ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ
በባለፈው ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በኦህዴድ ሲሸለሙ እኔ የተሰጠኝ ያህል ነበር ደስ ያለኝ።እናም እታች ያለችውን ቪዲዮ አያይዤ ደስታየን ገለጽኩ።
* ይህንን ያረኩት ከኢህአዴግ ጋር ሆነው ስላልበደሉኝ አይደለም።
* ወይም ከመጀመሪያው የህወሃት ህገ መንግስት ሲወጣ አብረው ስላላጸደቁም አይደለም ።
* ከህወሀት በላይ ህወሀት ሆነው ሲያቆስሉን እንደነበሩም ዘንግቼ አይደለም።
በቃ ሰው ይሳሳታል ከስህተቱ ደግሞ ተምሮ ፓርላማን ረግጦ እስከወጣ ይቅር ይባላልና ይህንን በማሰብ እኔም ክብር ሰጠሁ።
ይሄው አክብሮቴ ሳይጎልባቸው /ሳናጎልባቸው /ጭራሽ ኮከባማ ባንዲራ ስላልያዛችሁ ህግ ጥሳችኋል ይሉናል።ያወጡት ህግ ለራሳቸው ሳይበጃቸው።
ሁኔታቸው ግን ይህን የፕሮፌሰሩን “ውቃቤ የራቀው ትውልድ” ነበር እንዴ እንድል አስደፍሮኛል።