>
5:13 pm - Saturday April 19, 9208

በአንዳርጋቸው ጽጌ ላይ በሃሰት አልመሰክርም በማለቱ 11 ዓመት የተፈረደበት ወንድማገኝ አበበ ተፈታ!!! (ታማኝ በየነ)

ሰላም ለሁላችሁም
ያለአግባብ በግፍ ታስረው በምድራዊ ሴኦል ውስጥ የሰው ልጅ ይችለዋል የማይባል መከራን ተቀብለው ፈጣሪ የሰጣቸውን እድሜ በጨካኖች ተቀንሶባቸው እናቶቻቸው በመውለዳቸው ሲጸጸቱ ኖረው  ያለ ሃጢያታቸው ይሄን ሁሉ መከራን ተሸክመው በመጨረሻም ተፈቱ ሲባል” እንኳን ደስ አላችሁ” ለማለት ያመኛል:: ነገር ግን የመከራውን ቀን ያሳጠረውን አምላኬን አመሰግናለሁ!!!!!!!
ይሄ በእቅፌ ላይ የምታዩት ህጻን ማቲ አበበ ይባላል የዛሬ አራት ኣመት ወደ ሎንዶን በሄድኩበት ጊዜ በአንድ የቤተሰብ ምሽት ነው የተዋወኩት ::
ሳየው እንደ ልጆች አይስቅም አይጫወትም ለምንድን ነው ብየ እናቱን ስጠይቃት እሷና ባሏ( አበበ ወንድማገኝ) ከጋብቻቸው በኋላ ልጃቸውን ለቤተሰቦቻቸው ለማሳየት ወደ ኢትዮጵያ በሄዱበት ጊዜ አበበን “የግንቦት 7 “አባል ነህ በማለት በህጻን ልጁ ፊት እጁን ወደ ኋላ አስረው በፊቱ ላይ ቦንብ ደርድረው በቪዲዮ ከቀረጹት በኋላ እሱን ወደ ማእከላዊ ህጻኑን ማቲንና እናቱን ደግሞ ወደ እንግሊዝ ዲፖርት አደረጓቸው :: በመጨረሻም በአንዳርጋቸው ጽጌ ላይ መስክር ሲሉት በሃሰት አልመሰክርም በማለቱ የ11 ኣመት እስራት ፈረዱበት::
ዛሬ ወንድማገኝ አበበ መፈታቱን ሰማሁ ያኔ ማቲን ለማሳቅ ብዙ ቀልድና ብዙ ነገር ሞክሪያለሁ ዛሬ ግን ማቲ ለመሳቅ የእኔ ቀልድ ሳይሆን የአባቱን ፊት ብቻ ማየት ይበቃዋል። እስከዳርና ማቲ እግዚአብሄር እንኳን መከራችሁን አሳጠረው
ዛሬም ነገም ሁሌም እግዚአብሄር ይመስገን
– ህወሀት ወያኔ በሽብር ወንጀል ጠርጥሬዋለሁ በሎ በግፍ ያሰረውን አበበ ወንድማገኝን ቢፈታም ከቤተሰቡ ጋር ሊቀላቀል አልቻለም በዜግነት እንግሊዛዊ በመሆኑ ለኤምባሲ ነው የምናስረክበው እያለ ነው ።
– ሌላው
Filed in: Amharic