>
5:13 pm - Sunday April 20, 7017

ከመቀሌው ስብሰባ ያልሰማናቸው የታፈኑ መረጃዎች (ከድር እንድሪያስ)

ከመጋቢት 22-25 #መቀሌ ላይ ተካሂዶ በነበረው ህወሃት ከመላው የሀገራችን ክፍል የኢህአዴግ አባላት እና አባል ያልሆኑ የየአካባቢው ተወካዮችን ሰብስቦ ባካሄደው የሰላም ኮንፈረንስ ብሎ በሰመየው ኮንፈረስ  ያልተሰሙ ብዙ ክስተቶች አሳልፎ ነበር።
ዋናዋናዎቹ
– ከትግራይ ከተለያየ ቦታ ተወክለው የመጡ ትንሽም ቢሆን ከህወሃት ይልቅ ለህዝቡ ቀረብ የሚሉ ተወካዮች ተሳትፈውበት ነበር
– ህወሃት ይቃውሙኛል የሚላቸውን የትግራይ ወገኖች እንዳይሳተፉ በትልቁ ጥረት አድርጓል። በተለይ የ #አረና ደጋፊዎች ዝር እንዳይሉ አድርጓል።
– ሁሉም የህወሓት ቱባ ባለስልጣናት ተሳትፈዋል።
– ሁለት ተሳታፊዎች ከትግራይ ክልል የመጡ ከሌላው ክልል የመጣው ተሳታፊ ከተናገረው የህወሓት ክፉ ስራ እና ከራሳቸው ክልል እና ህዝብ ካለው በደል ብዛት በስሜት ሲናገሩ እራሳቸውን ስተው ኮማ ውስጥ ገብተው ወደ ህክምና የተወሰዱ ሁለት ተሳቲፊዎች ነበር።
– ህወሓት የፈለገው ከሌላው ክልል የመጣው ህዝብ ስሜት ለመስማት ነበር ግን ከትግራይ የመጡትም እንዲህ እድል አግኝተን አናውቅም ችግራችን መቸም ባትፈቱትም የኢትዮጵያ ህዝብ ይስማልን ይወቅልን እንናገራለን በሚል ጭቅጭቅ ነበረ።
– የመጨረሻው 2 ቀናት ውስጥ ህወሓት ከትግራይ የመጡት እንዳይገቡ አድረገዋቸው ይሁን ወይስ ተሳታፊዎቹ ተስፋ ቆርጠው ቁጥራቸው ተመናምኖ ነበር። በዛም ዞምቢዎቹ ደስተኛ ነበሩ።
– ከሌላ ክልል የመጣውም ህዝብ ስሜቱን ያለፍረሀት ሲገልፅ ነበር።
መድረኩ ላይ የተነሱ ጥያቄዎች
ከትግራይ ክልል ተሳታፊዎች የተነሱት ግን ያልተሰሙ ጥያቄዎች
1. አንቀፅ 39 አያስፈልግንም። ነው እናንተ በድብቅ ያሰባችሁት ሴራ አለ??
2. ጠቅላይ ሚኒስቴር ሲመረጥ እናንተስ ለምን አልመረጣችሁትም?
3. በኢህዴግ ድርጅቶች አንድነት የለም በመካከላችሁ የተፈጠረውን ችግር ለምን አትናገሩም ?
4. አስቸኳይ አዋጁ ፓርላማ ላይ ውድቅ ሁኖ እያለ ለምንድን ነው ያፀደቃችሁት ??
5. በማሰር ችግር አይፈታም እያልናችሁ ሰው እያሰራችሁ ነው ያለው ፣ ስንነግራችሁ ደግሞ አረና ናቸው ፀረ ሰላም ናችሁ እያላችሁ ትፈርጃላችሁ
6. በቤተሰብ ነው የምሰሩት ስራ ሁሉ በመመሪያ እና በህግ የተደገፈ ስራ አትሰሩም
7. ለህዝብ የተበጀተ በጀት ለግል ጥቅም ነው የምታውሉት
8. ሀወሃት ነው ክፍፍል ያመጣብን እኛ አንድ ነን ከአማራው ጋር
9. ትግራይ ላይ የገመገመ ሀሳብ የሰጠ ጠላት ሁኗል። ለእኛ ግን ጠላታችን አማራ ኦሮሞ ሳይሆን ህወሓት ውስጥ ያላችሁ አመራሮች ናቸሁ
10. በችግር ተከበን ትግራይ አድጓል ይላላችሁ
11. የትምህርት ጥራት ሞቷል
12. የገበሬ መሬትን ለምን በሊዝ ይሸጣል?
13. አርሶ አደር ተገዶ ለምን ማዳበሪያ ይገዛል? ማዳበሪያ ይልወሰደ ሌላው ጥቅም ይቋረጥበታል
14. ስልጣን የኑሮ ማደላደያ ብቻ ነው እያገለገለ ያለው። የህዝብ ድምፅ አይሰማም።
15. ሙስና የሰሩ አመራሮች ለህግ አይቀርቡም። የሚያጋልጡ ሰዎች የአረና አባል ናቸው እየተባሉ ይታሰራሉ።
16. ከዞን በላይ ያሉ ባለስልጣኖች ፎቅ ሰርተዋል ህዝቡ ግን ረሀብ ላይ ነው።
17. አባላነት በውዴታ ሳይሆን በግዴታ ነው
18. ሁሉም ነገር የወረደ ሁኖ ህዝቡ በችግር እየተሰቃየ የሌለ እና ያልተሰራ ነገር ነው በውሸት ሪፖርት ነው የሚቀርበው።
19. የትራንስፖርት መኪናዎች ሀገር አቀፍ ሰሌዳ እንጅ በክልል መሰጠት የለበትም።
Filed in: Amharic