>

" ዛሬም ነገም ኢትዮጵያዊ ነን ዜግነታችን በ36 ቅል ራስ ፖለቲከኞች አይወሰንም!!!" (የኢሮብ ህዝብ) 

አለማ ተስፋዬ
የኢሮብ ህዝብ በመሬታችን ኣንደራደርም፣ የአልጀርስ ስምምናት የህልውናችን ፀር ስለሆነ በፍፁም ኣንቀበልም ስል ከተማውን ስያጥለቀልቅ ውሎዋል!! የኢሮብ ብሔረሰብ በወረዳ ኢሮብ ከተማ ደውሃን ደማቅ ሳላማዊ ሰልፍ አካሄደዋል፡፡
መሬታችን የብሄር ብሄረስቦች መቃብር ናት ! ስለዝህ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የልጆቹ መቃብር ለመጠበቅ ከ ኢሮብ ህዝብ ጎን መቆም አለበት ።
ታላቁ የኢሮብ ህዝብ በሰላማዊ ሰልፉ ካሰማቸው መፈክሮች የሚከተሉትን ይገኙበታል፡፡
1. “We don’t accept the disintegration of Irob!”
2. ‹‹የኢሮብ ብሔረሰብ ለሁለት አይከፈልም! አይከፈልም!››
3. ‹‹በደም ሰማእታት የተከበረው የኢሮብ ህዝብና መሬት በተሳሳተ ውሳኔ አይነጠቅም!››
4. ‹‹እኛ የኢሮብ ብሔረሰብ ኢትዮጵያዊነታችንን የሚቀይር ማንኛውም ውሳኔ አንቀበልም!››
5. ‹‹የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ በኢሮብ ህዝብ ማንነት ተጠያቂ ነው!››
ሚሊዮኖች ሂወታቸውን , ንብረታቸውና ሁሉም ነገራቸውን ያጡበት ከኢትዮ..ኤርትራ ጦርነት..ጋ የተያያዘው የአልጀርሱ ይግባኝ የሌለው የፍርድ ውሳኔን 36 ቅል እራሶች ብቻቸውን ውሳኔ ሰጡበት…!!!  ሰልፍ የወጡት ሰዎች ከ36 በላይ ናቸው የእነዚህን ሰዎች መብት የመወሰን ስልጣን አዲስ አበባ የተቀመጡ 36 ሰዎች አይደለም። በኛ በኢሮብች ከኛ ጋራ ሳይነጋገርና የአልጀርስ ውልና የሄግ ኮሚሽን ውሳኔ ተቀብሎ ከፋሽስቱ ኢሳያሳ ጋራ እደራደላለሁ የሚለን ድርጅት የኢሮብ ህዝብ ላይ “የዘር ማጥፋት ” ፍጅት እንደማወጅ ወይም እንደመፈጸም እንቆጠረዋለን! እኛ የኢሮብ ብሔረሰብ ኢትዮጵያዊነታችንን የሚቀይር ማንኛውም ውሳኔ አንቀበልም!
ዶክተር ዓቢይ የመለስን  የተሳሳተውን ውል ተቀብሎ ለመተግበር መወሰን የባሰ ስህተት ነው። መለስ ውሉን ሲፈርም ከተሳሳተ ዶር አብይ ስህተቱን ማረም  ስህተቱን በተግባር መፈፀም  የለበትም።
የኢትዮ ኤርትራ የድንበር ጉዳይ ቀደም ሲል ቅኝ ገዚዎች ራሳቸው ያፈረሱት ውል ሲሆን ከአልጀርስ ውል በሗላም ሻዕቢያ ራሱ ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ በመጣስ ያፈረሰው ስለሆነ ካሁን በፊት የተደረጉ ውሎች ሁሉ በአሁኑ ግዜ ተፈፃሚነት የላቸውም::
የሀገሩን ባለቤት የሆነውን ሰፊው ህዝብ በማግለል መሬትን የመሸንሸን እሽቅድድም በሀገርና በህዝብ ላይ ተጨማሪ ክሕደትና ወንጀል መፈፀም ነው::  የኢህኣዴግ ስራ ኣስፈፃሚ ኮሚቴ በኣልጀርስ ውል ላይ የወሰነው ውሳኔ የሃገር ክህደት ነው! የእፍኝ ኣፈር ንፉግ መሪ የወለደች ሃገር መሬት ቆርጦ መሸጥ ልማዱ ያደረገ ባንዳ እንዴት ልትፈጥር ቻለች?
 የአሮብ ህዝብና መሬት ጥንትም ዛሬም፣ ነገም ኢትዮጵያዊ ነው።
አዎ ክህደት ነው። ይሄ የሀገር ጉዳይ ነው። ኢህአዴግ እንደፈለገ አክሮባት የሚሰራበት አይደለም።
ስንት ደም ያፋሰሰ ውስብስብ የሆነውን የሀገራችን ሉዓላዊነት ጉዳይ በአንድ ፓለቲካዊ ድርጅት በጓዳ የሚወሰን አይደለም :: ጉዳዩ ከፓለቲካ ድርጅቶች እጅ ወጥቶ አግባብ ባላቸው የመንግስት አካላት አማካኝነት ለፓርላማ ቀርቦ ይፋ የሆነ ውይይት ሳይደረግበት በነ በረከት ስምዖንና በነ ስብሓት ነጋ አጃቢነት የሚወሰን አይደለም::
ይህ ህዝብ በፍቅሩ ጀግንነቱና ፅናቱ ስመለከት መገረሜ ሳይቀር ሰላማዊነቱ ሳይ ‘ተናነቀኝ እንባ’ ከማለት በላይ ምንም አልልም ። ኢትዮጵያ የሁላችን ናት፤ኢሮብን የምንረዳው በዚህ ግዜ ይሆናል።
Filed in: Amharic