>

ዶ/ር ዐብይን ከስልጣን ለማስወገድ አሲረዋል የተባሉት ካሳ ተክለብርሃን፣ ተቀዳ አለሙ እና አስቴር ማሞ ተጠሩ

ከብሔራዊ ጥቅም በተቃርኖ ቆመዋል የተባሉ፤ ሶስት አምባሳደሮች ሊጠሩ ነው

ሕገመንግስታዊ ሥርዓቱ ተከትለው ወደ ስልጣን በመጡት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አስተዳደር ላይ አሲረዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሶስት አምባሳደሮች ሊጠሩ መሆኑን ምንጮቻችን ገለፁ፡፡

በሴራ የተጠረጠሩት አምባሳደር ዶክተር ተቀዳ አለሙ በተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ ቋሚ መልክተኛ፣ በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ወ/ሮ አስቴር ማሞ እና በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ካሳ ተክለብርሃን ሲሆኑ፣ ግለሰቦቹ የሀገሪቷን ጥቅም በሚፃረር ሁኔታዎች ውስጥ ሴራ አድርገዋል ተብለው መጠርጠራቸውን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

በሕገመንግስታዊ ሥርዓቱን ተከትለው ወደ ሥልጣን የመጡትን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድን ከስልጣን ለማስወገድ ተንቀሳቅሰዋል ተብለው ከተጠርጠሩት መካከል፤ ወ/ሮ አስቴር ማሞ ኪራይ አንዳንድ የኦሕዴድ አባሎችን በማንቀሳቀስ፤ አቶ ካሳ ተክለብርሃን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጠላቶቻችን ጋር አብሮ እየሰሩ ነው በማለት በአደባባይ በመክሰስ እና ዶክተር ተቀዳ ዓለሙ ለውጡን በመቃወም ሕገወጥ እንቅስቃሴ በማድረጋቸው ተጠርጥረው ወደ ሀገር ቤት እንደሚጠሩ ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

በተያያዘ ዜናም፤ በቅርቡ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው የተሾሙት አቶ ያሬድ ዘሪሁን ባጋጠማቸው የጤና ችግር ምክንያት ለኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በግል ያቀረቡት የሥራ መልቀቂያ ጥያቄ ተቀባይነት በማግኘቱ በምትካቸው አቶ ዘይኑ ጀማል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ሆነው ተሹመዋል፡፡

ሰንደቅ ጋዜጣ የሰኔ 13, 2010 ዕትም

Filed in: Amharic