>

"ጸጉሬን እየነጩ  ‹‹አንተ ለዚህ መንግስት እንደዚህ ጸጉር ኢምንት ነህ›› እያሉ ተሳልቀውብኛል!!! ካፕቴን ማስረሻ ሰጠኝ 

“ጸጉሬን እየነጩ  ‹‹አንተ ለዚህ መንግስት እንደዚህ ጸጉር ኢምንት ነህ›› እያሉ ተሳልቀውብኛል!!!
ካፕቴን ማስረሻ ሰጠኝ 
በህዋሃት ትግሬዎች የሚፈጸሙ እና ለመስማት የሚዘገንኑ በአማራዎች ላይ የሚደረጉ ግፎች ዛሬም እንደቀጠሉ ናቸው። የዛሬው ተረኛ ደግሞ ጎጃም ተወልዶ ያደገው እና በድሬዳዋ የአየር ሃይል አብራሪ የነበረው መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጠኝ ነው። እየደረሰበት ያለው መከራ ይህ ነው!
“ስሜ ማስረሻ ሰጠኝ ነው። እድሜየ 34። የተወለድሁት ምስራቅ ጎጃም ነው። ትምህርቴን የተማርሁትም በተወለድሁበት አካባቢ ነው። እስከታሰርሁበት ጊዜ ድረስ ድሬዳዋ በሚገኘው የኢፌዴሪ አየር ኃይል በአብራሪነት እሰራ ነበር። የመኖሪያ አድራሻዬም እዚያው ድሬዳዋ ከተማ ነበር።
ለእስር የተዳረግሁበት ምክንያት፡- በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረሃል የሚል ነው፡፡
 በይፋ የተመሰረተብኝ የክስ አይነት፡- ቀደም ሲል የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁን አንቀጽ 7(1) መተላለፍ የሚል የሚል የሽብር ክስ እንዲሁም የመንግስትን ጦር መሳሪያ ይዞ መሰወር የሚል ክሶች ነበር የቀረቡብኝ፡፡ በእነዚህ ክሶች የአስር አመት ፍርደኛ ነኝ፡፡ አሁን ላይ ደግሞ በነሐሴ 2008 ዓ.ም ቂሊንጦ እስር ቤትን አቃጥላችኋል በሚል የሽብር ክስ ከቀረበባች እስረኞች መካከል አንደኛ ተከሳሽ አድርገው ከሰውኝ ከአሰቃቂ የእስረኛ አያያዝ በላይ ከግድያ ዛቻ አንስቶ ከባድ የስነ ልቦና ጉዳት አድርሰውብኛል፡፡
በእስር በምገኝበት ወቅት የሚከተሉት የመብት ጥሰቶች ተፈጽመውብኛል፡፡
ሀ. ማዕከላዊ ወንጅል ምርመራ እያለሁ
1. ቀዝቃዛና ጨለማ ክፍል ታስሬያለሁ፡፡
2. ጠያቂና የህግ ባለሙያ እንዳላናግር ተከልክየ ቆይቻለሁ፡፡
3. ስድብና ዛቻ ደርሶብኛል፡፡
4. ማታ ማታ ጭቃኔ የተሞላበት አሰቃቂ ሊባል የሚችል ምርመራ ተደርጎብኛል፡፡
ለ. በቂሊንጦ ቃጠሎ ክስ ምክንያት ሸዋሮቢት ለምርመራ በተወሰድሁባቸው ጊዜያት ብዙ መከራ ደርሶብኛል።
1. የግድያ ዛቻ ተሰንዝሮብኛል፡፡
2. ሲቪል በለበሱ መርማሪዎች በተደጋጋሚ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞብኛል፡፡
3. ሁለቱን የእጅ አውራ ጣቶቼን በሲባጎ አስረው አሰቃይተውኛል፡፡
4. ልንገድልህ ነው እያሉ በመዛት ሜዳ ላይ ወስደው ፊቴ እስኪያባብጥ ደብድበውኛል፡፡
5. ስድብ፣ ዛቻ፣ ማንቋሸሽ፣ የንቀት ንግግር አድርሰውብኛል፡፡
6. ቀንና ሌሊት በካቴና ታስሬያለሁ፡፡ በተለይ ማታ ማታ ከአልጋ ጋር ያስሩኝ ነበር፡፡
7. ጸጉሬን እየነጩ፣ የነጩትን ጸጉር እያሳዩ፣ ‹‹አንተ ለዚህ መንግስት እንደዚህ ጸጉር ኢምንት ነህ›› እያሉ ተሳልቀውብኛል፡፡
8. በግዳጅ እነሱ የሚፈልጉትን ብቻ እንድናገር እያደረጉ በቪዲዮ ቀርጸውኛል፡፡
9. ሽንት ቤት ጥንድ አድርገው በካቴና አጣምር ከሌላ እስረኛ ጋር በማሰር አብረን እንድሄድ አስገድደው፣ ክብረ ነክ በሆነ መልኩ አንዳችን ስንጸዳዳ ሌላችን ቆመን እንድናይ ተድርጌያለሁ፡፡
10. በግዳጅ የሰጠሁት ቃል ላይ ተገድጄ እንድፈርም ተደርጌያለሁ።”
*የህወሀት ሰዎች ጥላቻ የሰው ልጅ ከሚያስበው በላይ ነው! ከእነዚህ ሰዎች ጋር በአንዲት ሃገር መኖራችን ደግሞ የሚገርም ነው።
Filed in: Amharic