>

ለትውልዱ ቅንጣት ሃላፊነት ቢሰማቸዉ ኖሮ..... (እስራኤል ሶቦቃ)

ለትውልዱ ቅንጣት ሃላፊነት ቢሰማቸዉ ኖሮ…..
እስራኤል ሶቦቃ
ከጥቂት ቀናት በፊት ዳንኤል ብርሃኔና ኣንዳንድ የወያኔ ጦማሪያን ኢትዮጵያና የኣካባቢዉ ሃገሮች ከሰላም ለማትረፍ የጀመሩትን የምስራቅ ኣፍሪካ የለዉጥ ጉዞ ለመቃወም ምክንያት ሲያጡ “…ኤርትራዉያን ከናንተ ይልቅ ለኛ ይቀርባሉ”.. ከኤርትራ ጋር ከሚደረገዉ የሰላም ጉዞ ይበልጥ የምንጠቀመዉ እኛ ነን በማለት በገጹ ላይ ያሰፈረዉ ጽሁፍ መልካም ነበር። ወያኔ ከሰላም ለመጠቀም ፍላጎት ማሳየቷ የሚደገፍ ነዉና።
ይሄዉ ሰዉ ዛሬ አስመራ ላይ የታየዉ የህዝብ ፍቅር የቆየ በሽታዉን ክፉኛ ሲቀሰቅስበት “የሰላም ጉዞዉ በወያኔ ላይ የተቃጣ ከበባ ነዉ” የሚል ኣዲስ ነጠላ የሙሾ ዜማ በመልቀቅ እየየዉን እያቀለጠው ነው። ሰሞኑን ከወያኔ መደመሩን ሚያወሳው ሌላኛው  ክላንድስታይን ወያኔ በላቀው የፓለቲካ ጥበቡ በተአምር የተከስተለትንና የትኛው ድርጅት የኦሮሞ ህዝብ ድጋፍ እንዳለው ካካሄደው ወያኔዊ የፖለቲካ ጥበብ ቀድቶ ትንሽ አቀመሰን።
ወያኔዎች ለሁለት ከተሰነጠቁ ወዲህ በየቲቪው የሚሰማዉ፤ ለቅሶ፤ ወቀሳና ዛቻ በኢትዮጵያ የተጀመረዉን የሰላምና የዲሞክራሲ መንገድ የሚቃወመው ኣርጌው የወያኔ ሙሰኛ ቡድን
መሆኑ ይታወቃል።
ይህን ፋሽስታዊ ቡድን የተጠናወተው የጂኒ መንፈስ ደም ለማፋሰሰ በሀገሪቷ ዉስጥ ከዳር እስከ ዳር የሚያደርገዉን መቅበዝበዝ መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በኣንክሮና በትዝብት እየተመለከተዉ ነዉ።
የለዉጡን መንገድ የሚደግፈዉና ድምጽ ኣልባዉ ወያኔና የትግራይ ኤሊት ባብዛኛዉ ዝምታን ቢመርጥም የለዉጡን መንገድ በመደገፍና በኢትዮጵያ ዉስጥ የዲሞክራሲን ስርአት ለማስፈን በሚደረገዉ የሰላም ጥረት የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ ለማበርከት በርካታ የትግራይ ኤሊቶች ከለዉጥ ጉዞው ጋር ተቀላቅለዋል።
ለዉጡ እነርሱ ከሚጠብቁት በላይ በመፍጠን ጥሎዋቸው ቢጉዋዝም የዳንኤል ብርሃኔና የኣለቆቹ ለቅሶ ግን ቀጥሏል።
የሚያሳዝነዉ ግን ወጣቱ ጦማሪ የራሱንና የትዉልዱን ብሩህ የተስፋ ጉዞና መጻኢ እድል
በኣገዛዝ ዘመናቸዉ ሚሊዮኖችን የረሸኑ፤ አስረዉ ባሰቃዩ አሮጌ ፋሽስቶች እጅ ኣሳልፎ መስጠቱ ነው።
ግን ለመሆኑ ዳንኤል ብርሃኔና ወጣቶቹ ወያኔዎች ለራሳቸዉና ለትውልዳቸው ሃላፊነት ኣይሰማቸዉም?
Filed in: Amharic