>
5:13 pm - Tuesday April 19, 1188

ባተሌው ጋዜጠኛ ጥላሁን በቀለ ይግለጡ (ተፃፈ በደረጀ ፍቅሩ - አርቲስት)

አቶ ጥላሁን በቀለ ይግለጡ ከእናታቸው ከወ/ሮ አሰለፈች ከበደ እና ከአባቱ ከፌተውራሬ በቀለ ይግለጡ በ1955 ዓም በቀድሞ ሐረርጌ ክ/ሀገር ጨለንቆ በሚባለው አካባቢ ተወለደ።
 ~~~~~
በልጅነት ዕድሜው ወደ አ/አ የመጣው ጥላሁን ዕድገቱ መነን እየተባለ በሚጠራው ሰፈር በአባቱ ፌታውራሬ በቀለ ይግለጡ መኖሬያ ቤት ሲሆን የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በዓማሀ ደስታ (እንጦጦ አምባ) የመጀመሬያ ደረጃ ት/ቤት የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ ቀእቴጌ መነን(የካቲት 12) ተምሮ አጠናቋል።
~~~~
ወቅቱ ደርግ ከልዩ ልዩ ሃይሎች ጋር ትግል ላይ የነበረበት ወቅት በመሆኑ በተዳጊ ወጣትነት እድሜው በኢህሀፓ ተወርዋሬነት ወረቀት በመለጠፍና በተመሳሳይ እንቅስቃሴ የተሳተፈ ሲሆን ወደ በኋላም በተደጋጋሚም የጎበኘውን የእስር ቤት ህይወት አሃዱ ብሎ የጀመረውም በቀበሌያቸው በሚገኙ አነስተኛ እስር ቤቶች እንደነበረ አብሮ አደጎቹ ይናገራሉ።
~~~~
አንዳንድ ሰዎች ጥቂት ስራ ሰርተው የእውቅና እና የአብት ማማ ላይ ይገኛሉ ፤ እንደ ጥላሁን ያለ እድል አብራው ያልቆመች ባተሌ ደግሞ በርካታ ስራዎችን ቢሰራምና ለአገር ለወገን የሚጠቅሙ ጉዳዮች ላይ ቢሳተፍም ምሰጋና ሳያገኝ ምስጋናው ይቅርና አንገቱን የሚያስገባበት ጎጆ እና የሚተዳደርበት ቋሚ ገቢ እንኳ ሳይኖረው እንደባይተዋር ባደገበት ከተማ እነደተንከራተተ ባተሌ እንደሆነ ያልፋል።
~~~~
እንዲህ የሚያስብለንን ጥቂት ያለፈባቸውን የህይወት መንገዶቹን ለመጥቀስ ያህል ጥላሁን በቀለ በ1977 ዓ.ም በሀረር ሁርሶ ጦር አካዳሚ የእጬ መኮንነት ኮርስ ተከታትሎ ለመቶ አለቃነት ማህረግ የበቃ ሲሆን ኢህሀዴግ ሀገሬቱን ሲቆጣጠር ወደ እስር ተወርውሮ ለአንድ ወር ከቆየ በኋላ በተሃድሶ ለመለቀቅ ቀቅቷል።
~~~~
ጋዜጠኛ መቶ አለቃ ጥላሁን በቀለ ከ1983 ዓ.ም በኃላ የነፃውን ፕሬስ በመቀላቀል በታዋቂዎቹ ማህበል ፣ፈታሽ፣ገናናው ፣ ሞገድ አምደ ሃይማኖት ጋዜጦች በዋና አዘጋጅነት እና በሬፖርተርነት የሰራ ሲሆን ነፀብራቅ የተሰኘ የራሱ ጋዜጣ በማቋቋም ተለይቶ በሚታወቅበት የምርመራ ጋዜጥኝነት ሰርቷል።
~~~~
