>
5:13 pm - Tuesday April 19, 6355

የህወሓት ውድቀት ምክንያቶች እና ምልክቶች! (ስዩም ተሾመ)

ዶ/ር አብይ፤ አቦይ ስብሃት ነጋ፣ አቶ አባይ ፀሃዬ እና አቶ ዘርዓይ አሰግዶም በቅደምተከተላቸው መሠረት በጡረታ፣ በቲራ እና በቴስታ ብሎ ከስልጣን አስወግዷቸዋል፡፡ ነገር ግን፣ በተለይ እነዚህን ሶስት የህወሓት ባለስልጣናት ከማንኛውም ዓይነት የፖለቲካ ስልጣን ዘርጥጦ ማውረድ የነበረበት አብይ/ኢህአዴግ ሳይሆን የራሳቸው ፓርቲ ህወሓት ነበር፡፡ ምክንያቱም፣ አንደኛ፦ አቦይ ስብሃት ህወሓትን ከተመሠረተበት ግዜ አንስቶ በተንሸዋረረ እይታ እንዲመራ ያደረጉ ናቸው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ እንኳን በተለያየ ግዜ ስለ ኢትዮጲያ የሚናገሯቸው ነገሮች በተለይ በአማራ ልሂቃን ዓይን ውስጥ ሚጥሚጣ እንደመነስነስ ነበር፡፡ ሁለተኛ፦ አባይ ፀሃዬ የህወሓት እብሪትና ግብዝነት ትክክለኛ መገለጫ ነው፡፡ በተለይ በኦሮሚያ የታየው ህዝባዊ ተቃውሞን በመቀስቀስና አዲሱ የኦህዴድ አመራር ወደፊት እንዲመጣ #ከቄሮዎች ቀጥሎ ከፍተኛ አስተዋፅዎ ያበረከተው አባይ ፀሃዬ ነው ቢባል ማጋነን አይመስለኝም፡፡ ሶስተኛ፦ ኣይተ ዘርዓይ አሰግዶም የህወሓትን ድንጋጤና ውድቀት በብሔራዊ ቴሌቪዥን በይፋ የመሰከሩ ናቸው፡፡ የአማራ ቴሌቪዥን እና #OBN ለማስፈራራት ባዘጋጁት የውይይት መድረክ አቶ ንጉሱ ጥላሁን እርቃናቸውን ካስቀረ በኋላ “ስልጣን መልቀቅ አለብህ” እያለ ከተሳለቀባቸው  በኋላ ኣይተ ዘርዓይ ለአንድ ቀን እንኳን በስልጣኑ ላይ መቆየት አልነበረበትም፡፡ በአጠቃላይ ሶስቱም የህወሓት ባለስልጣኖች ከስልጣናቸው መውረድ የነበረባቸው ገና ድሮ ነው፡፡ ዶ/ር አብይ ያደረገው የህወሓት ውድቀት ምክንያቶች እና ምልክቶችን ማስወገድ ነው፡፡ ታዲያ ውለታው ለማን ነው??
Filed in: Amharic