>

አገሬ ስለአንድ የዜጋው ነፍስ የሚጨንቅ መሪ አገኘች- እናት ሐሊማና ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶር አቢይ ወግ ! (ነቢዩ ሲራክ)

አገሬ ስለአንድ የዜጋው ነፍስ የሚጨንቅ መሪ አገኘች

እናት ሐሊማና ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶር አቢይ ወግ   !

* ለፈጣሪ አምላክ ምስጋና ይድረሰው  ! 

ነቢዩ ሲራክ
     ብርቱ ናት የምላችላሁ እናት ሐሊማ ለገንዘብ ሰብዕናዋን ሽጣ ለልጇ ፍትህ መከበር  ስለ እውነት ቃል እምነቷን ሳታዛንፍ 13 አመት በመከራና ስቃይ ተጓዘች … በ13 ኛው  አመት   ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር አቢይን አገኘች …እውነቷን ዘርግፋ አጫውታቸው ፣  ዶር አቢይም “እህ ” ብለው መስማት ያውቃሉና እናት ሐሊማን አዳመጧት  !
በመጨረሻም ”  አይዞሽ በልጅሽ ጉዳይከልዑላኑ ጋር  ተነጋግረናል ፣ አስፈላጊው ካሳችሁ ተከፍሏችሁ በቅርቡ ወደ ሀገር ትገቡ ዘንድ ስምምነት ላይ ተደርሷል  !  ” የሚል የደስታ ብስራት እናት ሐሊማን አበሰሯት  🙂 እናማ እናት ሐሊማን ስቃ ፈንድቃ የደስታ እንባ እያጎረፈች ተሳሳምን  !
እናንተ ሰብዕናን ያስቀደማችሁ የብላቴናው አጋሮች ሆይ ድሉ የሁላችሁም ነው  ! ምስጋናውም ለእናንተ ነው  ! ሀገሬ መሪ አግኝታለች ፣ የዜግነት የላቀ ክብሩ የተሰማኝ ታላቁ አርብ
 ጁምአ የፍትህ ዘመቻችን 13 ኛ ሳምንት ስኬት ምክንያቱ ብርቱው የእናት ሐሊማ ጽናትና የእናንተ አጋርነት ነው  !
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር አቢይ አህመድንና ዶር ወርቅነህን  ደጋግሜ አመሰግናለሁ  !
ለዚህ ደስ የሚል ቀን ላደረሰን ፈጣሪ አምላክ ምስጋና ይድረሰው  ! 
ግንቦት 10 ቀን 2010 ዓም
Filed in: Amharic