>

አሁንም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ!! " ፍትሕ ለድሬዳዋ!"  (ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ)

አሁንም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ!!
 ” ፍትሕ ለድሬዳዋ!” 
ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ
 
#ከዚህ በኃላ ከሚኖሮት የሕዝብ መድረክ ቅድሚያውን የድሬዳዋን ሕዝብ ማወያየት ይሁን። እስከዛሬም ወደ ድሬዳዋ አለመሄዶት ጥያቄ እንዳጫረብኝ ልደብቆት አልፈልግም።
#ውይይቱን ከመጀመሮ በፊት ህውሓት/ኢህአዴግ ሆን ብሎ በታቀደና በተጠና መንገድ ድሬደዋን ለማጥፋት ለወሰዳቸው እርምጃዎች በይፉ እውቅና ይስጡ።
#ውይይቱን ከመጀመሮ በፊት በአባይ ፀሐዬ ቀማሪነት በመለስ ዜናዊ ይሁንታ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ የሆነውን “የድሬደዋ ቻርተር” በተሰብሳቢው ዘንድ ቀዳደው ይጣሉ። በቻርተሩ የተደራጀውን ከላይ እስከ ታች የተደራጀ ምክር ቤትና አስፈፃሚ ያፍርሱ። በፉንታው ” የድሬደዋ የሽግግር መንግስት” አሊያም በቴክኖክራቶች በጊዚያዊነት የሚተዳደር ” ባለ አደራ አስተዳደር” ይመስርቱ።
#ውይይቱን ከመጀመሮ በፊት 40 -40 -20 በሚል ቀመር የተዋቀረውን ” የድሬደዋ ህፃናት ፓርላማ” በይፉ ያፍርሱ። በኢህአዴግ ሊቀመንበርነቶ ድርጅቶህ እንዲህ አይነት ለትውልድ የሚተላለፍ አደገኛ መርዝ በመርጨቱ የድሬደዋ ህፃናትን ይቅርታ ይጠይቁ። አደረጃጀቱ ለወደፊቱ ሊፈጥረው የነበረውን የክፉት ግድግዳ ህፃናቱን በመሰብሰብ ያስተምሩ።
#NB:  40 -40 -20 ማለት ምን ማለት ነው?
በድሬደዋ ውስጥ በአባይ ፀሀዬ ቀማሪነት በሁሉም መስክ እንዲተገበር የተፈጠረ እጅግ በጣም አደገኛ አሰራር ነው። መቶ ፍላጐት(አቅርቦት) ቢኖር 40 ኦሮሞ፣ 40 ሶማሌ፣ 20 የተቀሩት ብሔረሰቦች የሚመረጡበት አካሄድ ነው። ይሄ መርዘኛ አሰራር በተራዘመ ሂደት ቢያንስ ሶስት አደገኛ ውጤቶች ይኖሩታል። አንደኛው የግዳጅ ማንነት ቅየራ( ፎርስድ አሲሚሌሽን)፣ ሁለተኛው የዘር ማጥፋት ወንጀልና ሶስተኛው የዘር ሽኩቻ(40:40 የሆኑት) ላይ ይፈጠራል። በተግባርም እየሆነ ያለው ይሄ ነው። ለምሳሌ የመንግስት ቢሮክራሲው አዲስ ሰራተኛ የሚቀጥረው በዚህ ቀመር ነው። በሌላ አነጋገር ቅጥሩ በዚህ መልኩ ከቀጠለ የዛሬ 25 አመት ከመንግስት ሰራተኛ ውስጥ 40 በመቶ ኦሮሞ፣ 40 በመቶ ሶማሌ ይሆናል። የተቀሩት 83 ብሔረሰቦች ተደምረው(አማራ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ፣ ሃረሬ፣ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ አፋር፣…ወዘተ) ድርሻቸው 20 በመቶ ብቻ ይሆናል። እጅግ የሚያመው ቀመሩ የጉልት መሬት ተከራይተው የእለት ሸቀጦችን ለመቸርቸር እንኳን የሚሰራ መሆኑን መስማት ነው።
( #ማስታወሻ:  ጉዳዩን የበለጠ ለመረዳት በኢሳት “የህሊና ፍርድ” ፕሮግራም ላይ የቀድሞ በድሬደዋ የኢህአዴግ ቢሮ የምሁራን አደረጃጀት ኃላፊ ከነበረው ሙልጌታ እና የድሬደዋ ተወላጅ ከሆነው ዶክተር ሰለሞን ጋር ያደረኩትን ውይይት ይመልከቱ። ” ፍትሕ ለድሬዳዋ!” )
Filed in: Amharic