>
5:13 pm - Sunday April 20, 2273

ጀነራሎቹ እና የህወሀት ወታደራዊ ሳይንስ (የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት)

  በ1990/1991 ሁለተኛው የጭንቀት ጊዜ መጣ። ሻዕቢያ ባድመንና ሽራሮን ወረረ ተባለ። አዲሱ የኢፌዴሪ መከላከያ ሀይል ወራሪውን ከተያዙት ቦታዎች መነቅነቅ ተሳነው። በባድመ ግንባር የተደረገው ውጊያ በድል ቢጠናቀቅም በዚህ ግንባርና በጾረና ግንባር ብቻ ህወሓቶች ለ17 ዓመታት የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ ካጡት ሰው ጋር የሚስተካከል ሰራዊት አለቀ። ያለአቅማቸውና ያለአንዳች ወታደራዊ ሳይንስ“ጄኔራል”፣ “ኮሎኔል”፣“ሻለቃ” እየተባሉ የተሾሙት የቀድሞ ነፃ አውጪዎች ኮንቬንሽናል አርሚ መርተው ማዋጋት የማይችሉ ሆነው ተገኙ።ስለዚህ “የጨፍጫፊው ደርግ ጦር” ተብለው የተበተኑት የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ሀገር በማዳን ተግባር እንዲሳተፉ ጥሪ ተደረገላቸው። በፊት ይከፈላቸው ከነበረው በእጥፍ የሚበልጥ ደመወዝ ተቆረጠላቸው።በወቅቱ ሞዴል የነበሩ ኮብራ መኪና ታዘዘላቸው፡፡ ለዓመታት ትኩረት የተነፈገው የጡረታ መብታቸውም ተከበረላቸው። የቀድሞው ጦር አባላትም በዘመቻው ተሳትፈው ሰራዊቱን እየመሩ ሻዕቢያን በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ከሁሉም ግንባሮች አባረሩ። በዚህም ውትድርና ራሱን የቻለ ሳይንስ መሆኑ ተረጋገጠ።
.
በዚህ አጋጣሚ የሆነውን አንድ ክስተት ላውጋቹ
ቦታው ህወሀት አለኝ የሚለው እና የሚተማመንበትን 20ኛ ቃሉ ኮማንዶ ክ/ጦር ሙሉ በሙሉ የተደመሰሰበት እና በጣም አስቸጋሪ ፣ውግያው ከተፈጥሮ ጋር ጭምር የሆነባት የፆረና እገላ ግንባር ነው፡፡
.
 አስገራሚው ጉዳይ በዚህ አስቸጋሪ ግንባር  ምሽግ ሰባሪ ተደርጎ የተመደበው 18ኛ የተባለው ክ/ጦር ሙሉ በሙሉ ጥሪ በተደረገላቸው የቀድሞ ሰራዊት አባላት የተዋቀረ ነው
(አስቡት ህወሀት ወያኔ በ1990 የራሱን ልዩ ኮማንዶ በዚህ ግንባር አዝምቶ እንኳን ምሽግ ሊሰብር ራሱንም ማዳን ሳይችል ቀርቶ የእገላ ሜዳ ላይ የእፍኝ አፈር ቀብር አጥቶ የበረሀ ሲሳይ ሁኖ በየ ሜዳው አጥንቱ እንደተዘራ ባለበት የውግያ ቀጠና ነው ይህን ጦር እነዲገባ ትእዛዝ የተሰጠው)
ግንቦት 9/1992
 የቀድሞ ጦር አባላቱ ትእዛዙን የተቀበሉት ቢሆንም አንድ በልባቸው ያመቁት እና ሙሉ በሙሉ በሚስጥር ተነጋግረው የደመደሙት እቅዳቸውን ግልጽ ሳያወጡ ግንቦት 9 እንደሆነ በክ/ጦር አዛዣቸው አመካይነት አስደንጋጭ የሆነ ጥያቄያቸው አዲግራት ላይ ላለው ለግንባሩ አዛዥ ሳሞራ የኑስ በወታደራዊ ሬድዮ አቀረቡ
.
  ጥያቄው ለሳሞራም አስደንጋጭ ስለነበር እርሱም ጥያቄያቸውን በቀጥታ ለመለስ ዜናዊ አቀረበው፡፡
የቀድሞው ምልስ ጦር ጥያቄ “ውግያው እስከ የት ነው” የሚል ሲሆን በውስጧ ነገር ያዘለች እንደሆነ መለስም ሆነ ሳሞራ ተረድተውታል፡፡ይህንን ጦር አሁን ካለበት ምሽግ ማውጣት እንደማይችሉ እና የቀረቻቸው ሰአት ከ16 ሰአት እንደማይበልጥ ያውቁታል፡፡
.
