>
5:13 pm - Monday April 20, 4759

አላሙዲና ኢሳያስ (አርአያ ተስፋ ማርያም)

ጊዜው 1989 ዓ.ም ነው፤ የሻእቢያው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ በተደጋጋሚ ለአላሙዲ “አስመራ ለጉብኝት ና” እያሉ የጭቅጨቃ ያክል ሲወተውቱ ቆይተው በተጠቀሰው አመት ሼኹ አስመራ ይሄዳሉ። ..በማግስቱ አዲስ አበባ ሲመለሱ 5 የህወሀት ከፍተኛ የፖሊት ቢሮ አመራሮች ጋር ተገናኝተው ያወራሉ። አላሙዲ ሲናገሩ ” ከአንድ መሪ ጋር 3 ሰአት አውርቼ አላውቅም። በጣም ይጨንቃል! ኢሳያስ እየደጋገመ ‘ኢትዮጵያ በሙስና አያሰሩህም። እዚህ የሙስናም ሆነ የቢሮክራሲ ችግር አይገጥምህም። ወደብ አለን..ያለምንምን ክፍያ በነፃ መገልገል ትችላለህ። ኤርትራ ውስጥ ኢንቨስት አድርግ’ እያለ ተደጋጋሚ ጥያቄ አቀረበልኝ። ኢትዮጵያና ኤርትራ አንድ ቢሆኑ ይህን አደርግ ነበር። ነገር ግን ጥያቄዬውን መቀበል ያዳግተኛል..ስለው ተመልሶ ያንኑ ይጠይቀኛል። ሲጨንቀኝ ላስብበት አልኩት..በመጨረሻም ‘ኒያላ ሆቴልን ግዛን’ አለኝ። ለመገላገል ስል የ5 ሚሊዮን ዶላር ቼክ ፅፌ ሰጠሁት..” በማለት ለባለስልጣናቱ ነገሯቸው። በአመቱ ሻእቢያ አገራችንን ወረረ። አላሙዲ ተመልሰው አስመራ አልሄዱም፤ ገንዘቡም ቀልጦ ቀረ።
..ጦርነት ያወጁት ኢሳያስ ለአላሙዲ “የኢትዮጵያን መንግስት በገንዘብ እረዳለሁ፣ እጄን አስገባለሁ..” ካልክ ብለው የላኩትን የማስጠንቀቂያ መልእክት ለህወሀት ባለስልጣናት ተናገሩ። አላሙዲ ለመሰሪያ መግዣ ገንዘብ በመርዳት የኢሳያስን ዛቻ ከቁብ እንዳልቆጠሩት ያወቁት ኢሳያስ በሻእቢያ ሰላዮች እጃቸው ያስገቡትን ቪዲዮ ሳኡዲ አሳልፈው ቢሰጡም..ተቀባይነት አላገኙም። (ቪዲዮውን በተመለከተ ለህወሀት ባለስልጣናት ቢነግሯቸውም..ስለጉዳዩ ከመግለፅ እቆጠባለሁ)..በነገራችን ላይ ኢሳያስና መለስ ለአላሙዲ የነበራቸው አቋም (በ80ዋቹ አጋማሽ) ተቃራኒ ነበር…(ይህ መረጃ በ1997 ጥቅምት ወር በኢትኦጵ ጋዜጣ በዝርዝር የተዘገበ ሲሆን..በተጨማሪ ከ3 አመት በፊት አቶ ገብሩ አስራት ለንባብ ባበቁት መፅሀፍ ተፅፏል)
Filed in: Amharic