>

ስለ አብይ አህመድ ያልተነገረ ታሪክ! (ተስፋየ ገብረአብ)

ስለ አብይ አህመድ ያልተነገረ ታሪክ!
ከተስፋየ ገብረአብ
አብይ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት መካፈሉ ይታወቃል። ምስጢር አይደለም። በጦርነቱ ወቅት የRDF ባለሙያ ነበር ይባላል።( radio direction finder) ማለትም የኤርትራ የጦርሜዳ ራዲዮኖችን ነበር የሚከታተለው።
ምናልባትም አብይ የኤርትራን ትግርኛ የቻለው በዚህ ምክንያት ሊሆን ይችላል። በትግራይ ትግርኛ “አሁን” ማለት “ሕዚ” ነው። በኤርትራ ትግርኛ ግን “ሕጂ” ነው። አብይ ሲናገር “ሕጂ” እያለ ነበር።
የሆነው ሆኖ ላእላይ ዴዳ በሚባል ቦታ አብይ በግዳጅ ላይ ሳለ ከኤርትራ የተተኮሰ የመድፍ ቁምቡላ መጥቶ አብይ የነበረባት መኪና ላይ አረፈ። የአብይ team ስምንት ነበሩ። ሰባቱ ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ አብይ ምንም ሳይሆን ተረፈ።
ይህን ታሪክ የነገረኝ ሰው በወቅቱ ኮሎኔል ሆኖ በቦታው የነበረው ገመቹ አያና ነው። ይህን ታሪክ እንድጽፍም ፈቅዶልኛል።
የአብይን ታሪክ በሰማሁ ቁጥር መገረሜ እየጨመረ ይሄዳል። በተአምራት አላምንም። የአብይና የለማ መገርሳ ነገር አጋጣሚ ብቻ ነው ብዬ ለመደምደም ግን እቸገራለሁ።
(ከታች የምትመለከቱት ፎቶ – አብይ በጦርነቱ ወቅት።)
Filed in: Amharic