>
5:13 pm - Wednesday April 19, 8541

ከሦስቱ ክፍፍሎች የትኛው ፍትሐዊ ክፍፍል ነው??? (አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

አንድ አንበሳና ዘጠኝ ጅቦች በጋራ ለአደን ወጡና በለስ ቀንቷቸው ዐሥር ቆርኪ አድነው ተመለሱ፡፡ ቀጣዩ ጉዳይ መካፈል ነበረና ጅቦቹ አንበሳውን ከመፍራትም ከማክበርም የማከፋፈሉን መብት ለአንበሳ ሰጡትና “አያ አንበሳ አንበሴ እርስዎ ያከፋፍሉ?” ብለው ተሽቆጥቁጠው ጠየቁ፡፡ አያ አንበሳ አንበሴ ግን እራሳቸው ጅቦቹ እንዲያከፋፍሉ ነገራቸው፡፡ ጅቦቹ እነኝህን ዐሥር ቆርኪ እንዴት መካፈል እንዳለባቸው ሲማከሩ ቢውሉም መግባባት ግን ሳይችሉ ቀሩ፡፡
ፍትሐዊ ክፍፍል ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው ስላመኑ ግን የክፍፍሉ መስፈርት ፍትሐዊ ክፍፍል መሆን እንዳለበትና በዚህ ጉዳይ ላይም ፈጽሞ እንደማይደራደሩ እንደምንም ደፍረው ለአያ አንበሳ አንበሴ ተናገሩ፡፡ ፍትሐዊ ክፍፍሉን አይቀበለንም ብለው ፈርተውት የነበረው አያ አንበሳ አንበሴም “መሆን ያለበት እሱ ነው!” ሲል ፍትሐዊ ክፍፍሉን እንደሚቀበለው ተናገረ፡፡ ይሄኔ ጅቦቹ ተደሰቱ ፈነጠዙ፡፡ አስተሳሰባቸው ግን ቡድናዊ ስለነበረ ፍትሐዊ ክፍፍልን በቡድናዊ አስተሳሰብ ዓይን ስላሰቡት ሊያገኙ የሚችሉትን ጥቅም አጡ፡፡
ቀጥ ብለው ሔዱና ለአያ አንበሳ አንበሴ “ክፍፍሉን መድበናል አምስት አምስት ቆርኪ ይደርሰናል! አምስት ቆርኪ ለእርስዎ አምስት ቆርኪ ደሞ ለእኛ!” በማለት ለአያ አንበሳ አንበሴ ተናገሩ፡፡ አያንበሳ አንበሴ ግን በአንድነት ተሰማርተን፣ አንድላይ አድነናል ስለዚህም አንድ ነን ብሎ ያስብ ነበርና ለእዳንዳንዳችን አንዳንድ ቆርኪ ይደርሰናል ብሎ እያሰበ እያለ በመሀከላቸው እኛና እርስዎ የሚባል ነገር በመፈጠሩ፣ የጅቦቹ ቡድናዊ አስተሳሰብና ፍትሐዊነትን በተሳሳተ መልኩ ለቡድናዊ አስተሳሰብ መጠቀሚያ ለማድረግ መሞከራቸው፣ ፍትሐዊነትን ከቡድናዊ አስተሳሰብ ውጭ ቢመለከቱት ኖሮ ክፍፍሉ ዘጠኝ ጎሽ እንዲደርሳቸው አድርጎ ይበልጥ ተጠቃሚ ሊያደርጋቸው ሲችል ቡድናዊነት የገነነባቸው ጠባብ በመሆናቸው፣ ከቡድናዊ አስተሳሰብ ውጭ ሌላ አስተሳሰብ ለማስተናገድ አለመፈለጋቸው በእጅጉ አስቀይሞት ተቆጥቶ የአምስት ለአምስት ክፍፍሉን “አልቀበልም!” አለና “እንደገና ደልድሉ!” ብሎ አዘዛቸው፡፡
ጅቦቹም አያ አንበሳ አንበሴን ስለፈሩ እየከፋቸው ስድስት ለአንበሳ አራት ለነሱ አድርገው መደቡ፡፡ ይሄንንም አልቀበልም አለ፡፡ እያጉረመረሙ ሰባት ለሱ ሶስት ለነሱ መደቡ፡፡ ይሄንንም “አልቀበልም ይሄ ፍትሐዊ አይደለም እንደገና ደልድሉ!” አለ፡፡ ጅቦቹም “አይ ከዚህ በኋላ እንኳን እርስዎ ይደልድሉ!” ብለው መለሱ፡፡
