>

የዳንጎቴ ሀላፊን ጨምሮ በእንጭኒ ከተማ 3 በሶማሌ ክልል 11 ሰዎች ተገደሉ!

(ቬሮኒካ መላኩ)
አብይ አህመድ  በተለያዩ ዘርፎች ጥሩ እየሰራ ቢሆንም በአገሪቱ የተፈጠረውን አናርኪ በማስቆም ረገድ ቀሰስተኛ እየሆነ ነው።
* ቤኒሻንጉል ውስጥ በጋርዮሽ ዘመን ሰው መሰል ጎሬላዎች  ንፁሃን  ለማሰብ በሚከብድ ሁኔታ እየተጨፈጨፉ ነው።
* በዛሬው ቀን   አለምአቀፍ ካምፓኒ የሆነው የዳንጎቴ ስራ አስኪያጅ እና ሁለት ሰራተኞች ተገድለዋል።
ኃላፊው ዲፕ ካማራ፣ ፀሐፊያቸውና ሹፌራቸው የተገደሉት ከአዲስ አበባ 85 ኪሎሜትር ርቀት ውስጥ በምትገኘው ኢንጪኒ ከተማ ነው ።የገዳዩ ማንነትና ምክንያቱ ለጊዜው ባይታወቅም በክልሉ ተከስቶ በነበረው ተቃውሞ የፋብሪካው ማሽኖችና ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸው አይዘነጋም።
Deep Kamara ከዳንጎቴ ፋብሪካ ጋር በተያያዘ የአከባቢው ወጣቶች ላነሱት ተቃውሞ እውቅና ሰጥቶ የአከባቢውን ሽማግሌዎች ጉልበት ስሞ ይቅርታ የጠየቀ።
ሽማግሌዎቹም ይቅርታውን ተቀብለው ከእንግዲ ልጃችን ነህ ብለው በኦሮሞ ባህል መሰረት እርቅ አውርደው  ” ገለታ ” የሚል ስም አውጥተው ልጃቸው አርገውታል ።
የፋብሪካው ሰራተኞችም ሆኑ የአከባቢው ህዝብ  Deep Kamara ሳይሆን ባወጡለት “ገለታ” በሚል ስም የሚጠሩትና የሚወዱት ስራ እስኪያጅ ነበር ። ዛሬ መገደሉን መስማት አስደንጋጭ ነው ።
ግድያው በአዲሱ ጠ/ሚር ላይ ጥቁር ነጥብ ማስቆጠር የሚፈልግ አካል ገዳይ ስኳዱን በመጠቀም እንዳስፈጸመው የብዙዎች እምነት ሆኗል።
* በሱማሌ ክልልም በአብዲ ኢሌ ልዩ ፖሊስ በሁለት ቀን ብቻ 11 ሰዎች ተገድለዋል።
አብይ አህመድ ይሄን ቅጥ ያጣና ከውስጥ በተጠነሰሰ ሴራ የሚፈፀም አደገኛ  በንፁሃን ላይ የሚፈፀም ቴረር በፍጥነት ማስቆም ብቻ ሳይሆን ፈፃሚዎቹን የገቡበት ገብቶ ለፍርድ ካላቀረበ ከሀይለማሪያም ደሳለኝ ዘመን የበለጠ አናርኪ  ተፈጥሮና ከቁጥጥሩ ውጭ ሆኖ ድመቷ አቢዮት እንዳትበላው ያስጋል።
ይሄን የተቀነባበረ  የአናርኪ ረሲፒ  ቶሎ ካላጠፋው ለራሱም ያሰጋዋል ።
የሀይለማሪያምንም እድል ላያገኝ ይችላል።
Filed in: Amharic