>
5:13 pm - Thursday April 19, 9123

የኢትዮጵያን የለውጥ ግስጋሴ ለማደናቀግ ህወሀትና  የሱዳኑ አልበሽር በጋራ እየሰሩ (እያሴሩ) ነው!! (አዳነ አጣነው)

የኢትዮጵያን የለውጥ ግስጋሴ ለማደናቀግ ህወሀትና  የሱዳኑ አልበሽር በጋራ እየሰሩ (እያሴሩ) ነው!!
አዳነ አጣነው
አንዳድን ከሱዳን በኩል እርግጠኝነት ያልቸው መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደው ሰላማዊ ለውጥ  በበሽር የሚመራው መንግስት  ላይ  ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሯል፡፡ እንደሚታወቀው የበሽር መንግስት ከወያኔ ጋር እጅ እና ጓንት ሆኖ ለ27 አመት ከወያኔ ባልተናነሰ በኢትዮጵያን ላይ አስቃቂ ግፎችን ሲፈጽም መቆየቱ ይታወቃል፡፡
ሰሞኑን የሱዳን ወታደሮች አልፎ አልፎ በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ በገበሬዎች ላይ ተንኳዋሽ ተግባራትን ፈጽመዋል፡፡ከዚያም ባለፈ በመተከል በአጠቃላይ በተለይ ደግሞ አሶሳ ላይ የሚፈጸሙት የጎሳ ግጭቶች በዋናነት የሱዳን መንግስት እና የወያኔ የቅንብር ውጤት ናቸው፡፡
በመተከል አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ ጎሳዎች በአንድ ወቅት ሱዳኖች የነበሩ ሲሆኑን አሁንም ቢሆን ሱዳን ውስጥ ጉሙዝ እና በርታ እንዲሁም ሌሎች ጎሳዎች በሱዳን ግዛት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ሱዳን በኢትዮጵያ እና ሱዳን በጋራ የሚገኙ ጎሳዎችን  በመጠቀም በኢትዮጵያ መተከል ጠረፍ አካባቢ ችግሮችን የመፍጠር አቅምዋ ከፍተኛ ነው፡፡
ከአሁን በፊት ሱዳን አሰልጥና ያስታጠቀቸው የመተከልን አካባቢን ነጻነት ወይም ወደ ሱዳን እንዲጠቃለል የሚጠይቅ ነጻ አውጭ ድርጅት አደርጅታ መስርታ ነበር፡። በኻላም ሱዳን እና ወያኔ ባደረጉት ስምምነት ድርጅቱ ወደ መተከል ተመልሶ የመንግስት አስተዳደር አካል ሆኗል፡፡ ይህ ሱዳን ያደራጀው በኻላ ትጥቁን ፈቶ መተከል ውስጥ የመንግስት አባል የኾነው ቡድን አሁንም ቢሆን ከሱዳን መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት እንደጠበቀ ነው፡፡
በዚህ አጋጣሚ ለማንሳት ያኽል፡- አሁን መተከል ያሉ ጎሳዎች እንግሊዝ ሱዳንን በቀኝ ግዛት ከመያዝዋ በፊት “ፉንጅ”የሚባል እራሱን የቻለ የግሙዝ፣በርታ አና ሌሎችንም ጎሳዎች ያካተተ መንግስት ሱዳን ውስጥ ነበር፡፡በዛን ወቅት አሁን ሱዳን ውስጥ የምተገኘው የስናር ከተማ የኢትዮጵያ አካል የነበረች ሲሆን  ከፉንጅ መንግስት ጋር የኢትዮጵያ የወሰን ከተማ ነበረች፡፡  እኔ እራሴ ይህን የኢትዮጵያ ድንበር ስናር ነው የሚለውን እንዳአፈታሪክ ነበር የምቆጥረው፡፡ በቅርቡ አንድ ፓሮፌሰር ስለ ኢትዮ-ሱዳን ድንበር ሲያጠና  ከእንግሊዞች መረጃ ማግኘቱን እስኪነግረኝ ድረስ፡፡
የሱዳኑ የበሽር መንግስት ከወያኔ ጋር በማበር ሰሞኑን በሱዳን በስደተኝነት የሚኖሩ የወልቃይት ተወላጆችን 80 ሺህ ፓወንድ እየተከፈውላቸው “ትግሬዎች” ነን ብለው እንዲፈርሙ እያስገደደ ነው፡፡
የሱዳን ማእከላዊ ባንክ በወያኔ አና ሱዳን መንግስት ትእዛዝ  መሰረት የኢትዮጵያ የብር ኖቶች በገፍ ካርቱም ላይ እየታሙ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ይህ የብር ህትመት በኢትዮጵያ ውስጥ የዋጋ ጝሽበት ፈጥሮ የአብይ አስተዳደርን  ከህዝብ ጋር ለማቃቃር እና በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ተጽእኖ ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡
በአጭሩ የሱዳኑ የአልበሽር መንግስት ከወያኔ ጋር ወግኖ ኢትዮጵያን ወደ ማያልቅ የጎሳ ብጥብጥ እንድትገባ የተቻለውን ሁሉ እያደረገ ነው፡፡
Filed in: Amharic