>

የሰዎችን በግፍ ከቀዬአቸው መፈናቀል "ለምን?"  ለማለት ባለ ህሊና ሰው መሆን ብቻ በቂ ነበር ግን...!????! (የዋግ ነሽ ስዩም)

ትላንት ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ አማራዎችን ወገኖችን አይተን ከሀዘናችን ሳናገግም ዛሬ ደግሞ 406 አባውራዎች ትላንት የአማራ ርስት ከነበረው እና ወያኔ ለኦሮሞዎች ከሰጣቸው ክልል ተባረው ራያ እና ቆቦ ሰፍረዋል።
ከተወሰኑ ሰዎች ውጭ ለምን ብሎ የሚጠይቅ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ግን የለም። ኢትዮጵያዊነት ልክ እንደዚህ ፍርክስክሱ ወጥቷል የምንለው ለዚህ ነው። እስኪ ልብ ካላችሁ ታዲያ ሁላችሁም ብሄር ብሄረሰቦች፣  የመንግስት ደጋፊዎች በየጊዜው ከሚፈናቀለው አማራ ጎን ቆማችሁ ድርጊቱን ለምን አትኮነኑም?
ትግሬው፣  አፋሩ፣   ቤንሻጉሉና ሌላው ሌላው አይፈናቀልም አማራው ብቻ ለምን ይፈናቀላል ብሎ ለመጠየቅ አማራ መሆን አይጠይቅም ህሊና ብቻ በቂ ነው። ግን መንግስትን ለመጠየቅ ቀርቶ  እራሱን የሚጠይቅ ሰው የለም።
ታዲያ የትኛው ነው አንድነት የትኛው ነው ኢትዮጵያዊነት።
ጭራሽ አንዳንዶቹማ የጠሚውን አድናቆት እናጣጥምበት አትረብሹን የሚሉ ይመስላሉ። ለማነኛውም ግን ኢትዮጵያ የምትባል አገር በአሁኑ ሰአት ምስጥ የበላት ግንድ ትመስላለች አካሏ እንጅ ውስጧ ተቦርቡሮ አልቋል። መተሳሰብ፣ መረዳዳት፣  መተዛዘን የሚባለው ነገር እራሱ በብሄር ሁኗል። አማራ ደግሞ በብሄሩ ስላልተደራጀ ለብዙ ነገር ሰለባ ሁኗል።
አማራ ሆይ እባክህ ንቃና ተደራጅ። ያልተደራጀ ህዝብ አቀመቢስ እና ሁሉም የሚያጠቃው ይሆናል።

“… እናቶች በስለት ሲታረዱ አይትን ከቀስት ከጩቤ ተርፈን የወጣነውን እንዴት ነው ተመለሱ የምትሉን???

የአማራ ተፈናቃዮች –  አርትኦት አለማየሁ ማ/ወርቅ
“.. ከኦሮሚያ ክልል ብደሌ ዞን ዴዴሳ ወረዳ ነው የመጣነው ….
– ወደ አገራችን መግባት እንፈልጋለን ግን እንዴት ሆነን ነው የምንገባው???
– ከዛ የቀን ጭለማ ወጥተን ወደ ብርሀኑ ገብተናል እንዴት ነው “ተመለሱ” የምትሉን? ህይወታችንን ማቆየት እንፈልጋለን….
– ከልጆቼ ያዳንኲቸውን አድኛለሁ የተገደሉብኝን የሞተውን ሬሳ አይቼ እንዴት ነው የምመለሰው???
– ልጆቻችን ከጀርባችን ላይ እየተገነጠሉ እየቀሩ ፣ ሀብት ንብረታችን ወድሞ እንዴት ነው የምንመለሰው???
– ከቀስት ከጩቤ ተርፈን መጥተናል እንግዲህስ እዚሁ እንሙት እያልን ነው
ብዙ ስቃይ ሰቆቃ ከፊታቸው ላይ የሚነበብባቸው ሁለት እናቶች ናቸው ይህን ያሉት።
– በ1999 አ.ም ነው ይላል ሌላው የግፉ ሰለባ የሆነው የአማራ ወጣት
 –  በ1999 ቤተ ክርስቲያን ተቃጥሎ እናቶች በስለት እየታረዱ ማተብ አንበጥስ ሲሉ ከነበሩት አንዱ ልጅ አሁን አብሮኝ እዚህ አለ። በገጀራ ፊቱ ላይ ተመቶ ግማሹ የፊቱ አካል ተቆርጦ በተአምራት የዳነ ልጅ ነው። በወቅቱ በጋዜጣ ሁሉ ወጥቶ ነበር።
– መንግስት አረጋግተናል ግቡ ተቀመጡ ብሎ ከተቀመጥን በላይ በ2010 የካቲት ላይ እየደረሰብን ያለውን በደል እስከ ዞን ድረስ ሄደን አመለከትን
– “ለእናንተ መፍትሄ አይሰጣችሁም አማራ ስለሆናችሁ ውጡ ” አሉን።
ወዴት እንሄዳለን መሄጃ የለንም ብለን በተቀመጥንበት ለሊቱን የመከላከያ ሀይል እና የቀበሌው አመራሮች በሙሉ ወርዶ ሀብት ንብረታችንን በመዝረፍና በማቃጠል….
የተቀሩት ደግሞ ንብረታችንን ጭነን እንውጣ ሲሉ “የኦሮምያን ሀብት ይዛችሁ ወዴትም አትሄዱ” ብለው
ከመኪና አስወርደው አንገት አንገታቸውን ነው ያረዷቸው
– ከዛ መአት ወጥተን ይመለከተናል ለሚሉት አካላት በምናመለክትበት ጊዜ ወደዛው ተመልሳችሁ ኑሩ እንባላለን ።
የሀይማኖት፣ የኢኮኖሚ፣ የሞራል ጉዳት ደርሶብናል።
– የህገ መንግስቱ አስከባሪ ነን የሚሉ የፌደራል ልብስ የለበሱ ሰዎች ናቸው ንብረታችንን ዘርፈው ወደ እስር ቤት የወረወሩን … የሚለው ሌላው ወጣት ተፈናቃይ ወደ እዛ እንዴት ተመለሱ ይሉናል ህግ ነው እኮ ያዘረፈን ያስገደለን በማለት እንባ እየተናነቀው ብሶቱን ያሰማል…..።
ህግ ካለ በህግ አምላክ እንላለን ዜጎች ላይ ዘርን ተመርኩዞ የሚሰነዘር ጥቃት ይቁም !!!
Filed in: Amharic