>

ኢህአድግ የአልጄርስን ስምምነት እና አግአዚያኑ!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

የኢትዮጵያን ፖለቲካ በደንብ የሚተነትን ፅሁፍ ፈልጌ ፈልጌ ሳጣ የዛን ዘመን ዝሆኖችና የፖለቲካ ሊቆች ከሆኑት ውስጥ ጋሽ ሙሉጌታ ሉሌንና ጋሽ አሰፋ ጫቦን ክፉኛ እናፍቃለሁ።
ለመሆኑስ ይች አግአዚያን የምትባለው እንቅስቃሴ እንደ እፉዬ ገላና እንደ ጧት ጤዛ  ብን ብላ ጠፋች አይደለም።
እኔማ ተናግሬ ነበር የሚሰማኝ አጣሁ እንጅ እነዚህ ሁለት ህዝቦች እንኳን አብረው ሊኖሩ ይቅርና በፍርድ ቤት ውሳኔ እንኳን መስማማት አልቻሉም። ኢህአድግ የአልጄርስን ስምምነት እቀበላለሁ ብሎ መግለጫ ከማውጣቱ በፊት እነአግአዚያን የሚባሉት የቁጩ ቡድን “ባድመ ወደ ኤርትራ ቢሄድም ወደ ትግራይ ቢቀርም ሁለቱም የአግአዚያን አገር ስለሆነ ችግር የለውም ።” ሲሉን ነበር ። 🙂
ይሄው አሁን ህውሃት የፍርድ ቤት ውሳኔ አከብራለሁ ብሎ መግለጫ ሲያወጣ”  አንድ  ነን ” የሚሉት ተረሳና  በተቃውሞ እየቀወጡት ነው ።
እስኪ ዛሬ ስለኤርትራውያንና ትግሬዎች ያለውን የዘላለም ጥልና መናናቅ  የሚያሳይ ፅሁፍ ከጋሼ አሰፋ ጫቦ መፅሀፍ ልጥቀስ … …
<< በኢትዮጵያ ብሄሮች መካከል ቅራኔ የለም ። አንድት ብቻ ተገትራ የማትነቃነቅ ቅራኔ ያለው በትግሬና በኤርትራውያን ነው። ታሪካዊ መሰረትም አለው። ትግሬውንና ኤርትራውያኑን በአንድ ክፍል ፈፅሞ ማኖር አይቻልም። ውስብስብና ታሪካዊ በሆኑ ምክንያት በኤርትራና በትግራይ መካከል ቅራኔ አለ። ለዘመናት ከትግራይ ፈልሰው ወደ ኤርትራ የሚሄዱ ሰዎች  የመጨረሻውን ዝቅተኛ ስራ ሲሰሩ ኑረዋል።ይህም አስፀያፊና ንቀት የተሞላበት ስም እንድያገኙ አድርጓል። ለምሳሌ ለትግራይ ተወላጅ ” ወዲ አጋመ” መሆን የሚያኮራ ነው። ኤርትራዊ ግን አጋመ ሲል አፀያፊ ስድብ መሳደቡ ነው።… ረዘነ ትዝ ይለኛል ፣ ወይናይ ትዝ ይለኛል… …>> እያለ ይቀጥላል።
የትዝታ ፈለግ (ገፅ 36)
አሰፋ ጫቦ 
አሳታሚ ነባዳን የሚዲያ PLC
Filed in: Amharic