>

ብአዴን የወልቃይት እና የራያን ጉዳይ የሚያቀነቅኑትን ማስቆም ካልቻለ ፕላን ቢን እንጠቀማለን!!! -  ዶ/ር ደብረ ጽዮን

                                                                             የሰሜኑ ቋያ
በወቅታዊ የአገራችን ጉዳይ  ዙሪያ ከዶክተር  ደፂ  ጋር  ቃለ መጠይቅ  ተደርጎ ነበር  
  ቃለ መጠይቁ  እንድህ  ይላል
የኢህአዴግ  የግምገማ ውጤት  በትክክል  ተግባር ላይ እየዋለ ነወይ  ??
ዶክተሩ…  ከሞላ ጎደል አዎ
    በግምገማችን  መስረት  ህወሃትና ደቡብ  የተሻሉ ሲሆኑ  ብአዴንና ኦህደድ  ችግር  አለባቸው  አሁንም በተለይ ብአዴን የኢህአዴግን ውሳኔዎች እየጣስ ነው  ለምሳሌ  የወልቃይትንና  የራያን  ጉዳይ  የሚያቀነቅኑ  ስዎችን ቡድኖችን  ማስቆም  አልቻለም ይህ  ደግሞ  ትልቅ  አደጋ  ነው   ስለዚህ ብአዴን  አሁንም ይህንን ማስቆም አለበት  ካልሆነ አሁንም  ጉዳዩን  ለኢህአዴግ አቅርበን  እንድታይ እናደርጋለን  ይህም  ካልተቻለ  ግን  ሎሎች አማራጮችን  እንድንጠቀም እንገደዳለን ( ሌሎች አማራጭ  እንድንጠቀም እንገደዳለን )  የምትለዋ  ይስመርባት::
ጠያቂ… የኤርትራ  ጉዳይስ ??
ዶክተር …. ከኤርትራ  ጋር በሶስተኛ ወገን ድርድር ጀምረናል  ውጤታማ  እንደምንሆን  እርግጠኛ  ነኝ
………
የቋያ ዕይታ:-
ዶፍተርዬ.. በመጀመሪያ  ድሮውንም እርስዎ ብዙ  መናገር  የማይወዱ  ነገር ግን ከተናገሩ  ደግሞ  ነገርን መደበቅ  የማይችሉ  መሆነወትን ለሚያውቅ ስው  ይሄ  ሌሎች  አማራጮችን እንጠቀማለን አባባልዎትን  ለእኛ ጥሩ  ደወል ነችና እናመስግናለን
 ሁለተኛ  ድሮውንም ከምናውቀው  ልምዳችን አንድ  መልዕክት  ከመተላለፉ  በፊት  ሙቀትን መለካት  በሚለው አስራራችን መሰረት  እርስዎም  በአብርሃ ደስታ  አማካኝነት  ለጦርነት  እንዘጋጅ  በተስፋ ኪሮስ  አማካኝነት በብአዴንና በአማራ  ልንወረር ነው  ሁላችንም  በስነ  ልቦና  እንዘጋጅ  የዋልድባው ስኳር  ፋብሪካ  ወደ  አማራ ከሚሄድ  ብንዋጋ  ይሻለናል  የሚሉ  የሙቀት  መለኪዎች  ላነበበ  ስው  ቀጥሎ  ምን ሊመጣ  እንድሚችል  እንኳን  እኛ  ቀርቶ  ደቡብ ሱዳንም  ወይም  ኤርትራም  ጠንቅቃ  ታውቃለች::
 እናማ
  እኔ  የምመክረዎት
1– ሌላው  አማራጭ ያሉት  ጉዳይ
      ሀ- በህገ ወጥ  የሄደን  መሬት መመለስ
       ለ- ምንም በህገ ወጥ ቢሄድ  አሁን ግን በህገ
              መንግስቱ መሰረት  መፍታት
2- ብአዴንን የአማራን ህዝብ እፈኝልኝ ከማለት
      በጋራ  እንስራ  ህዝብ የሚለውን እንቀበል ማለት
    *  ከእነዚህ ውጭ  እሆናለሁ  ማለት  እና  አሽከሮችዎ  እንደሚፎክሩት  ነጋሪት  ከጎስሙ  ግን ለእርስዎም የዩሃንስን  ዕጣ  መድገም  ነው ለህዝብም  አይበጅም *
        አይ  እገፋበታለሁ   ካሉ   ግን  ከተሞክሮ   የሚማሩበት  ጊዜ እንዳማይኖረዎት አስረግጨ ስናገር  በዮሃንስ  እየማልኩ  ነው::
ሌላው ነገር ብአዴንስ አታሳዝነዎትም ??  ድሮስ የወልቃይትንና  የራያን  ጥያቄ  ያነሳ ታጋዯን ስታባርር ..ስታስር  .. ስታስገድል  ኖረች  አሁን ግን  ህዝቡ ይህን ጥያቄ  ሲያነሳ   ስንቱ  ታስሮ  ተገርፎ  ተገድሎ  ያልቆመውን እንደት  አድርጋ  ልታቆምልህ  ትፈልጋለህ ??
 ለእስካሁና  እናመስግናለን ለወደፊቱ  ደግሞ  ያውላችሁ  መሬታችሁ  አብረን  እንኑር   ማለት  ማንን ገደለ ??
ማረጋገጫ >> የወልቃይትንና የራያን  ጥያቄ   አይደለም ብአዴን ወይም ህወሃት ኢህአዴግ ቀርቶ  ማንም ምድራዊ  ሃይል  አያቆመውም  እንዳውም  ፕላን B ሌላ አማራጫችሁን  አ ፍ ጥ ኑ ትትትትት::::::::
  ጥያቄውን  የሚያስቆመው  የወልቃይትና የራያ  ህዝብ ከማንም  ቁሞ ቀር አንባገነን ነፃ  ሆኖ  በህገ መንግስቱ መስረት ሲወስን  ብቻና  ብቻ ነው አለቀ::
የኤርትራ ጉዳይ ..  አንችው ታመጭው አንችው ታሮጭው  ይላል የወንዜ ሰው
  በግሌ  ደስ ነው የሚለኝ  በስጥቶ መቀበል የጅል ብሂል ከምንጏዝ  የእነርሱን  ይውስዱ  እኛም በአስብ ወደብ የመጠቀም መብታችንን እናረጋግጥ  ይሄ የእልክና እኔ  ያልኩት  ብቻ  ይፈፀም አስተሳስባችሁን  ብትቀብሩት ጥሩ ነው እላለሁ!!
Filed in: Amharic