ጥላሁን በጋዜጠኝነቱ ህይወቱ በርካታ ወከባና መከራዎች የደረሱበት ሲሆን በተደጋጋሚ ለክስ እና ለእስር ተዳርጓል። በአንድ ወቅት ከ25 በላይ ክሶች ተመስርተውበት እንደነበረም የሞያ ባልደረቦቹ መስክረዋል። ከሮያል ክራውን (የመጀመሬያ ሀይላንድ ውሃ) ጋር በተያያዘ በፈታሽ ጋዜጣ ያስነበበው የምርመራ ሬፖርት በአገር ደረጃ ብዙ ያነጋገረ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ለጥላሁን ግን ብዙ ዋጋ ያሰከፈለው ሆኖ አልፎል።
~~~~
ጥላሁን የአዲስ አበባ ዩንርቨስቲ ለአጭር ግዜ ያዘጋጀውን የፌልም ሰልጠና የተከታተለ እና ስልጠናውን መሰረት በማድረግም በአደባባዮች ላይ ለእይታ የበቃውን” አያትየው” የተሰኘውን ፌልም በደራሲና አዘጋጅነት ሰርቶ ለህዝብ አቅርቧል።
~~~~
ጥላሁን በአንድ ወቅት የኢትዮጵያን የመከላከያ ምስጢር ለግብፅ ደህንነቶች ለመሸጥ የተንቀሳቀሱትን ከፍተኛ መኮንኖችና ግለሰቦችን በማጋለጥ አጅ ከፍንጅ በማስያዝ አኩሬ ስራ እንደሰራ በወቅቱ በሬፖርተርና በልዩ ልዩ ጋዜጦች ታትሞ የወጣ ሲሆን የመከላከያ ሚኒስተር ግን ከአንዲት ሰርተፍኬት በስተቀር ምንም አይነት ሽልማትም ሆነ ኑሮውን ሊቀይርለት የሚችልበት ነገር እንዳለደረገለት እስከ ህይወት ህልፈቱ ቀን ድረስ በቁጭት እንደተናገረ ቁጭቱን ይዞ ከዚህ አለም በሞት የተለየ አአንጋፋ ጋዜጠኛ ነው።
~~~~
ጥላሁን በርካታ ያላሳካቸው ራዕይ የነበሩት ጋዜጠኛ ነበር። በአንድ ወቅት ለመስራት የሞከረው የፈጠራ ስራው ግን በአንድ ግዜ ሰዎችን ከአደጋ ሊያድን የሚችል መሳሬያ ፅንስ ሃሳብና ንድፍ ከሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር እና ከአህምሮዊ ንብረት ፅ/ቤት እውቅና አሰገኝቷል። ዕውቅናውን ይዞ ወደ ተግባር ለመለወጥ እላይ ታች ሲል እና በርካታ ጥረቶቹን ለአራት አመታት አድርጎ ውጤቶቹን ማየት ሳይችል በእንጥልጥል ላይ ህይወቱ በድንገት ሊያልፍ ችሏል።
~~~~
ጥላሁን በርካታ አክሲዮን ማህበራት አደራጅ ሆኖ ሰርቷል። የማርሻል አርት ፌዴሬሽኖች አማካሬና አደራጅ ሆኖ አገልግሏል።
~~~~
ለኢትዮጵያ መድሃኒት ቅመማ (ድራጊስቶች) ማህበር ዋና የመፅሔት አዘጋጅ ሆኖ ከመስራቱም ባሻገር ለጥቂት ወራትም በብራና ማተሚያ ቤት በአርታኢነትት ያገለገለ ፈርጀ ብዙ ባለሙያ ነበር።
~~~~
ጥላሁን የዕድል ጉዳይ ሆነና ኑሮውን መስመር ሊይዝለት ባለመቻሉ በድንገተኛ ዕመም ግንቦት 7 ቀን 2010 ዓ.ም በ55 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።
~~~~
ጥላሁን የሁለት ልጆች አባት ሲሆን ግንቦት 9 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቀጨኔ መድህን አለም ቤተክርስቲያን የቀብር ሰነ-ስርሃቱ ተፈፅሟል።
– ይህ ፅሁፍ ዛሬ የወጣው  የሐበሻ ወግ መፅሔት ላይ የተወሰደ ነው።
Filed in: Amharic