አያ አንበሳ አንበሴም ጅቦቹን “እናንተ ስንት ናቹህ?” ሲል ጠየቀ፡፡ ጅቦቹም “ዘጠኝ ነን!” ሲሉ መለሱ፡፡ እሱም “ከአንድ ቆርኪ ጋራ ዐሥር ሆናቹህ ማለትም አይደል?” ሲል ጠየቀ፡፡ “አዎ!” ብለው መለሱ፡፡ “እኔ ስንት ነኝ?” ሲል ጠየቃቸው፡፡ “አንድ ነዎት!” ሲል መለሱለት፡፡ “ከዘጠኝ ቆርኪ ጋራ ዐሥር ሆንኩ ማለትም አይደል?” ሲል ጠየቀ፡፡ “አዎ!” ሲሉ መለሱ፡፡ ከዚያ አያ አንበሳ አንበሴ “አዎ አሁን ዐሥር ለዐሥር ሆነናል ፍትሐዊ ክፍፍል ይሄ ነው!” ብሎ አንዷን ቆርኪ ሰጥቶ ዘጠኙን ለራሱ አስቀርቶ ሸኛቸው፡፡
ጅቦቹ አንዷን ቆርኪ ይዘው ከሔዱ በኋላ እርስበርሳቸው በጣም ተወዛገቡ “ይሄ ውርደት ነው! ለእኛ ለጅቦቹ ያለውን ንቀት ያሳያል፡፡ እንደገና ሔደን ተከራክረን ካልሆነም መክፈል ያለብንን መሥዋዕትነት ከፍለን በጉልበታችን ፍትሐዊ የሆነ ድርሻችንን ይዘን መምጣት አለብን!” ብለው እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው ሔዱና ከቦታው ደረሱ፡፡ አያ አንበሳ አንበሴንም በሚያስፈራ ግርማ ፊት ለፊት ጉም ብሎ አገኙት፡፡ እንዳያቸው በቁጣ “ምንድን ነው?” ሲል ጠየቃቸው፡፡ ጅቦቹ ተደነባበሩና “አይ እእእእእእ አደን ልንሔድ ፈልገን ይህችን ቆርኪ እርስዎ ጋር አደራ ለማቆየት ፈልገን ነው አያ አንበሳ አንበሴ!” ሲሉ በመፍራት በመንቀጥቀጥ መለሱ፡፡ አያ አንበሳ አንበሴም “እህ ነው እሽ አምጧት!” ብሎ ተቀበላቸውና “ሒዱ በሉ አድኑ!” አላቸው፡፡ ጅቦቹም ከነአንዲቷም እሷንም አስረክበው ሔዱ፡፡ ባዷቸውንም ቀሩ ይባላል፡፡
ይሄ ምሳሌ አግላይ የሆነው ዘውግን መሠረት ያደረገ የቡድናዊነት አስተሳሰብ ሌሎችን ምን ያህል ሊያስከፋ ሊያስቀይም የሚችል መሆኑን፣ እራሱን ቡድኑንም ሊያስጠቃው ሊያስገልለው የሚችል መሆኑን፣  አስተሳሰባችን የግል መብትን ዘንግቶ የቡድን መብት ላይ ሲመሠረት የቡድን መብትና ጥቅም የሚጎዳ ወይም
ፖለቲካዊ ጥቅም፣ መብትና ፍትሕ ግለሰብ ላይ ካልተመሠረተ ሁሉም ነገር የዚሮ ብዜት መሆኑን፣ የግል መብትንና ጥቅምን ማክበርና ለሱ መብት መጠበቅ መቆም ሲቻል የቡድን መብትም የበለጠ ተጠቃሚ መሆኑን ወዘተረፈ. ያሳያል፡፡
በተጨማሪም ምሳሌው ፍትሐዊ ክፍፍል በሦስት የተለያየ መንገድ እንደተፈለገ መተርጎም መቻሉንም ያሳየናል፡፡ ጉልበተኛ እስከሆንክ ጊዜ ድረስ ፍትሐዊ ክፍፍልን ለራስህ በሚመችህ መልኩ እየተረጎምክ ፍትሐዊ ያልሆነን ጥቅም በፍትሐዊ ክፍፍል ስም ለራስ ማግበስበስ መቻሉንም ያሳያል፡፡
