>

የቅዳሜው ሰልፍ  ከምር የሚደረግ ከሆነ፤ ጥያቄ አለኝ?!? (ዘመድኩን በቀለ)

አዲስ አበባ፤ አዱ ገነት፣ ሸገር፣ ፊንፊኔ፣ በረራ፣ አብዮት አደባባይ ፣ መስቀል አደባባይ !። 
ከምርጫ 97 ወዲህ መስቀል አደባባይ ለመጀመሪያ ጊዜ ህዝብ ያለ አበል ሰልፍ ሊወጣ መዘጋጀቱን ባየሁ ጊዜ በእጅጉ ደስስ አለኝ። እናም ሰልፉ ከፓርቲ ተጽዕኖ ነፃ የሆነና የህዝብ የራሱ ስለሆነም ጥያቄ መጠየቅ አማረኝ። ጥያቄዬም የሚከተለው ነው።
~ በዕለቱ ሰልፈኛው በሰልፉ ላይ ይዞ፣ ለብሶ፣ ተቀብቶ፣ አሽብርቆ የሚወጣው የትኛውን ሰንደቅ ዓላማ ነው?
A፦ የጥንት የጠዋቱን የኢትዮጵያ ባንዲራ ነው? ማለትም [#ኮተት_አልባውን] ንፁሑን ሰንደቅ ዓላማ ? ወይስ 
B፦የህውሓት/ኢህአዴግ የፈጠራ ውጤትና ሟቹ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የፈጠረልንን ደንቃራ ባንዲ?
 ነው ወይ ማለቴ ነው።
ስለባንዲራዎቹ ግንዛቤ ይኖራችሁና ለምርጫ ይረዳችሁ ዘንድ ጥቆማ ቢጤ ልስጣችሁ።
ተመራጭ A ሰንደቅ ዓለማ:- ማለት ጥንታዊው የኢትዮጵያ ባንዲራ ነው።
– ይኽች ባንዲራ ቋረኛው ካሳ  በዘመነ መሳፍንት መኳንንቱ እንደ ቅርጫ ስጋ ተቀራምተዋት የነበረችውን የዛን ዘመኗን ኢትዮጵያ አሀዱአዊት እና ገናና ሀገር ለማድረግ ከሽፍትነት እስከ አጼነት ብሎም በመቅደላ በፍጹም ጀግንነት የወደቁላት..
– ይኽን ባንዲራ አንግቦ ነው ህዝቡ የንጉሱን ዱካ ተከትሎ ዓድዋ የዘመተው፤ የጥቁርን ህዝብ የሽንፈት ታሪክ በድል አድራጊነት የቀየረው
 – ይህው ባንዲራ ነው ዶጋሊ ላይ የተውለበለበው። ኦሜድላ ላይ የተኩነሰነሰው።
በኦጋዴን በካራማራም ላይ የተሰቀለው። ይኼ ባንዲራ ነው ባድመ ላይ በመቶሺዎች ሬሳ ላይ የተውለበለበው። ጠሚዶኮ ዐቢይ አህመድ ራሱ ቆሞ እያለቀሰ የሰቀለው። ይኼ ባንዲራ ነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጀርባው ላይ አዝሎ ኢትዮጵያን በመላው የዓለም ሀገራት አየር ላይ እያውለበለበ ሲያስተዋውቅ የሚውል የሚያድረው። ይኼን ባንዲራ ነው ነፍሳቸውን ይማረውና ሻለቃ አድማሴ ለመለስ ዜናዊና ለነጋሶ ጊዳዳ ፣ ለአባተ ኪሾም ቱ ምን አለ በሉኝ ይኽች ሰንደቅ ዓላማ ትወድቃለች ነገር ግን አይናችሁ እያየ ደግሞ ትነሳለች ብለው ትንቢት የተናገሩላት።
– “የአድዋን ድል በአል ወደ ትግራይ እንወስዳለን ” ብለው ህወሀታውያን እና ፍርፋሪ ለቃሚዎቻቸው በተነሱ ጊዜ መአህድ በጠራው የተቃውሞ ሰልፍ አክቲቪስትና የሰብአዊ መብት ተከራካሪው ታማኝ በየነ መስቀል አደባባይ ከፍ አድርጎ ያውለበለባት ሰንደቅ ዓላማ።
ተመራጭ B ሰንደቅ ዓላማ ፦ ብዙም ታሪክ የለውም። ታሪኩም ከአውሬው ጋር የተያያዘ ነው። የ666 ምልክትም ነው። ባንዲራው በኢትዮጵያ ከተውለበለበ በኋላ የኢትዮጵያውያን ደም እንደ ግብር ሲፈስለት ፣ ሲጠጣ የከረመና የደለበ አጋንንታም በንዲራ ነው። ይኼ ባንዲራ ከመጣ በኋላ ነው በረከት ፣ ረድኤት ከምድሪቱ የራቀው። ይኼ ባንዲራ ከመጣ በኋላ ነው እርስ በርሳችን የተባላነው።  ባንዲራውን ቆሻሾች ይወዱታል። በጣም ያፈቅሩታል። መለስ ዜናዊ እንኳን በዚህ  ባንዲራ ነው ተጠቅልሎ ግብአተ መሬቱ የተፈጸመው። እናም ለምርጫ ያመቻችሁ ዘንድ የባንዲራዎቹ የህይወት ታሪክ በጥቂቱ ይህን ይመስላል።
~ የምርጫው ውጤት ማጭበርበር ቦታ የላቸውም። ሁሉ ነገር ሃላል ነው የመቀመጠው። ውጤቱን አህአዴግም፣ ተቃዋሚውም፣ ህዝቡም በግላጭ ነው የሚያዩት። ያለ ልዩነት ሁሉም ሰው ውጤቱን ይመለከተዋል። አከተመ።
ወይስ  B
በሉ አሁን ወደ ምርጫው! 
Filed in: Amharic