>

ሼኩ ላይ የወረደው መአት ለእናንተስ የማይተርፍ መስሏችሁ ይሆን?!? (ሀይሌ በአንተ)

አንነካም፣ አንደፈርም የሚሉ ተመጻዳቂዎች፣ የስልጣን እና የሃብት ቁንጮ የተባሉ ሰዎች፣ በሰራዊታቸው እና በድርጅታቸው የሚመኩ፣ በሃብት በንብረታቸው የሚታበዩ ባለጸጋዎች ዛሬ የት ናቸው? #ሰዎቹ አትማሩም እንጂ የአድዋዎችን መለስ እና ፓትርያርኩን አለም እያያ በአንድ ሳምንት ወደ መቃብር ሲወርዱ ጥሩ መልእክት ነበር። እናም አሁንም ጊዜ መቀየሩ ላይቀር ሰከን በሉ። ግፍ በደሉ ይብቃ!
የሚድሮክ ጎልድ የለገደምቢ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ፍቃድ በኢትዮጵያ መታገዱ ብቻ አይደለም። ሞሮኮ የሚገኘው የሼክ አል አሙዲ ነዳጅ ማጣሪያ ኩባንያ የሆነው ኮራል ፔትሮሊየም ከአንድ አመት በፊት በፍርድ ቤት ትእዛዝ እንዲፈርስ ተወስኗል። ዛሬ ሰውየው ከአለም ሃብታሞች ስም ዝርዝር ወርደዋል። እሳቸውም ለጊዜው #ንብ ቲሸርት ለብሰው ሸራተን አይገኙም። ESFNA ቀጥሏል።
#Ethiopia : ሼክ መሀመድ አላሙዲን ከአለም የቢሊየነሮች ቁጥር ተርታ ውስጥ ወጣ:: #Forbes ሼክ መሀመድ አሊ አላሙዲ አሁን ያለው ንብረት ከ 13 ቢሊያን ዶላር ወደ አንድ ቢሊየን በታች በመውረዱ ቀጥራቸው 600 መቶ ከሚደርሱ ቢሊየነሮች ተርታ ውስጥ ስሙን አውጥቶታል:: የሼክ አላሙዲን ስም ፎርብስ ላይ እስከ 600 የአለም ቢሊየነሮች ቁጥር ተርታ ውስጥ በቢሊየነርነት የተመዘገበው ስሙ የለም:: አሊሙዲን ፎርብስ ላይ በ 2010 አንድ መቶ ሰባኛ በቅርቡ ደሞ ሰባ ሰባተኛ የአለማችን ቢልየነር ተብለው ተመዝግበው እንደነበር ይታወቅ ነበር:: አላሙዲን በዚህ አጭር አመት ውስጥ ይህን ያህል ሀብት አካብቶ ቁጥሩ ከፍ ማለቱ አለም ላይ አነጋጋሪ እንደነበርም የቅርብ ግዜ ትውስታ ነበር:: የሼኩ ንብረት 40 % በሳውዲ መንግስት ሲወረስ በሞሮኮ ያለው 20 % ሀብቱ መወረሱም ታውቋል::
Filed in: Amharic