>

አፈጮሌው ኢህአዴግ የሰልፉን መርህ ቃል በመለወጥ “እኔን ለመደገፍ የተካሄደ ነው” ብሎ ፍቃድ ሰጥቷል?!? (የሰልፉ አስተባባሪዎች)

አፈጮሌው ኢህአዴግ የሰልፉን መርህ ቃል በመለወጥ “እኔን ለመደገፍ የተካሄደ ነው”  ብሎ ፍቃድ ሰጥቷል?!?

የሰልፉ አስተባባሪዎች

አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድን ለመደገፍ በአዲስ አበባ የተጠራው ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ፈቃድ ማግኘቱን አስተባባሪዎቹ ገለጹ።

ከአዲስ አበባ አስተዳደር የስብሰባ እና ሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ ሰጪ ቢሮ ይሁንታውን ያገኘው ይሄው ሰላማዊ ሰልፍ “ለውጥን እንደግፍ፣ ዴሞክራሲን እናበረታታ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ነው።

ይሁን እንጂ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ይህን በህዝብ አነሳሽነት እና በማህበራዊ ሚዲያ የተጠራውን ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ “እኔን ለመደገፍ የተካሄደ ነው” በሚል ሀሳቡን መጥለፉን እና ድርጂቱን ለመደገፍ የተጠራ ሰልፍ አስመስሎ መፍቀዱን አስተባባሪዎቹ አስታውቀዋል።

ሆኖም በሂደቱ ላይ የሚያስከትለው ችግር ባለመኖሩ ሰልፉ በዚሁም መሪ ቃል እንደሚካሄድ ተነግሯል።

Filed in: Amharic