እውነት እንነጋገር ከተባለ ኃያላን መንግሥታት ያለ ሐፍረት “ፍትሐዊ ነን!” እያሉ ጥቅማቸውን እያግበሰበሱ ያሉት አያ አንበሳ አንበሴ ለራሱ የፈረደበትን መንገድ በመጠቀም ነው፡፡ በመላው ዓለም ፍትሕ ከስሟ በስተቀር መልኳንና ይዘቷን ከቀየረች ከራርማለች፡፡ በግሌ ወደፊትም ቢሆን የፍትሕ አተረጓጎም በዚህ መልኩ ለራስ እንደሚመች እየተደረገ ይቀጥላል እንጅ ይቀናል ይስተካከላል የሚል እምነት የለኝም፡፡
በመሆኑም እኛም እንግዲህ እንደ አንበሳው የጅቦቹ ዘውገኛ ቡድናዊነት አንቅቶን አሳስቦን ቡድናዊነት ለራሳቸውም የማይጠቅም መሆኑን፣ ጥቅማቸውን እንደሚያሳጣቸው እንደማይጠቅማቸውም አስተምረን ዘውገኛ ቡድነኞችን መመለስ ከጠባብነት ደዌያቸው መፈወስ ካልቻልን ወይም የሚቻልበት ዕድል ከሌለ ጅቦቹ ፍርሐታቸው በለቀቃቸው አጋጣሚ አምስት ለአምስት ከማለት አልፈው እንደጅብነታቸው ዐሥር ለባዶ በማለት ጉድ እንደሚሠሩ ይታወቃልና ጊዜ ሳናባክንና እራሳችንን ሳናስበላ የአንበሳውን የፍትሐዊ ክፍፍል አተረጓጎም መጠቀም የግድ እንደሚኖርብን ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡ ይሄንን ማድረግ ካልቻልን የአማራ ሕዝብ ህልውና አደጋ ላይ መሆኑን አጥብቄ ማሳሰብ እወዳለሁ!!!
ምሳሌ እንጥቀስ፦ በዚህ የወያኔ የ27 ዓመታት ጎሳ ተኮር ቡድናዊ አገዛዝ የሌሎቹ ጎሳ ብሔረሰቦች መብትና ጥቅም የአማራ ክልል ባሉት የልዩ ዞንና ሌሎች መብትና ጥቅሞች ሳይሸራረፉ ብቻ ሳይሆን ከአማራውም በላይ ሲከበሩ ሲጠበቁላቸው አማራ ግን ያውም መብቱ የሆነውንና በሕጋቸው ላይ ሠፍሮ የሚገኘውን መብትና ጥቅም የምንትስ ክልል የምንትስ ክልል እያሉ በከፋፈሉት የሀገሪቱ ክፍል በአንዱም ላይ እንኳ ቢሆን ተከብሮና ተጠብቆ አያውቅም፡፡ ወደፊትም ይጠበቃል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ይሄ ያለጥርጥር የጅቦቹ የዐሥር ለባዶ የክፍፍል ስሌት ነው፡፡ ይሄ ግፍ የተሞላበት የጅቦች ስሌት አማራን ከጥቂት ዓመታት በኋላ ከገዛ ሀገሩ ከኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ አጥፍቶ ታሪክ አድርጎት ሊያስቀረው የሚችል ስሌት ነው፡፡ ምክንያቱም ጅቦቹ አማራ ያለውን ሀብት ሁሉ ለመንጠቅ ለመውሰድ ሲሉ አማራን ማጥፋት ቀላሉ አማራጭ እንደሆነ አምነው ሲሠሩበት ከርመዋልና ነው፡፡ አማራ ሆይ ንቃ! ንቃ! ንቃ! ተበልተህ ሳታልቅ ንቃ! ጅቦቹ ከጅብነት ባሕርያቸው መቸውንም ቢሆን የሚላቀቁ አይሆኑምና ፍትሐዊና የእኩልነት አስተሳሰብህን እርሳው! እርሳውና ይሄንን አንበሳ ሁን!!!…
ድል ለአማራ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
Filed in: Amharic