቁማቸው የሞቱ ፤ በሰማይ ቤት የገሃነም ባለ ርስቶች ናቸው ፡፡ በእውነት እናልቅስላቸው ፡፡
•️በየቢሮው እና በየቦታው ባለ ኮኮቡ ባንዲራ ሳይሰቀል ሲቀር ፌዴራል ፖሊስ የሚደበድብ የሚመስለው ፣ የመለስን ፎቶ እንደ አንጠልጥሎ ሰላሙን እና ደህንነቱን 100 ፐርሰንት ያረጋገጠ የሚመስለው ስንት የአእምሮ ድሃ በአጠገባችን እንደ አሸን ሰፍረዋል ፡፡ እነዚህ ሰዎች ከነፈሰው ጋር የሚነፍሱ ያመኑት መንግስት ዘንበል ሲል ወደ ሌላ የሚያዘነብሉ የቀን ጅቦች ናቸው ፡፡ ምክንያቱም አቋም የሌለው ሰው መተኛት እንጅ መራመድ አይችልም ፡፡ ማሳመን አይችልም ፡፡ መናገር አይችልም ፡፡ ባዶ  ቀፎ ነው ፡፡
• በሰንሰቅ ዓላማው ላይ ያለው ኮኮብ እንደ ሚነሳ እና ሌሎች አንቀጾች እንደ ሚሻሻሉ ረቂቅ ሕገ መንግስት እየወጣ ነው ፡፡ 27 ዓመት ኮኮብ የህዝቦችን እኩልነት ገላጭ ነው እያሉ ሲሰብኩ የነበሩት ተጎታቾች – በቀቀኖች ምን ይሉ ይሆን ? በነገራችን ላይ ሕዝብ በፈለገው ይመራል እንጂ ፣ መንግስት በፈለገው አይመራም ፡፡
‼- ለ27 ዓመታት በውሸት ራሳችሁን እና ቤተሰባችሁን ስታስተዳድሩ የኖራችሁ ዘመነኞች ንስሐ ግቡ – ነገ አፈር ናችሁ ፡፡
ዛሬ በሰረቃችሁት ገንዘብ መለወጣችሁን አትመልከቱ ፣ ነገ አፈር ናችሁ ፡፡ይህ ህዝብ አያውቅም አትበሉ ያውቃል ፡፡እውነት እላችኋለው ነገ የገሃነም ሙሽሮች ናችሁ ፡፡
በሁለት ካሪያ የምትመገቡ የሃይማኖት አባቶች በአንድ ካሪያ ብቻ ብሉ ፡፡ ባለኮኮቡን ባንዲራ ቤተክርስቲያን ላይ የምትሰቅሉ ፣ የሰቀላችሁ እውነት እግዚአብሔር ይቅር ይላችሁ ይሆን ? ለጉድ የተፈጠራችሁ ናችሁ እኮ ፡፡
🇪🇹ይህን ጽሑፍ ፖለቲካ ነው ብትሉ ትችላላችሁ ፡፡ የተቀረጻችሁት በጠማማ ሚዛን ነውና ፡፡  ሕዝብ ሲኖር ሃይማኖት አለ ፡፡ ህዝብ አልባ ሃይማኖት የለም ፡፡  ስለዚህ የህዝቤ ስሜት የእኔም ነው ፡፡ ሕዝቤ ሲራብ እኔም ይርበኛል ፡፡ ሕዝቤ ሲያለቅስ እኔም አለቅሳለሁ ፡፡ ሲደሰትም እደሰታለሁ ፡፡ግለሰብ እና መንግስት ይሳሰታል እንጅ ህዝብ አይሳሳትም ፡፡ በኦሮሞ እና በአማራ ክፍለ ሃገራት ትክክለኛውን ሰንደቅ ሲያውለበልቡ አልተሳሳቱም ፡፡ ተሳስቶ የነበረው መንግስት ነው ፡፡ ይህ ህዝብ ፤ለሆዱ ሳይሆን ለህሊናው ሟች መሆኑን አውቀናል ፡፡ እውነትም ኢትዮጲያዊ ናቸው ፡
Filed in: Amharic