>
5:13 pm - Thursday April 19, 6446

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉድና ለምን እንደሚሸጥ (ET is in deep trouble too) (ሚኪ አምሀራ)

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምናልባትም በአለም ካሉት የኮርፖሬት ካምፓኒዎች ጥያቄ የጠየቁ ሰራተኞችን የሚቀጣበት የምድር እስርቤት ያለዉ ብቸኛዉ ካምፓኒ ሳያደርገዉ አይቀርም፡፡ በአየር መንገዱ አሰራር ላይ ጥያቄ ያነሳ ሰራተኛ በእቃ መጫኛ አንጋር አካባቢ ወደ ሚገኘዉ ቀዝቃዛ እስር ቤት ለሳምንታት ወይም ለወራት ልትታሰር ትችላለህ፡፡ ሴቶች ከሆኑ ደግሞ በዚህ እስር ቤት ጠባቂዎች የመደፈር ጉዳይ አለ፡፡ ብዙ ሰዉ ይህ ድርጅት አትራፊ ነዉ ለምን ይሸጣል ይላል፡፡ በርግጥ በአመት 50 ወይም 100 እስከ 200 ሚሊየን ዶላር አትርፎ ያዉቃል፡፡ ነገር ግን ከአሜሪካ ባንኮች፤ ከቻይና አግዚም ባንክና እና ከህንድ ባንክ የተበደረዉ ብድር የትእየለሌ ነዉ፡፡ ለራሱ ለድርጅቱ ብቻ ሳይሆን መንግስት በዚህ ድርጅት ሰበብ ለራሱ ይበደርበታል፡፡ አሁን  ላይ በየአመቱ መንግስት ከሚከፍለዉ የብድር እዳ 60% የአየር መንገዱን እዳ ይሸፍናል፡፡እስኪ ከብዙ ችግሮች ዉስጥ አንዱን ለምሳሌ ላንሳዉ፡፡
የአምስቱ የመጨረሻዎቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ B787 ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች የማኔጅመንቱ ድብቅ ቁማር
ANA (All Nippon Airways) በመባል የሚታወቀው የጃፖኑ አየር መንገድ ከቦይንግ ካዘዛቸው በርካታ ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች ውስጥ ቀድመው ተመርተው የነበሩት B787 ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች በነበራቸው የምርት ጥራት ችግር የዲዛይን ደረጃቸውን ስለማያሞሉ እና በዚሁም ምክንያት አውሮፕላኖቹ ምንም ሳይጭኑ ከባድ በመሆናቸው እና የጭነት መጠናቸው ዝቅተኛ በመሆኑ፣ የነዳጅ ፍጆታቸው ከፍተኛ በመሆኑ እና አጭር ርቀት ብቻ መብረር በመቻላቸው በመሳሰሉ ትክክለኛ ምክንያቶች ከቦይንግ አልወስድም ብሎ ስለተዋቸው ፈላጊ አተው ለበርካታ አመታት ቆመው ነበር። የኢት ማኔጅመንት ግን እኒህን 5 አዉሮፕላኖች በጥቅም ተደልሎ ተቀብሏቸዋል፡፡
በቦይንግ አሰራር መሰረት አዳዲስ አውሮፕላኖችን ለአየር መንገዶች ብቻ እንደሚሸጥ ይታወቃል። በዚህም መሰረት South America አካባቢ የሚገኝ አውሮፕላን ገዝቶ በማከራየት የሚታወቅ አንድ ካምፖኒ እነዚህን አውሮፕላኖች ከመግዛቱ በፊት በዚህ standard ማንም እንደማይከራየው ስለሚያውቅ እና በቀጥታ ቦይንግ ስለማይሸጥለት በድርድር የኢትዮጵያ አየር መንገድ እያንዳንዱን 90 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ ከቦይንግ እንዲገዛው ካደረገ በሆላ ይሄው ካምፖኒ ገንዘብ ጨምሮ ወደ 120 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ መልሶ በመግዛት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ25 አመታት በላይ አውሮፕላኑ እስኪያረጅ ድረስ ተከራይቶ እንዲያበርለት የሚያስገድድ ውል ከማኔጅመንቱ ጋር ይፈራረማል፡፡ይሄው ዛሬም ተዋረዱ ሲላቸው ከጅምሩ ጀምሮ በፋን ብሌድ ዝገት፣ በሞተር ዘይት መፍሰስ በመሳሰሉ አወዛጋቢ ችግሮች ሲገጥመው በቆየው የተገጠመለት Trent 1000 Rolls Royce ሞተር ችግር ምክንያት ፓርቱ እስኪገኝ ድረስ አራቱ አውሮፕላኖች እዳቸው እየተከፈለ ላልታወቀ ረጅም ጊዜ እንዳይበሩ ተደርገዋል። የዚህ አውሮፕላን የሊዝ ክፍያ በዶላር በወር 800,000 እስከ 1.25 ሚሊየን USD ድረስ ነው (በዚህች በደሀ ሀገር ላይ ይሄ ዶላር ምን ያህል ቁም ነገር ሊሰራ እንደሚችል ማሰብ ነው) ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሌሎቹ B787 ድሪም ላይነሮች የነዚህ የተበላሹ አውሮፕላኖች መስመርን ለመሸፈን ሲባል ለጥገና መግባት ከነበረባቸው ሰአት በላይ ሴፍቲን በሚፃረር ሁኔታ እየበረሩ ይገኛሉ። እነዚህን አውሮፕላኖች ጨምሮ Trent 1000 Rolls Royce ሞተር የተገጠመላቸው አውሮፕላኖች ሁሉ ሞተራቸው ላይ ያለው ችግር ያለበት ፖርት እስኪቀየር ድረስ አውሮፕላኖቹ በገናናዎቹ የአየር ደህንነት ተቆጣጣሪዎች እንዳይበሩ መታገዳቸው ይታወቃል። ከዚህም ጋር በተያያዘ ቀድሞ መፈረም የነበረበት ወረቀት CEO አቶ ተወልደ ቢሮ ሳይፈረም ሲገላበጥ ቆይቶ የሚፈለገው መለዋወጫ በጊዜ ሳይገዛ በመቅረቱ እና ሌሎች አየር መንገዶች ቀድመው ጠራርገው በመውሰዳቸው ፖርቱ መገኘት አልቻለም። ኪሳራውም በቀን 110,000 ዶላር በላይ ይገመታል ። በዚህም ምክንያት የአውሮፕላኖቹ መቆም የፈጠረው መዘዝ እና ንትርክ ምክንያት የአውሮፕላኖቹ የሽያጭ እና ሊዝ ሚስጢር ሊታወቅ ችሏል፡፡ይሄም ያለ ጥናት ችግራቸው እየታወቀ በ CEO ትእዛዝ በመገዛታቸው በቀጥታ የአየር መንገዱን CEO ተጠያቂ አድርጎቸዋል። በዚህ ንትርክ ዉስጥ ከአየር መንገዱ የሴኪዉሪቲ ቢሮ ፊት ለፊት የሆነዉ የአቶ መስፍን (COO) ቢሮ ተሰብሮ የእነዚህን አዉሮፕላን የቴክኒክ ጉዳዮች እና ሌሎች መረጃወችን እንዲሁም የሰዉየዉን ላፕቶፕ ተሰርቋል፡፡ይህ የሆነበት አንዱ ምክንያት አቶ መስፍን እኒህን ዶክመንቶች በጥንቃቄ የያዘ ሲሆን አቶ ተወልደ ችግሩን ለማዳፈንና የቴክኒካል ጉዳዮችን ያማከረኝ አቶ መስፍን ናቸዉ ለማለት እንደሆነ ይገመታል፡፡ከዚህም በላይ አየር መንገዱ ለዉጭ አብራሪዎች የሚከፍለዉ ከፍተኛ ገንዘብ ሌላኛዉ ወጪዉ ነዉ፡፡ ስለዚህም በአመት 100 ሚሊየን ዶላር ቢያተርፍም አየር መንገዱ ያለበት በቢሊየን ዶላር የሚቆጠር እዳ መንግስት ከሚሸከመዉ አቅም በላይ ሁኖበታል፡፡
በ2010 ገደማ የአሜሪካ ኤምባሲ የኢትዮጵያን መንግስት የአየር መንገዱንና የኢትዮ ቴሌኮምን በጀትና የብድር መጠን እንዲያሳዉ በተደጋጋሚ እንደጠየቀ ዊክሊክስ ላይ የተለቀቀዉ የኢ-ሜል መረጃ ያሳያል፡፡ በጊዜዉ የንግድ ሚኒስቴር የነበረዉን መኮነን ማንያዘዋልን ኤምባሲዉ ድረስ ጠርተዉ በአየር መንገዱ የብድር መጠን ላይ ጥርጣሬ ስላለን በጀቱን እንዲሰጣቸዉ ቢጠየቅም፡፡ የአየር መንገድ የፋይናንስ ጉዳይ ማንም አያዉቅም ስለዚህም መረጃ የለኝም የሚል መልስ እንደሰጣቸዉ ኤምባሲዉ ለስቴት ዲፓርትምንት የላከዉ ኢ-ሜል ያሳያል፡፡ የአሜሪካ መንግስት በአይ ኤም ኤፍና አለምባንክ በኩል ለኢትዮጵያ በሚሰጠዉ እርዳታ መንግስት የነዚህን ድርጅት በጀት ካላሳወቀ እንዲያዝ እንደሚያደርግ ገልጾ ነበር፡፡
cc// ANDM CC office ANRS Communication Affairs OfficeGedu Andargachew Nigussu Tilahun Addisu Arega Kitessa Office of the Prime Minister-Ethiopia
Filed in: Amharic