>

"ታጋይ ማርታ በዘንዶ አልተበላችም" (እየሩሳሌም ተስፋው)

በእስር ጊዜዬ ካጋጠሙኝ ሰዎች መካከል የጉምሩኩ ምክትል ኃላፊ የገ/ዋህድ ባለቤት ኮሎኔል ሃይማኖት ተስፋዬ ሌላዋ ናት።
ሃይማኖት በሽብር ለተከሰስን ልጆች ጥሩ አመለካከት የላትም በአጠቃላይ በጣም ትጠላናለች።
ከርዕዮት አለሙ ጀምሮ እስከ እኔ ድረስ ብዙ አንገላታናለች። ሆኖም ወደ መጨረሻው ልትፈታ አካባቢ እሷም ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እየገባች ዘመዶቿም(ያሰሯት) በእሷ ተስፋ እየቆረጡ እኛ በመሃል ሰላም አገኘን ።
እኔና ኮሎኔል ሃይማኖት አንድ ቤት አልጋችንም አጠገብ ለአጠገብ ነበር። እንግዲህ በዚህ መሃል ነው አሁን እምነግራችሁን ታሪክ የመስማት እድሉ ያጋጠመኝ
ሃይማኖት በተለይ ፍ/ቤት ደርሳ ስትመጣ በጣም አዝና እያለቀሰች “ለኔ… ለኔ… ይሄ አይገባኝም ትላለች መሬቱን በእግሯ እየቆረቆረች”  የዛን ቀን ከኔ ጋር ሰላም ነው እምትሆነው ብዙ ነገሮችን በቁጭት ታወራኛለች በወሬ መሃል ዘንዶ ስለበላት ማርታ ጠየኳት
በጣም ተናደደች ፊቷ ተቀየረ ይህ በሬ ወለደ ውሸት ነው ማርታ ዘንዶ አልበላትም አንድ ውጊያ ላይ ነው የተሰዋችውም እኔም በቦታው ነበርኩ እንደው አማረልኝ ብሎ እማይመስል ነገር ማውራት አግባብ አይደለም አለች።
ግንቦት 20 በመጣ ቁጥር ከ 20 ዓመት በላይ ስንሰማው የኖረ ታሪክ ስለሆነ እውነት ነው ብዬ አምኜ ተቀብዬ ነበርና ከነባር ታጋይዋ ከአይን ምስክር ይሄን ስሰማ በጣም ገርሞኛል።
ታዲያ ለምን አንቺ እውነታውን ህዝብ እንዲያውቅ አታደርጊም? አልኳት ማለት ስላለብኝ እንጂ ምን ልመልስልኝ እንደምትችል እየገመትኩ ነው እሷ ግን ያልጠበኩትን መልስ ሰጠችኝ
አዎ ልኪያለው ሴት ታጋዮች ማህበር አለን እና ለእነሱ ልኪያለው ፤ ታሪክ አታንሻፉ ብዬ እንዲህ መሆን የለበትም አለችኝ።
እንግዲህ ይህ ነው እውነታው ታጋይ ማርታ ዘንዶ አልበላትም!!
Filed in: Amharic