>

ዶ/ር ዐቢይ በደስታ ጨረሰን እኮ!!! (ዘመድኩን በቀለ)

ኧረ ኡአኡ ከኢህአዴግ ጥይት የተረፍነውን ዶር ዐቢይ በደስታ ጨረሰን እኮ!!!
ዘመድኩን በቀለ
~ ተመልከት ዓላማህን ተከተል አለቃህን ነውና ዳይ ምን ትጠብቃላችሁ ደም  ለኢትዮጵያ ብለህ ቀይመስቀልን አጨናንቁት እንግዲህ። አከተመ።
~ ኢትዮጵያ ሆይ ከደም መጣጭ ወደ ደም ለጋሽ፤ ደም ከሚያፈስ መሪ ደም ወደሚለግስ መሪ ዘመን እንኳን በሰላም አሸጋገረሽ። አያ ጅቦ ሰምተሃል።
~ አዲስ አበባ ~ አዱገነት ፣ ሸገር ማማ ኢትዮጵያዬ እያየሽልኝ ነው አይደል ይኼንን ተአምር።
ይኽ ሰው ለኢትዮጵያችን ቀደም ሲል ሕይወቱን ሊሰጣት ባድመ ደረስ ሔዶ በተአምር ተርፎ፣ የወንድሙን ልጅ ማሙሽን ግን ከጎኑ ተነጥቆ ቀብሮ ተመለሰ።
ይህ ሰው የአፍሪካውያን ወንድሞቹን ሞት ሊሞት ወዶና ፈቅዶ ሩዋንዳ ድረስ ሔዶ እዚያም በተአምር ተርፎ ጓደኞቹን ቀብሮ ወደ ሀገሩ ተመለሰ።
አሁን ደግሞ በእግዚአብሔር ፈቃድ የዚህችን የ3 ሺ ዘመን ታሪክ ባለቤት የሆነች ታላቅ ሀገር ለመምራት ዕድሉን ቢያገኝ አይናችን ያላየውን፣ ጆሮአችን ያልሰማውን የለቅድመ ሁኔታ ሁሉን በፍቅር ወዶ፣ አዋድዶ ፣ አፈቃቅሮ የታሰሩትንም ሁሉ ከድቅድቁ ወኅኒ አስፈትቶ፣ ነፃም አውጥቶ፣ ሞት የተፈረደባቸውን፣ ዕደፈሜ ልክም ይታሰሩ ዘንድ የተወሰነባቸውን ምህረት የሚገባችሁ ናችሁ ብሎ የሀገሪቷን አየር በምህረት፣ በይቅርታ ጠረን አወደው።
ሰኔ 16 / የቀን ጅቦቹ ራዕዩን በአጭር ሊያስቀሩና ሊቀጩት፣ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ሁሉ ህልምም ላይ አሲድ ሊቸልሱ ሴረኞች ወደ እሱ ቢገሰግሱም በፍቅሩ ያበዱት ኢትዮጵያውያን የእሱን ሞት እነሱ ሞተው እሱን ለኢትዮጵያ እንዲያበራ ሻማውን ዐቢይ ሊያጠፋው፣ ደግሞም ጭልም ድርግም ሊያደርገው ከመጣው ንፋስ ከማእበል ከአውሎው ታደጉት። እነሱ ሞተው ለዐቢይ ህይወታቸውን ሰጡት።
በሞት ጣር ተይዘው በሆስፒታል አልጋ ላይ ተኝተው የነበሩ ቁስለኞችም ዐቢይን አደራ፣ ህልሙን ራዕዩን አደራ እያሉ እስከወዲያኛው ላይመለሱ አሸለቡ።
አሁን ደግሞ ለቁስለኞቹ ደም አስፈለገ። ቀደም ሲል የቅዱስ ጊዮርጊስነ የስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ደም መስጠታቸው ተነገረ። እናም የደም ባንኩ ደም እፈልጋለሁ ማለቱ ተሰማ።ይኽን ጊዜ ነው ዶር ዐቢይ ቀደም ሲል ለኢትዮጵያ ህይወታቸውን ለመስጠት ወደ ባድመ እና ሩዋንዳ እንደሄዱት ሁሉ ፤ አሁን ደግሞ ለኢትዮጵያውያን ፣ ለእሱ የተወረወረውን የሞት ፈንጂ ላመከኑ ወገኖቹ ደሙን ሊሰጥ በሆስፒታል ተገኘ። ይኼ ከአዕምሮ በላይ ነው።
ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ ሀገሬ ሳይል፣ አንድም ቀን ኢትዮጵያዊነትን ሳይሰብክ፣ የታመመ ሳይጠይቅ፣ አደጋ በደረሰበት ሳይደርስ፣ የተጣሉ ብሔር ብሔረሰቦችን ሳያስታርቅ በሙሉ አፉ ሀገሬ ኢትዮጵያ ሳይል፣ #ሀገሪቱ እያለ በሩቅ ሲጠራት ቆይቶ በጊዜ ተጠራ።
ይኼ ክስተት ይኸው ከች አለላችኋ። መጨረሻውን ያሳምርለት እንጂ በቅርቡ ከኢትዮጵያ አልፎ መላ አፍሪካን በፍቅርና በትህትና ረፍርፎ ሳይጨርስ እንደማይቀር ይገመታል።
ደም ለሚፈልግ ደሙን፣ ሰላም ለሚፈልግ ሰላሙን፣ ፍቅር ለሚፈልግ ፍቅርን፣ በ3 ወር ውስጥ አከፋፈለ። ደግሞ እኮ አያልቅበት፣ አይደክመው፣ አይኮራ፣ ቀን የለበሰውን ቲሸርት እንደለበሰ ሻወር ልውሰድ ሳይል ማታ በየሆስፒታሉ እየዞረ የተጎዱትን ሲጠይቅ አመሸ።
እንግዲህ ምን እንላለን። ሰው ማለት ይኼ ነው ሰው የሆነ ነው ሰው የጠፋ ዕለት። እሱም ሙሉ ሰው የሚለውን ትርጉም በተሟላ መልኩ አሟልቶ በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘው እንደኔ እንደኔ ጠሚዶኮ ዐቢይ አህመድ ብቻ ነው። አከተመ ።
እኔ ኢትዮጵያ ታፈርስ እንደሆነ እንጂ እንደማትፈርስ ካረጋገጥኩ ቆየሁ። ከምር እውነቴን ነው።
ድልና ትንሣኤ ለኢትዮጵያ ሀገሬ !  ሞት ለጠላቶቿ በሙሉ ይሁን !  አሜን !  አሜን !  አሜን  !  አንድ ሚለየን ጊዜ ! ኢንዴዢያ ነው ።
Filed in: Amharic