>
5:13 pm - Saturday April 20, 1850

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የማረሚያ ቤት አመራሮችን ከሃላፊነት አነሳ

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የማረሚያ ቤት አመራሮችን ከሃላፊነት አነሳ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የማረሚያ ቤት አመራሮችን ከሃላፊነት በማንሳት አዳዲስ አመራሮች መሾማቸውን ገለፀ።
የማረሚያ ቤት አስተዳደር ህገ መንግስታዊ ግዴታውን በተገቢው ሁኔታ መወጣት ባለመቻሉ እና ሰብዓዊ መብቶችን ከማክበር አንጻር ሰፊ ክፍተት በመኖሩ ለውጥ መደረጉን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጿል።
ቀደም ሲል የነበሩትን አመራሮች በማንሳት አዳዲስ አመራሮች መመደባቸውንም ነው ያስታወቀው።
በዚህም መሰረት ጀማል አባሱ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲሾሙ  ረዳት ኮሚሽነር ያረጋል አደመ፣ ኮማንደር ወንድሙ ጫላ፣ ኮማንደር ሙላቱ ዓለሙ እና ኮማንደር ደስታ አስመላሽ በምክትል ዋና ዳይሬክተርነት ተሹመዋል።
አዳዲሶቹ አመራሮችም የሚነሱ ቅሬታዎችን በመፍታት በህገ መንግስቱ የሰፈሩ ሰብዓዊ መብቶችን እና ህጎችን ባከበረ መልኩ እንዲሰሩ መመሪያ እንደተሰጠም ተመልክቷል።
አመራሮቹ ከሃላፊነት የተነሱት የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍና ህገመንግስቱን ለማስከበር በማሰብ መሆኑም ነው የተገለፀው።
ህግ የጣሱ አካላት ማጣራት እየተደረገባቸው ወደ ፍትህ እንደሚቀርቡም ጠቅላይ አቃቤ ህግ ገልጿል።
በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ላይ እየደረሱ ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ጣቢያችን ዜናዎች መስራቱ ይታወሳል።
በወቅቱም ታራሚዎቹ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደተፈጸመባቸውና መንግስት ጉዳዩን እንዲመለከተው መጠየቃቸውም የሚታወስ ነው።
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የማረሚያ ቤት አመራሮችን ከኃላፊነት አነሳ፡፡
ባሕርዳር ፡ሰኔ 27/2010 ዓ/ም (አብመድ) እርምጃዉ የተወሰደውም በታራሚዎች አያያዝ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍና ህገመንግስቱን ለማስከበር ነዉ ተብሏል፡፡
ማረሚያ ቤቶች ታራሚዎችን ተቀብሎ የመጠበቅ፣ የአስተሳሰብና የስነምግባር ለውጥ እንዲያመጡ የመስራት እና አምራች ዜጋ እንዲሆኑ የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው፡፡
የፌደራል አቃቢ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ የማረሚያ ቤት አስተዳደር ህገ መንግስታዊ ግዴታውን ባለመወጣቱ እርምጃ መዉሰዱን ለኢቢሲ አስታውቀዋል፡፡ አመራሮቹ ከኃላፊነት የተነሱት የማረም እና የማነፅ  እንዲሁም ሰብአዊ መብቶችን የማክበር ችግሮች በመኖራቸው መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
አቃቢ ህጉ እንዳሉት አዲስ የተመደቡት የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አመራሮች ዋና ትኩረቱ በዜጎች የሚነሱ ቅሬታዎችን መፍታትና በህገ መንግስቱ የሰፈሩትን የሰብአዊ መብቶችና ሌሎች ህጎች ባከበረ መልኩ መስራት ይሆናል፡፡
 ከዚህ በፊት ህግ የጣሱ አካላትም ጉዳያቸዉ ተጣርቶ ወደ ፍትህ እንደሚቀርቡም አስታውቀዋል፡፡
Filed in: Amharic