የቀድሞው ጦር በ1983 ከአስመራ በምን አይነት ሁኔታ እንደወጣ ያውቀዋል፡፡ሻእቢያ ከአህዮች ጋር ቀላቅሎት እደነዳው ከድንበሩ ውጭ አውጥቶ እንደቆሻሻ መጣላቸው ዛሬም እንደ እግር እሳት ሲመዘምዘው ኖሯል፡፡ዛሬም ማንነቱን ሊያሳያቸው መሀላ አድርገዋል(ውግያው እስከ አስመራ ነው) የሚል፡፡አልያ ግን እግራቸውን እንደማያነሱ ነው የተነጋገሩት፡፡
.
 ዮድሞው ጦር እቅድ ውስጠ ወይራ እንደሆነ የተረዳው መለስ ከቀኑ 11 ሰአት ሲሆን የልቡን በልቡ ይዞ “ውግያው አስመራ ድረስ ነው” የሚል ምላሽ ተላከላቸው፡፡
.
የቀድሞ ጦር ለሊቱን ያጋመሰው በደስታ ነበር፡፡ንጋት ላይ ውግያውን የሚያበስረው መድፍ ደምጽ እንደተሰማ ያ….ፈሪ ተብሎ እንዳልባሌ የተወረወረ እና የህወሀት ጦር 1990 ለአራት ቀናት ያህል ምሽግ ሰብራለው በማለት የ30 ሺህ ጦር የረገፈበት(የዚህ ውግያ እልቂት ከአንደኛው አለም ጦርነት ቀጥሎ ብዙ ሰው ያለቀበት ነው)ን ይህን ሶስት ዙር የጠላትን ምሽግ ለመስበር ከ35 ደቂቃ ያለፈ ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ውግያው የተከፈተው በአንድ ሰአት ውስጥ ሲሆን በግንባሩ ከአድዋ ፊት ለፊት ካለችው ራማ ግንባር እስከ ዛላንበሳን ተሻግረህ መኖክሲቶ የተዘረጋ ውግያ ሲሆን ያ ..የቀድሞው ጦር በራሱ ምሽግ ያለውን አጠናቆ በስተ ግራ ዛላንሳ ላይ የሰፈሰውን እና ጠንካራ የተባለውን የኢሳያስ ልዩ ሀይል በጎን ብሽሽቱን ብሎት ወደ ፊት በማምራት የአ.አ – አስመራን የአስፓልት መንገድ በመያዝ ጉዞውን ወደ ፊት ሲያደርግ ሊያስቆመው የሚችል አንዳች ሀይል አልነበረም፡፡
በኢጣልያ የተሰራውን የፎርቶ የሀዲድ ምሽግ ደርምሶ ወደ አዲ-ቀይህ ጉዞውን ሲያደርግ ወያኔ ላብ በላብ ወሆን ጀምራለች፡፡
.
ግንቦት 10  ምሽት ላይ አዲቀይህ ላይ በድል ግርማ የሰፈረው ጦር ከወዲያ ማዶ ቀይ ባህር ላይ ያረፈውን የአስመራ መብራቶች ወጋገን እያየ እንቅልፍ አልወሰደውም፡፡
.
ንጋት ላይ ከፊቱ የሚጋረጠውን ሀይል አሽመድምዶ አስመራ እንደሚገባ ምንም ጥርጥር አልነበረውም፡፡ንጋት ላይ ግን የህወሀትን ትእዛዝ የጣሰውን ጦር የራሳችን ጀቶች ተኩስ ከፍተውበት ሲመለሱ ልክ የተመካከሩ ይመስል የሻእቢያ ጀቶች እንዳይሆን አድርገው መሸሸጊያ በሌለው አውላላ ሜዳ ሲቀጠቅጡት በአቅራቢያው ያሉት የኢት.አየር ሀይል ሂልኮፕተሮች አንዳች እርዳታ ሳያደርጉለት ተቀጥቅጦ የተረፈው ሀይል ወደ ሁዋላ ተመልሷል፡
.
ውግያው በተጠናቀቀ ማግስት ታድያ የቀድሞው ጦር አዛዦች የነ ጄኔራል ተስፋዬ ሀብተማሪያምንና ጄኔራል በሃይሉ ክንዴን የማዋጋት ችሎታ የሚመለከቱ የተለያዩ
ዜናዎችና ሪፖርታዦችም በፕሬስ ውጤቶች ታትመው ወጡ። ያኔ ታዲያ ኢህአዴጎች ደነገጡ።
የነርሱ ሠራዊት አቅመ-ቢስ መሆኑ መረጋገጡ በጣም አሳፈራቸው። ስለዚህ አንድ ሰው ሰራዊቱን ወክሎ በጋዜጣዊ መግለጫ ስም ማስተባበያ እንዲሰጥ ተመደበ። ለዚህ የተመረጠው ደግሞ ሜጄር ጄኔራል አባዱላ ገመዳ ነበር። እርሱም በሰኔ ወር 1992 ወደ ቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብሎ እንዲህ አለ። “ሀገርን ከወራሪ ለማስለቀቅ በተደረገው ርብርብ ውስጥ የደርግ ወታደሮች አስተዋጽኦ ኢሚንት ነው”
@ Ethiopia Lezelalem Tenure
Gemaa Saketa
Filed in: Amharic